የዩክሬን ጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን የዩክሬን የደኅንነት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ

የዩክሬን የጦር ደኅነነት ኤጄንሲ ኃላፊ ክይርይሎ ቡዳኖቭ 
የምስሉ መግለጫ, የዩክሬን የጦር ደኅነነት ኤጄንሲ ኃላፊ ክይርይሎ ቡዳኖቭ 
ታትሟል

ሩሲያም ሆነች ዩክሬን ወሳኝ የሆነ ግስጋሴ ባለማሳየታቸው በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት አሁን ላይ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን የዩክሬን የጦር ደኅነነት ኤጄንሲ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ። ይሁን አንጂ ኪዬቭ አሁንም ከምዕራባውያኑ አጋሮቿ የሚላክላትን ተጨማሪ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን እየጠበቀች ነው።

 ኃላፊው ክይርይሎ ቡዳኖቭ  ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ  “ አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ባለበት ቆሟል። ወደ ፊት እየሄደ አይደለም” ብለዋል።

የዩክሬን ወታደሮች ኅዳር ወር ላይ ደቡባዊ ከተማዋን ኼርሶንን መልሰው ከያዙ በኋላ አብዛኛው ጦርነት እየተካሄደ ያለው በምስራቃዊ ዶንትስክ ክልል በምትገኘው ባክህሙት አካባቢ ነው።

በሌላ አካባቢ የሩሲያ ኃይሎች  ወደ ማጥቃት ተሸጋግረው የነበረ ቢሆንም የክረምቱ ወቅት ዩክሬን የምታካሂደውን የምድር ዘመቻ ፍጥነት ጋብ እንዲል አድርጎታል።

ኃላፊው ቡዳኖቭ እንዳሉት ሩሲያ አሁን ላይ መጨረሻዋ ላይ ተቃርባለች። ከባድ ኪሳራ ደርሶባታል።" ብለዋል።

ቡዳኖቭ አክለውም ክሬሚሊን ሌላ ንቅናቄ ለመፍጠር ወስናለች ያሉ ሲሆን የዩክሬን ኃይሎችም በበርካታ ቦታዎች ወደፊት ለመግፋት የመሣሪያ ግብዓት እጥረት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

“ በአጠቃላይ በሁሉም አቅጣጫ ልናሸንፋቸው አንችልም።እነርሱም ይህን ማድረግ አይችሉም። አዲስ እና ዘመናዊ መሣሪዎች አቅርቦትን እየጠበቅን ነው” ብለዋል።  .

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሩሲያ ጦር ተደጋጋሚ ውድቀት በኋላ፤ የዩክሬን ባለሥልጣናት የሞስኮ ኃይሎች በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ በቤላሩስ በኩል  የምድር ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉ ሲያስጠነቅቁ ነበር።

ወደ ፊት መግፋታቸውም ዋና መዲናዋን ኪዬቭን የመቆጣጠር ሁለተኛ ሙከራን ሊያካትት እንደሚችል እና ለዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በሩሲያ የሰለጠኑ ተጠባባቂ ኃይሎች ሊሳተፉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ቡዳኖቭ  እንደሚሉት በቤላሩስ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እንቅስቃሴን ጨምሮ የሩሲያ እንቅስቃሴ የተደመሰሰ ቢሆንም ዩክሬን ጦሯን በደቡብ እና በምስራቅ የውጊያ ቀጠና ወደ ሰሜን ፊቷን እንድታዞር የማድረግ ሙከራ ግን አለ።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

በቅርቡ የሩሲያን ወታደሮችን የጫነ ባቡር  በቤላሩስ እና ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ቆሞ ከሰዓታት በኋላ  ወታደሮቹን እንደያዘ ተመልሷል።

“ይህ የሆነው በግልጽ ነበር። ባንፈልግም እንኳን ማንም ሰው ማየት ይችላል” ሲሉም ኃላፊው በቤላሩስ የሚያሰጋ ነገር አለማየታቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስም ኪዬቭንም ሆነ በቤላሩስ በኩል ሰሜናዊ አካባቢዎችን ለመውረር የሚደረግ ዝግጅት እንደሚኖር የሚያሳይ ምልክትም አላየሁም ብለዋል ኃላፊው።

