ሮዛ ደረጀ አራተኛ በወጣችበት የማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ፔሬስ ጄፕቺርቺር አሸነፈች

ታትሟል

በሰሜን ጃፓን በምትገኘው ሳፖሮ ከተማ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ፔሬስ ጄፕቺርቺር ለአገሯ ኬንያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች።

በማራቶን የዓለም ሪከርድ ባለቤት የሆነችውን ብሪጅድ ኮስጌይን በጨረሻው ሰዓት በማሸነፍ ሁለት ሰዓት ከ 27 ደቂቃ ከ 20 ሰከንድ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው።

አሜሪካዊቷ ሞሊ ሲይድል የእስራኤሏ አትሌት ውድድሩን ለመጨረስ አምስት ኪሎ ሜትሮች ሲቀራት ውድድሩን ማቆሟን ተከትሎ የነሐስ ሜዳሊያ ለመውሰድ ችላለች።

ኢትዮጵያዊቷ ሮዛ ደረጀ በውድድሩ አራተኛ ሆና አጠናቃለች። ብርሃኔ ዲባባ እና ዘይነባ ይመር ሌሎች ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩ አትሌቶች ሲሆኑ ውድድሩን አቋርጠው ወጥተዋል።

አንድ ሰዓት ላይ ሊደረግ ታስቦ የነበረው የማራቶን ውድድሩ በነበረው ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ወደ 12 ሰዓት ተዘዋውሮ ተጀምሯል።

የኬንያ ቡድን ከምንጊዜውም ፈጣን የማራቶን ሯጮች መካከል ሦስቱን ቢያሰልፍም በዶሃ የወርቅ ሜዳሊያ በመውሰድ የዓለም ሻምፒዮን የነበረችው ሩት ቼፕንቼቲች ሰላሳ ኪሎ ሜትር ላይ አቋርጣ ወጥታለች።

ጄፕቺርቺር እና ኮስጌይ አምስት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩ ሲይዴል እና ሳልፕተር ሲመሩ የቆዩበትን የፊተኛውን ቡድኑ ተቀላቅለዋል።

ኬንያዊያኑ አትሌቶች ጥለው ወጥተዋል።

የአውሮፓ የ10 ሺህ ሜትር ሻምፒዮን የነበረችውን ሳልፕተርን በድንገት መውጣቷን ተከትሎም ሴይዴል የነሐስ ሜዳሊያውን ለማግኘት ተወዳድራለች።

በለንደን ማራቶን የእውቋን ፓውላ ራድክሊፍን ሬኮርድ የሰበረችው እንግሊዛዊቷ አትሌት ኮስጌይ ከአሻናፊዋ ጄፕቺርቺር 16 ሴኮንድ ዘግይታ ገብታለች።

በቶኪዮ ማራቶን የእርምጃ ብሎም የሩጫ የማራቶን ውድድሮች በዋና ከተማዋ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሳፖሮ ከተማ ተዘዋውሯል

ባጠቃላይም 14 አትሌቶች ውድድሩን አቋርጠው የወጡ ሲሆን 74ቱ ውድድሩን አጠናቀዋል።