BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በክርክር ላይ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው እንዲቋረጥ መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል? በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ምን ሃሳብ ቀረበ?
በሽብር እና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተከስሰው በፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠባቸው፣ እንዲሁም በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ ከ600 በላይ እስረኞች በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ከእስር ተለቅቀዋል። ከእስር የወጡት ሰዎች ጉዳያቸው "በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው" ለመንግሥት ጥያቄ በማቅረባቸው መሆኑ ተነግሯል። በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ለአገራዊ ዕርቅ ሁሉም በፖለቲካ ጉዳዮች የታሰሩ ሰዎች እንዲለቀቁ ሃሳብ መቅረቡን ተናግረዋል።
ቀጥታ, በኢራን ጦርነት ምክንያት አሜሪካ የወሳኝ ጦር መሣሪያዎች እጥረት እንደገጠማት ተገለጸ
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ፔንታገን ባወጣው ሪፖርት፣ ከኢራን ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የወሳኝ ጦር መሣሪያዎች እጥረት እንደተፈጠረ ተረጋገጠ። ይህም ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲናገሩ ከነበረው ፈጽሞ የሚቃረን ነው።
"ሐዘናችንን የበለጠ አክብዶታል" ልጆቻቸው በሳዑዲ በሞት ተቀጥተው መቅበር ያልቻሉ ወላጆች
የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንደሚያሳየው ሳዑዲ አረቢያ እስከ ሐምሌ 20 ድረስ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 116 ሰዎችን በሞት ቀጥታለች። የልጆቻቸውን መገደል የሰሙ ወላጆች ሐዘን ላይ ቢቀመጡም የልጆቻቸውን አስክሬን አግኝተው መቅበር ባለመቻላቸው እርማቸውን ማውጣት እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ።
ሶማሊላንድ በጋዛ ለሚሰማራው ዓለም አቀፍ ኃይል ወታደሮች ለማዋጣት ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብድራህማን መሐመድ አብዱላሂ መንግሥታቸው ሁለት ሺህ ወታደሮችን በጋዛ ይሰማራል ለሚባለ ዓለም አቀፍ የመረጋጋት ኃይል ለማዋጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ይህ የሚፈጸመው በይፋ ጥያቄ ከቀረበላቸው ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን አስተያየት የሰጡት በዋሽንግተን በተካሄደው "የመካከለኛው ምሥራቅ – አሜሪካ " ጉባኤ ላይ በተሳተፉበት ጊዜ ለእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ነው።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሊያጠፋን ይችላል?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውሎ ከፍተኛ ጥቅምን አስገኝቷል። በዚህም ውስብስብ ነገሮችን ከማቅለል አልፎ በርካታ ተግባራትን በቀላሉ ለመፈጸም አስችሏል። ይህ ደግሞ በተለያዩ መስኮች የሰዎችን ሥራ እየወሰደ እንደሆነ ሲገልጽ ቆይቶ አሁን ደግሞ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት እየተሰማ ነው
ቪዲዮ, አነጋጋሪ የሆነው የቻይናው ፕሬዝዳንት የካይሮ ጉብኝት
የቻይናው ፕሬዝዳንት ካይሮን በጎበኙበት ወቅት ግብፅ በአባይ እና በቀይ ባሕር ላይ የምታራምዳቸውን አቋሞች የሚደግፍ የጋራ መግለጫ ሁለቱ አገራት አውጥተዋል። የዓለማችን አንዷ ኃያል አገር ቻይና ይህንን አቋም ማንጸባረቋ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
ቪዲዮ, ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል። አንዳንዶች እንደ ኢራን እና እስራኤል ላሉ አገራት የተላለፈ መልዕክት አድርገው አቅርበውታል። ሌሎች ደግሞ ይህ ስምምነት አገራቱ ለደኅንነት ዋስትና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያላቸውን ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ሙሉው ስምምነት ለሕዝብ ይፋ ባለመሆኑ እየተሰሙ ያሉት መላምቶች ብቻ ናቸው።
ቪዲዮ, “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”
ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጦርነት ከተጀመረ ውጤቱ መሠረታዊ ለውጥን የሚያስከትል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
ህወሓት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን "ገለልተኛ አይደሉም" ማለቱ አንድምታው ምንድን ነው?
በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን ጦርነት ያስቆመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት በመሪነት ያደራደሩት የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛው ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ከህወሓት መሪዎች ከባድ ወቀሳ ቀርቦባቸዋል። የህወሓት መሪዎች የትግራይ ክልልን ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት በማድረግ ባሉት አሸማጋይ ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ ተነስቷል። ይህ ክስ ወደፊት ሊኖር በሚችል ንግግር ላይ ምን ተጽእኖ ይኖረዋል?
የዓለምን ገጽታ የቀየረው የመስከረም 1 ጥቃት 25ኛ ዓመት እና የስለላው ዘርፍ ያጋጠመው ውድቅት
ለብዙ አስርተ ዓመታት የተለያዩ መሪዎች እንደተናገሩት፣ የማንኛውም መንግሥት የመጀመሪያ ግዴታ ሕዝቡን መጠበቅ ነው። በአውሮፓውያኑ 2001 መስከረም 11 ቀን ግን አሜሪካ ይህንን ግዴታ ለመወጣት ሳትችል ቀርታለች። የስለላ መረጃዎች ቢኖሩም፣ የተለያዩ ፍንጮችን በጊዜው አገናኝቶ ተግባራዊ እርምጃ የወሰደ አልነበረም።
አሥመራ፡ በውሃ እጥረት የምትሰቃየው የኤርትራ ዋና ከተማ
"ትንሿ ሮም" በመባል የምትታወቀው አሥመራ አሁን መልክዓ ምድሯ ተለውጦ፣ ነዋሪዎቿ በከባድ የውሃ እጥረት የሚንገላቱባት ሆናለች። የከተማዋ ጎዳናዎች በቢጫና ሰማያዊ የውሃ ጄሪካኖች እንዲሁም ውሃ በሚያመላልሱ በእጅ የሚገፉ ጋሪዎች ተሞልተዋል። ነዋሪዎችን እያማረረ ያለው የውሃ እጥረት መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔስ ለምን አላገኘም?
ኤርትራ ግለሰቦች እና ተቋማት በሚይዙት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጣለች
የኤርትራ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ከባንክ ሥርዓት ውጭ ለተወሰነ ጊዜ መያዝ የሚችሉትን የጥሬ ገንዘብ መጠን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ማውጣቷን የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። በዚህም ግለሰቦች እና የተለያየ ደረጃ ያላቸው ተቋማት በይዞታቸው ሥር መቆየት የሚችሉት የገንዘብ መጠን ከመገደቡ በተጨማሪ ከሁለት ሳምንት በላይ ገንዘብ ይዘው ማቆየት የለባቸውም ተብሏል።
ቻይና በአባይ እና በቀይ ባሕር ጉዳይ የግብፅን አቋም ማንጸባረቋ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
ከፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የካይሮ ጉብኝት በኋላ ቻይና ከካይሮ ጋር ባወጣችው የጋራ መግለጫ “ናይል ወንዝ የግብፅ ዋነኛ የሕይወት መስመር መሆኑን” ገልጻለች። በመግለጫው ስለ አባይ ወንዝ እና ቀይ ባሕር የሰፈሩ አገላለጾች “የግብጽ ቋንቋ” መሆናቸውን ተንታኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ መግለጫ ሁለተኛዋ ልዕለ ኃያል አገር ቻይና በአባይ ጉዳይ ወደ ግብፅ ማዘንበሏን ያሳያል? የተንጸባረቀው አቋምስ ለኢትዮጵያ ምን ማለት ነው?
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች "የጦር ቁስለኞች እና ታጣቂዎች" ካልወጡ ተማሪ እንደማይመደብ ትምህርት ሚኒስቴር አስጠነቀቀ
ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ግቢዎቻቸውን "ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ" እንዲያደርጉ አስጠነቀቀ። የዩኒቨርሲቲዎቹ ካምፓሶች ውስጥ የሚገኙ "የጦር ቁስለኞች እና ታጣቂዎች" እስካልወጡ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተማሪዎችን እንደማይመድብ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ አየር ከሌሎች ከተሞች ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ተበክሏል?