ቢቢሲ በኪዬቭ ተገኝቶ ከቡዳኖቭ ዲምሊይ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በሦስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤላሩስ ዋና ከተማ ሚኒስክ ከተጓዙ በኋላ ነው።

የፕሬዚደንቱ ጉብኝትም ቤላሩስ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን እንድትልክ የረጅም ጊዜ አጋራቸውን ፕሬዚደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮን ለማግባባት ይሞክራሉ የሚሉ ግምቶች እንዲነሱ አድርጓል።

ቤላሩስ ለሩሲያ ኃይሎች ጥቃት መፈፀሚያ ሆና አገልግላለች። ይሁን እንጂ ኃላፊው እንደሚሉት  የቤላሩስ ማኅበረሰብ አገሪቷ በጦርነቱ ያላትን ተሳትፎ አይደግፉም። ተንታኞች 48 ሺህ ወታደሮች ያሉት ጠንካራ ጦር ዝግጅት ላይ ግን ጥያቄ አንስተዋል።

ለዚህም ነው ፕሬዚደንት ሉካሼንኬ አገራቸው ላይ አደጋ እንዳይከሰት ለመከላከል ሁሉንም እርምጃዎች እየወሰዱ ያሉት።

ዩክሬን ኼርሶንን መልሳ ከተቆጣጠረች በኋላ ኃይሎቿ ከሩሲያ ወታደሮች ጋር በባክህሙት አካበቢ ደም አፋሳሽ ጦርነት አካሂደዋል።

ለሩሲያ  ከተማዋን መቆጣጠሯ የዩክሬን የድጋፍ መስመር እንዲቋረጥ የሚያደርግ ሲሆን ወደ ምስራቃዊ ክፍል ክራማቶርስክ እና ስሎቪያንስክን ጨምሮ ወደ ምስራቃዊ ክፍል ለመገስገስ መንገድ ይከፍትላታል።

ጥቃቱ የተመራ ያለውም በሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በሆኑት ዋግነር ግሩፕ እንደነበር ቡዳኖቭ ተናግረዋል።  መስራቹ የቭጅኒይ ፕሪጎዚን ከተማዋን ለመያዝ በሩሲያ ባለሥልጣናት መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንዳለ ገልጸዋል።

ሩሲያ በጦር ሜዳዎች ከምታካሂደው ውጊያ ባሻገር ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ የዩክሬን ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ በማድረግ በሚሳይል እና ድሮን ጭምር የአየር ዘመቻዎችን እያካሄደች ነው።

ይህም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ሙቀት እና ውሃ  እንዳያገኙ አድርጓል። ይህ ጥቃት ሊቀጥል እንደሚችል፣ ነገር ግን ሩሲያ የሚሳይል አቅሟ እየቀነሰ በመምጣቱ እና የሩሲያ ኢንዱስትሪዎች ማቅረብ ስለማይችሉ በተመሳሳይ አቅም ጥቃቱን መቀጠል እንደማትችል ኃላፊው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ምንም እንኳን ኢራን አብዛኞቹን ለጥቃት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ( ድሮኖችን) እና ሚሳይሎችን ለሩሲያ የሰጠች ሲሆን ኃላፊው እንደሚሉት ምዕራባውያን አገራት በኒዩክሌር ፕሮግራሟ ምክንያት በማዕቀብ እየተንገዳገደች ባለችው ቴህራን ላይ ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ የተረዳችው ኢራን ለሩሲያ ሚሳይል ለማቅረብ ፈቃደኛ አልሆነችም ብለዋል ኃላፊው።  

በመሆኑም "ጦርነቱ አሁን ላይ ጦርነቱ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ሊሆን ይችላል" ያሉት ኃላፊው፣ ነገር ግን ዩክሬን ሩሲያ እንደ አውሮፓውያኑ 2014 የያዘቻትን ባህር ገብ መሬት ክሪሚያን ጨምሮ የተያዙባትን ሁሉንም ግዛቶቿን መልሳ እንደምትቆጣጠር እምነት አላቸው።

ዩክሬን ሶቭየት ሕብረት ከፈራረሰች በኋላ በ1991 ነጻነቷን ስታውጅ ወደነበረው ድንበሯ እንደምትመለስም ገልጸዋል።