አርሰናል፣ ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል. . .ከዓለም ዋንጫ በፊት የመጨረሻውን ጨዋታ እነማን ያሸነፋሉ?

ኳስ
ታትሟል

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለሳምንታት ከዓይን ሊርቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ ይቀረዋል። 

ሊጉ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ምክንያት ይቋረጣል።  

የአስራ ስድስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሑድ ይከናወናሉ።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታን ክሪስ ሱቶን የሊጉን አስር ጨዋታ ግምት አስቀምጧል።

ቅዳሜ 

ማንቸስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ 

ማንቸስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ 

ተጫዋቾች ድካም ላይ በመሆናቸው ከዓለም ዋንጫው በፊት አሰልጣኞች ከአቋም ጋር በተያያዘ እረፍት ለመስጠት ትልቅ ውሳኔ የሚሰጡበት ሳምንት ነው። 

ፔፕ ጋርዲዮላ ኃላፊነቱ ለክለቡ ስለሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሲቲ ነው። 

ሲቲ ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋቾች ከብዙ ልፋት በኋላ ከፍጹም ቅጣት ምት በተገኘች ጎል ቢያሸንፍም በዚህ ሳምንት ነገሮች ይቀሉታል። 

ብሬንትፎርዶች ከሜዳቸው ውጭ ጥሩ አይደሉም። ዘንድሮ ከሜዳቸው ውጭ ማሸነፍም አልቻሉም። 

ግምት፡ 4 - 0

በርንማውዝ ከ ኤቨርተን 

ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ዋንጫ ሲገናኙ ተጨዋቾቻቸውን ቀይረዋል። 

በርንዝማውዝ ማሸነፉን ተከትሎም አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ላይ ጫናዎች በርትተዋል። 

ይህ ጨዋታ ከሳምንቱ አጋማሽ እንደሚለይ እሙን ነው። 

ኤቨርተን የፊት መስመሩ ክፍተት አለበት በርንማውዝ ደግሞ በሁለት ጎል ከመምራት ነጥብ መጣል ቀጥለዋል። 

ግምት፡ 1- 1 

ሊቨርፑል ከሳውዝሃምፕተን 

ሊቨርፑል ከሳውዝሃምፕተን 

ናታን ጆንስ ሳውዝሃምፕተንን ይዘው ወደ አንፊልድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀናሉ። 

ዘንድሮ ለሊቨርፑል የምሰጠው ግምት በብዛት ባይሳካም ከቶተንሃም ጋር የነበራቸውን ጨዋታ በትክክል ገምቼ ነበር። 

በአቋም መዋዠቅ ምክንያት ቀዮቹ ስለማሸነፋቸው እርግጠኛ አይደለሁም። 

ክሎፕ ከዓለም ዋንጫው በፊት ድል ለማስመዝገብ እንደሚትሩ እገምታለሁ።

ግምት፡ 3- 0  

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ክሪስታል ፓላስ 

ማንም የሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በመሆን ወደ ዓለም ዋንጫው እረፈት ማቅናት ስለማይፈልግ ፎረስት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደርጋል። 

ፎረስት ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ነበር። በኋላ ግን ተፍረከረኩ። 

በጨዋታው አንድ ነጥብ ከማግኘት ባለፈ በሳምንቱ አጋማሽ በተካሄድ የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታ ቶተንሃምን አሸንፈዋል። 