ዛሬ ዓለም አቀፍ የንጹሕ አየር እና የሰማያዊ ሰማይ ቀን ነው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ጥናት እንዲሁም ሌላ ናሳ የሠራው ጥናት እንደሚያሳየው፤ በአዲስ አበባ የትራፊክ መጨናነቅ ባለባቸው ሰዓቶች እንዲሁም በዓመት በዓል ወቅት የአየር ብክለት ይጨምራል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ዋነኛ በካይ የትኞቹ ናቸው?
ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታ ሲለቀቁ 28 ይቅርታ ባለመጠየቃቸው ሳይፈቱ ቀሩ
ከአማራ እና ከኦሮሚያ ክልሎች በከባድ ወንጀሎች ተከስሰው በፌደራል መንግሥቱ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ከስድስት መቶ በላይ ሰዎች በይቅርታ መፈታታቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በተመሳሳይ ክስ ለዓመታት በእስር ላይ የቆዩ ነገር ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ 28 እስረኞች ደግሞ ሳይፈቱ ቀርተዋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
በሳምንታት ኢራንን ያንበረክካል ተብሎ ስድስተኛ ወሩን በደፈነው ጦርነት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመሩ ከስድስት ወራት በኋላ፣ አጭር ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ጦርነት፣ መጨረሻው ግልጽ ያልሆነ እና የተራዘመ ሆኗል። የካቲት 21/2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነቱን ሲጀምሩ በሳምንታት ውስጥ እንደሚቋጭ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ጦርነቱ ጋብ እያለ አስካሁን ዘልቆ ተጽእኖው በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?
ግብፅ ትቀላቀለዋለች እየተባለ ያለው ቱርክ፣ ሳዑዲ እና ፓኪስታን የመሠረቱት 'የሙስሊም ኔቶ'
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን 'የመካ ስምምነት'ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት "የሱኒ ስምምነት" ወይም "የሙስሊም ኔቶ" ሲሉ ጠርተውታል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
ባለ ፓስፖርት አይጦች እና ስለ ቲቢ የሚመራመሩት ኢትዮጵያዊ
አይጦች በጎ ስም የላቸውም፤ ሰዎች ከቤታቸው፣ ምግብ እና የተለያዩ እቃዎች ከሚያስቀምጡባቸው ሥፍራዎች አይጦችን ለማራቅ መርዝ ወይም መጥመድ ይጠቀማሉ። በአጠቃላይ አይጦች ከጥፋት ጋር ስለሚያያዙ በበርካቶች ዘንድ የተጠሉ ናቸው። ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ምርምር የሚያደርጉባቸው ባለ ፓስፖርት አይጦች ግን ለሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት ከፍተኛ ጥቅም አላቸው።
አጃኢብ!
በኢትዮጵያ 55 በመቶ ሴቶች ሚስትን ለመደብደብ የሚያበቃ ምክንያት አለ ብለው እንደሚያስቡ ጥናት አሳየ
በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያደረገው ጥናት አመለከተ። ሚስትን ለመምታት አሳማኝ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ብዛት ከሴቶች ያነሰ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር በ11 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
የአዲስ ዓመት አከባበር ሥርዓቶች በተለያዩ የዓለም አገራት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?
ቪዲዮ, ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች, ርዝመት 1,28
ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች
በአፍንጫ በሚገባ ውሃ አማካኝነት የሚከሰተው አንጎልን የሚያጠቃው አስፈሪው ተህዋስ
ባለፈው ዓመት በሕንድ በዚህ አንጎልን በሚያጠቃ ጥገኛ ተህዋስ የተያዙ ከ200 በላይ ሰዎች ተመዝገበዋል። ይህ ቁጥር በዓለም በአንድ አገር የተመዘገበው ከፍተኛው ሲሆን ከቅርብ ወራት ወዲህ በአገሪቱ እንዲህ ዓይነት ኬዞች መታየታቸውን ቀጥለዋል። ከዚህ በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የበሽታው ክስተቶች ከ500 ያነሱ ነበሩ።















































































































