በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ የቀረበው የመድፈር ክስ ውድቅ መደረግ አለበት ተባለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ የተከፈተው የመድፈር ክስ በፍርድ ቤት እንዳይታይ አንድ ዳኛ ሐሳብ አቀረቡ።
የ 36 ዓመቱ ተጫዋች እአአ በ 2009 በላስ ቬጋስ በሚገኝ ሆቴል አንዲት ሴት ላይ ጥቃት አድርሷል ተብሎ ጉዳዩ በፍትሐብሔር ህጉ መሰረት እየታየ ነበር።
ዓቃብያነ ህጉ ክሱ "ከጥርጣሬ በዘለለ ሊረጋገጡ አይችሉም" ሲሉ በሮናልዶ ላይ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንዳይከሰስ በ2019 ወስነዋል።
በደል ደርሶብኛል ያለችው ሴት የከፈተችው ካሳን የመሻት ጉዳዩ በፍትሐ ብሔር ሲታይ ሲታይ ቆይቷል።
ሮናልዶ ጥፋት አለመፈጸሙን ሲገልጽ ቆይቷል።
ሌላ ዳኛ የመጨረሻ ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት ጉዳዩን የገመገሙት ዳኛ ዳንኤል አልብረግስ በሮናልዶ እና በጠበቃዎቹ መካከል የተደረገውን ውይይት በህገወጥ መንገድ ያፈተለከ መረጃን በመውሰድ እንደማስረጃ ጥቅም ላይ መዋል ተገቢ አይደለም ብለዋል።
አልበርግስ "በተጠቂዋ ጠበቃ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ክሱን መሰረዝ አስከፊ ውጤት የሚኖረው ነው" ሲሉ ጽፈዋል።
"ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የሚያቋርጥ ትዕዛዝ ካልሰጠ፣ [የጠበቃዋ] ድርጊት በፍርድ ሂደቱ ሕጋዊነት ላይ ሰፊ እና አደገኛ ውጤት ሊያስከትል ይችላል።"
የሮናልዶ ጠበቃ ፒተር ክርስትሰን ምክሩ ሃሳቡን በደስታ ተቀበለዋል።
"በፍርድ ቤቱ በዚህ ጉዳይ በዝርዝር ገምግሞ እና ሕጉን በትክክል ለመተግበር እና ሮናልዶ ላይ ክሱ በየፍትሐ ብሔር ህጉ መስረት እንዳይከፈት መፍቀዱ አስደስቶናል" ብለዋል።
ከሮናልዶ ጋር ጉዳዩን ይፋ ላለማድረግ ከተጫዋቹ ጋር ከስምምነት የደረሰችው ግለሰብ ጠበቆች በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸው እንዲሰጡ ተጠይቀው ምላሽ አልሰጡም።












