የቱርክ ርዕደ መሬት፡ እናትና ልጅን ጨምሮ 5 ሰዎች በፍርስራሽ ውስጥ ከ9 ቀናት በኋላ በህይወት ተገኙ

የቱርክ ርዕደ መሬት

የፎቶው ባለመብት, FACEBOOK/MAYOR MUZAFFER BIYIK

ታትሟል

በቱርክ ርዕደ መሬት ከተከሰተ ከዘጠኝ ቀናት በኋላ 5 ሰዎች በፍርስራሾች ውስጥ በህይወት ተገኝተዋል።

ከነዚህ ውስጥ አንዷ የሁለት ልጆች እናት ስትሆን የተቀሩትም ሴቶች ናቸው።

የ42 ዓመቷ ሜሊክ ኢማንጉሉ እና የ74 ዓመቷ ሴሚሊክ ኬኪትስ በርዕደ መሬቱ ክፉኛ ከተጎዳችው ካሃራማንማራሰ ከተማ ፍርስራሽ ውስጥ በነፍስ አድን ሰራተኞች በህይወት ተገኝተዋል።

ከዘጠኝ ቀናት በፊት ከተከሰተው ርዕደ መሬት በኋላ ከተማዋን በማጽዳት ላይ የነበሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች ናቸው የሰዎቹን ህይወት የታደጉት።

በሶሪያና ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እየኖሩ ሲሆን የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

የዳርካ ከተማ ከንቲባ ሙዛፈር ቢያክ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩት ቪዲዮ የነፍስ አድን ሰራተኞች የ74 ዓመቷ ሴሚሊክ ኬኪትስን እያበረታቱ ወደ አምቡላንስ ሲጭኗቸው አሳይቷል።

በሌላ በኩል የ42 ዓመቷ ሜሊክ ኢማንጉሉን ነፍስ አድን ሰራተኞች በህይወት ሲያገኟቸው አድናቆታቸውን እንደገለጹላቸው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በርዕደ መሬቱ ክፉኛ በተጎዳችው ሌላኛዋና አንታይካ በተባለችው ከተማ አንዲት እናት ከፍርስራሽ ውስጥ ከሁለት ልጆቿ ጋር በህይወት ተገኝታለች።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከተከሰተ አስር ቀን የሞላው ሲሆን ከነዚህ ቀናት በኋላ ሰዎችን በህይወት ማግኘት ከባድ ይሆናል። በርዕደ መሬቱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 41 ሺህን ተሻግሯል።

አሁን ላይ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ መጡባቸው ቦታዎች ለመመለስ ዝግጅት የጀመሩ ሲሆን የሀገር ውስጦቹ ደግሞ ትኩረታቸውን ፍርስራሾችን ማስወገድ ላይ አድርገዋል።

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ዳግም መቋቋም ይጠበቅባቸዋል። የቱርክ መንግስት ከመሬት መንቀጥቀጥ ጋር በተያያዘ የሚኣሰጋ ነገር እንደሌለ በማሳወቅ የሚችሉ ሰዎች ወደቤታቸው እንደሚለሱ እያበረታታ ነው፥።

ሆኖም በርካታ ሰዎች መኖሪያ ቤታቸውን በአደጋው ያጡ ሲሆን በጊዜያዊ መጠለያዎች ለመግፋት የተገደዱ ናቸው። ሴቶቹ በህይወት በተገኙበት ካሃራማንማራሰ ከተማ 1 ሺህ ሰዎች በአከባቢው ባለው ስታዲየም ተጠልለው ይገኛሉ።

በሶሪያ ደግሞ ሀገሪቱን የከፋፈለው የእርስ በእርስ ጦርነት የእርዳታ ተግባሩን አስተጓጉሏል።

የመንግስታተቱ ድርጀት የሎጀስቲክስ ችግር እንደገጠመው በመግለጸ በሶሪያ ለቀናት ሰብአዊ እርዳታ ማቅረብ አልቻለም ነበር።

በቱርክ የሚያቁርጠው ድንብር ተከፍቶ ነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ ሶሪያ ከገቡ በኃላ ፍርስራሹን ለማስወገድ የሚያስፈልጉ ከባድ መሳሪያዎችን ማግኘት አልቻሉም ነበር፥

“የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብና ተመድ እርዳታ ያለቀረቡበት አጋጣሚ ተፈጥሮ አያወቅም” ሲሉ በአከባቢው የሚደረገውን የነፍስ አድን ስራ የሚመሩት ራድ ሳል ተናግረዋል።