የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ወቅት ወታደሮች ሚኒስትሮችን አግተው ነበር ተባለ

የፎቶው ባለመብት, AFP
የደቡብ አፍሪካ ግብረ ኃይል በኦፓርታይድ አገዛዝ ወቅት ላደረጉት ትግል ካሳ ይከፈለን በሚል የነፃነት ወቅት ወታደሮች ሁለት ሚኒስትሮችን አግተው እንደነበርና ነፃ መውጣታቸውንም አስታውቋል።
ኤኤንሲ ከነጮች አፓርታይድ አገዛዛዝ ወቅት ነፃ ለመውጣት በሚደረገው ትግል ወታደራዊ ክንፍ አቋቁሞ የነበረ ሲሆን የዚህም ክንፍ አባላት ናቸው በአሁኑ ወቅት ለቤተሰቦቻቸው የመኖሪያ ቤት እና የህክምና መድን የሚሆን 280 ሺህ ዶላር የአንድ ጊዜ ክፍያ እየጠየቁ ያሉት።
ትናንት ማምሻውን በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ በሚገኝ ሆቴል የካሳ ጥያቄያቸውን ለመደራደር የፕሬዚዳንት ሚኒስትሩ ሞንድሊ ጉንጉቤሌ ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ታንዲ ሞዲሴ እና ምክትላቸው ታባንግ ማክዌትላ ተገናኝተው ነበር።
ድርድሮቹ ፍሬ አለማፍራታቸውን ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናቱ ታግተው ነበር። በኋላ ላይ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ለመደራደር የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን ከ50 በላይ ሰዎች ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ተዘግቧል።
ሁኔታው ከመጋጋሉም ጋር ተያይዞ በፀረ-ሽብርተኝነት እና በታጋቾች ሁኔታዎች ውስጥ የሰለጠነው ልዩ ግብረ ኃይል መጠራት ነበረበት።
ሚኒስትሩ ሞንድሊ ጉንጉቤሌ ድርጊቱ "የማይታለፍ" እና "በሕግ ተቀባይነት የሌለው" ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም እነዚህ የነፃነት ታጋዮች ች በጭካኔ የተሞላውን የአፓርታይድ መንግስት ለመዋጋት ላደረጉት አስተዋፅኦ ካሳ ስላልተከፈላቸው በኤኤንሲ መንግሥት እንደተከዱ እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።
ነገር ግን፣ ወታደራዊ አርበኞቹ በየወሩ በመንግሥት የሚደገፍ ጡረታ ይሰጣቸዋል።
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይቡድኑ ከገዥው ፓርቲ ኤኤንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ በማሰማታቸው ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገዋል።