ፓላስ ደግሞ ጥሩ ከመጫወት ባለፈ የፊት መስመሩ ድንቅ ነው። ብዙ ጨዋታን መግደል የሚችሉ ተጫዋቾች አሏቸው። 

ግምት፡ 1- 2 

ቶተነሃም ከሊድስ

ቶተንሃም ከ ሊድስ 

የስፐርሱ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጫዋቾቻቸው መዳከማቸውን ገልጸዋል። 

የሊድሱ ጄሴ ማርሽ ደግሞ ከሊቨርፑል ድል በኋላ ከበርንማውዝም ሦስት ነጥብ ነጥቀዋል። 

የቶተንሃምን ተከላካይ መስመር ማመን ቢከብድም ለመጥፎው የሳምንቱ አጋማሽ ሽንፈት ምላሽ ይሰጣሉ። 

ይህ ሁለቱም ቡድኖች ሊያሸንፉት የሚችሉት ዓይነት ጨዋታ ቢሆንም ግምት የምሰጠው ለቶተንሃም ነው። 

ግምት፡ 3 - 1 

ዌስት ሃም ከሌስተር 

ሌስተር እያንሰራራ ሲሆን በዚህ ወቅት ውድድሩ እንዲቋረጥም አይፈልገም። 

የቡድኑ ተከላካይ መስመር ድንቅ ሲሆን ሃርቪ ባርነስ እና ጀምስ ማዲሰንም በጥሩ ብቃት ላይ ናቸው።

ይህ ፉክክር ያለበት ጨዋታ ሲሆን ዌስት ሃም ወደ ብቃቱ ጥግ ባይደርስም የሚሸነፍ አይመስለኝም። 

ግምት፡ 1- 1 

ኒውካስትል ከቼልሲ

ኒውካስል ከ ቼልሲ 

ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ጋር ጥሩ አልነበሩም። 

አርሰናሎች የራሳቸው አጨዋወት ሲኖራቸው ሰማያዊዎቹ ግን ወደ ፊት ሲሄዱ ምን መሥራት እንዳሰቡ የሚያውቁ አይመስልም ነበር።

ኒውካስሎች የትኛውም ውጤት ቢመዘገብ እስከ አራት ባለው ደረጃ ውስጥ የሚቆዩ ሲሆን በደረጃቸውም ሆነ በአጨዋወታቸው ደስተኞች ናቸው። 

ብዙ ጎሎች የሚቆጠሩበት ጨዋታ ባይሆንም ኒውካስሎች የሚያሽነፉ ይመስለኛል። 

ግምት፡ 1  0  

ዎልቭስ ከ አርሰናል 

ዎልቭስ ከ አርሴናል 

ዎልቭሶች በዚህ ጨዋታ በስቲቭ ዴቪስ ቢመሩም አዲስ አሰልጣኝ በመሾማቸው ለአርሰናል ከባድ ይሆናል። 

የአርሰናል ደጋፊዎች ትኩረታቸው ሊጉ ላይ በመሆኑ በሳምንቱ አጋማሽ ከካራባኦ ዋንጫ መውጣታቸው አያሳስባቸውም። 

ቡድኑ ቼልሲን ሲያሸንፍ በራስ መተማመን የነበረው ሲሆን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታም ለዋንጫ እንደሚፎካከሩ ጠቁመዋል። 

ካላቸው የአጥቂ እና የተከላካይ መስመር ጥንካሬ አንጻር ጨዋታውን ያሸንፋሉ። 

ግምት፡ 0 - 2 

እሑድ 

ብራይትን ከ አስቶን ቪላ 

አዲስ አሰልጣኝ በመሾም ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸነፉት ቪላዎች ድላቸውን ማስቀጥ ይፈልጋሉ። 

ከተከታታይ ድል በኋላ ብራይተኖች ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። 

አሁን ባላቸው አቋም እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ቢያጠናቅቁ ይገባቸዋል። 

ግምት፡ 2 - 1 

ፉልሃም ከ ዩናይትድ

ፉልሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ 

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በመጀመሪያዎቹ ወራት የዩናይትድ ቆይታቸው ደስተኛ ቢሆኑም ችግሮችን በሙሉ እንዳልፈቱ ባለፈው ሳምንት ተመልክተናል።

ቡድኑም የዓለም ዋንጫውን እረፈት በመጠቀም መደራጀት ያለበት ይመስለኛል። 

አሰልጣኙ ሃሪ ማጓየርን አጥቂ በማድረግ እና ሮናልዶን አምበል በማድረግ ግራ አጋቢ ውሳኔ አሳልፈዋል። 

ከሜዳ ውጭ ሦስት ጊዜ የተሸነፈው ቡድናቸው ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። 

ፉልሃም ባለፈው ሳምንት በ10 ተጫዋች ካሸነፋቸው ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ መጥፎ ባይሆኑም የማሸነፍ መተማመን አልነበራቸውም። 

በሜዳቸው ድንቅ ድል በማስመዝገብ ወደ ዓለም ዋንጫው ይጓዛሉ ብዬ አስባለሁ። 

ግምት፡ 2 - 1