ጆርዳን ከውሃ በታች ወታደራዊ ሙዝየም ገነባች

ታትሟል

ጆርዳን ከውሃ በታች የሚገኝ ወታደራዊ ሙዝየም ይፋ አድርጋለች። በአቃባ የወደብ ከተማ የተገነባው ሙዝየም ለአገሪቱ የመጀመሪያው ነው።

አቃባ የምትገኘው በቀይ ባህር ዳርቻ ሲሆን፤ ሙዚየሙም ከቀይ ባህር በታች ተገንብቷል። ትላንት በተካሄደ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ከውሀ በታች የተቀመጡ ወታደራዊ መኪኖች፣ ታንክና ሄሊኮፕተር ታይተዋል።

ሙዝየሙ ለቱሪስቶች ተጨማሪ መዳረሻ እንደሚፈጥር የአካባቢው ባለ ሥልጣኖች ተናግረዋል።