ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በዩኬ አንዲት ነርስ ጨቅላዎችን በኢንሱሊን በመመረዝና በመግደል ፍርድ ቤት ቀረበች
በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ የሚሞቱ ጤነኛ ህፃናት ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ አንዲት ነርስ ፍርድ ቤት ቀረበች።
ሉሲ ሌቢ በቼስተር ሆስፒታል ውስጥ አምስት ጨቅላ ወንድ እና ሁለት ጨቅላ ሴቶችን በመግደል እና ሌሎች 10 ህፃናትን ለመግደል ሙከራ በማድረግ ፍርድ ቤት ቀርባለች።
አቃቤ ህግ ኒክ ጆንሰን እንዳሉት በሆስፒታሉ ህፃናት አራስ ክፍል ውስጥ ህፃናቱ በሞቱበትና በከፋ ሁኔታ በታመሙበት ወቅት በፈረቃ ላይ እንደነበረች ተናግረዋል።
የ32 ዓመቷ ነርስ ሉሲ በማንችስተር ክራውን ፍርድ ቤት የቀረበባትን 22 ክሶች ውድቅ አድርጋለች።
ነርሷ ከቀረቡባበት ክሶች መካከል አንድ ጨቅላን ሶስት ጊዜ ለመግደል መሞከሯ እንዲሁም ባዶ መርፌ የወጋችው ህፃንም ህይወቱ ማለፉንም ፍርድ ቤቱ ሰምቷል።
በፍርድ ቤቱ ጉዳዪ የሚመለከታቸው የአንዳንድ ህፃናት ቤተሰብ አባላትም በችሎቱ ተገኝተው ነበር።
የቼስተር ሆስፒታል እንደ ሌሎች በእንግሊዝ ውስጥ እንዳሉ ህሙማን ከሚበራከቱባቸው አጠቃላይ ሆስፒታል አንዱም እንደሆነ አቃቤ ህግ አስረድቷል።
ሆኖም ከሌሎች ሆስፒታል በተለየ መልኩ በቼስተር ሆስፒታል የአራስ (የህፃናት) ክፍል ውስጥ መርዛማ ነርስ ስራ እየሰራች ነበር ብሏል።
ከአውሮፓውያኑ 2015 በፊት በቼስተር ሆስፒታል በህፃናት ክፍል ውስጥ ያሉ የሕጻናት ሞት አኃዝ ከሌሎች ተመሳሳይ ክፍሎች ጋር ሊወደዳር ይችላል” ብለዋል አቃቤ ህጉ
ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ ባሉት 18 ወራት የሚሞቱት ህጻናት ቁጥር በመሰረታዊነት ከፍ ማለቱን እና በአስከፊ ሁኔታ የሚታመሙ ህፃናትም ቁጥር እንዲሁ ጨምሯል ተብሏል።
የሚሞቱ ህፃናት ቁጥር መጨመርም የሆስፒታሉ አማካሪዎች ማየት መጀመሩ።
በተጨማሪም ድንገት ተዝለፍልፈው ራሳቸውን የሚስቱ ህፃናትም ቁጥር መጨመርና ለማስነሳትም ሲሞክሩ ለህክምናው ምላሽ አለመስጠቱን የህክምና ባለሙያዎች መገንዘብ ጀመሩ።
ለህፃናት ሞት መጨመርና ድንገት ተዝለፍልፈው ለመውደቅም ምክንያቱ ምንድን ነው ብለው ሲመረምሩም አንድ ተመሳሳይ ነገር ያገኙት በነዚህ ክስተቶች ውስጥ የነርሷ መገኘት ነው።
የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ፖሊስ ሞቱንና ክስተቶችን እንዲመረምር ጠርተዋል። በአውሮፓውያኑ 2015- 2016 ባለው ጊዜ ሁለት ህፃናት በኢንሱሊን መመረዛቸውንና ሆን ብሎ የተመረዙ መሆኑንም መረጃዎች አግኝቷል።
ከዚያ በኋላ የሚሞቱ ህፃናት ቁጥር ከፍ ያለ ሲሆን እነዚህ ወንጀሎች ሲፈጸሙም ነርሷ በስራ ፈረቃ ላይ ነበረች ተብሏል።
ነርሷ በወቅቱ የማታ የስራ ፈረቃን ትሸፍን የነበረ ሲሆን ወደ ቀንም ስትዛወር ሞቶቹና በአስከፊ ሁኔታም ተዝለፍልፎ መውደቅ ከሷ ጋር ወደ ቀን መዛወሩን አቃቤ ህግ መረጃ አቅርቧል።
በዚህም የሰባት ጨቅላዎች መሞትና እንዲሁም አስር ህፃናት በከፋ መታመም ምክንያቷ ነርሷ መሆኗም ተገልጿል። በአንዳንዱም ሁኔታ መጀመሪያ ልትገድል የሞከረችው ጨቅላ ባለመሳካቱ እንደገና መግደሏንና በአንዳንድ አጋጣሚም ሶስት ጊዜም እንደሞከረች ክስ ቀርቧል።
የፍርድ ሂደቱም እስከ ስድስት ወራት ድረስ ሊወስድ ይችላል ተብሏል።