"መቼም መመለስ እንደማልችል ተነግሮኛል" ከሩሲያ የተባረረችው የቢቢሲ ዘጋቢ

የፎቶው ባለመብት, Jonathan Ford
የቢቢሲዋ የሞስኮ ዘጋቢ ሳራ ራይንፎርድ የቪዛዋ ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በነሐሴ ወር መጨረሻ ሩሲያን ለቃ ትወጣለች። ታዲያ እርምጃውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዩኬ ለሩሲያ ጋዜጠኞች ቪዛ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኗ የተሰጠ የበቀል እርምጃ ነው ብለውታል። ሳራ ከምትወዳት ሩሲያ በመውጣቷ ስለተሰማት ሀዘንና ተያያዥ ጉዳዮች ለቢቢሲ ቱዴይ ፕሮግራም አጋርታለች።
"በርግጥ ቪዛዬ አለመታደሱ ችግር ቢሆንም ከሩሲያ የምባረርበት ዋና ምክንያት እሱ አይደለም። ከሀገሪቱ እንድወጣ ስደረግ መቼም መመለስ እንደማልችል ተነግሮኛል።
"እውነቱን ለመናገር ፣ በግሌ ጎድቶኛል ብቻ ሳይሆን አስደንግጦኛል። ሩሲያ በሕይወቴ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ያላት ሀገር ናት…
"ሳስበው በሩሲያ ውስጥ የኖርኩበት የሕይወቴን አንድ ሦስተኛ ያህል ነው። ስለዚህ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ቋንቋውን እየተማርኩ፣ ባሕሉን ፣ ታሪኩን እያጠናሁ፣ ሰዎችን ለመረዳት እየሞከርኩ እና እንደ ጋዜጠኛ ለብዙ ዓመታት ቆይቻለሁ።
"ምንም እንኳን አስቸጋሪ እየሆነ ቢመጣም የሩሲያ ጉዳይ ለዓለም ስዘግብ በጣም ደስ እያለኝ ነው። ይሄ ይሆናል ብዬ ግን አልጠበቅሁም ነበር። በሀገሪቱ ሚዲያ መጪውን ጊዜ የሚያመላክቱ ግልፅ ምልክቶች ይታዩ ነበር - በሩሲያ ለነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከባድ ፈተናዎች እየመጡ ነው፣ ግን እስከ አሁን ድረስ የውጭ ዘጋቢዎች ፣ በሆነ መንገድ ከዚህ ሁሉ ነጻ ነበርን።
"ግን አሁን የሆነው ነገሮች እንደተለወጡ ግልፅ ምልክት ያሳየ ይመስለኛል። የሩሲያን መንግስት የተመለከተ ሌላ መጥፎ ምልክት እና በሀገሪቱና በዓለም መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ታች የሚጎትት ነው። ይህ በራሱ ሩሲያ ራሷን ዝግ እያደረገች መምጣቷን የሚያመላክት ነው።
ያልተጠበቀው!
"ስለ አንድ ጉዳይ በይፋ ተነግሮናል [ቪዛውበእንግሊዝ ስለተከለከለ ወይም ስለዘገየበት ጋዜጠኛ] ከሁለት ዓመት በፊት የነበረ ጉዳይ ነው።
"በቺቼኒያ ውስጥ ይፈጸማሉ በተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በሙስና ምክንያት የዩኬ መንግሥት በሩሲያ ዜጎች ላይ ማዕቀቦችን መጣሉን ጨምሮ የተሰጡኝ የተለያዩ ምክንያቶችም አሉ። ሆኖም ማዕቀቡ በትልቅ አውድ የሚታይ በሩሲያ እና በእንግሊዝ መካከል ያለው ግንኙነት አልፎም በሩሲያ እና በምዕራቡ ዓለም ያለውን ግንኙነት መሻከሩን የሚያሳይ ነው።
"ይህ ያልተጠበቀ ፈንጂ ሲወረወር ይህንን ለሚሉኝ ሰዎች 'እኔ ጠላትህ አይደለሁም' አልኳቸው። ይህንን ሀገር ለመረዳት እና የዚህን ሀገር ጉዳዮች ለመዘገብና ለልቤ በጣም ቅርብ ነው የሆነውን ስራ ለመስራት የቻልኩትን ሁሉ አድርጌያለሁ።
'ሩሲያን የሚረዳና አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በሩሲያ ሰዎችን በቀጥታ እያናገረ ስለሩሲያ ለዓለም ለማስረዳት የሚሞክር የሆነን ሰው እያስወገዳችሁ ነው።' "
"እውነታው ግን እንደዚህ ያሉ ሰዎችን እዚህ አይፈልጉም። እዚህ የሚረዱት እና ሰሰዎች በቀጥታ እያናገሩ ታሪኮቻቸውን ከሚሰሙ ሰዎች ይልቅ ቋንቋውን የማይናገሩ ፣ አገሩን በጥልቀት የማያውቁ ሰዎችን ማግኘት በጣም ቀላል ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ የሚሄድ ጨቋኝ ሁኔታ እየተፈጠረ መምጣቱን የሚያመለክት ይመስለኛል።
የፈተና ወቅቶች
"በብዙ መንገዶች ሩሲያ ለብዙ ሰዎች የበለጠ ጠንካራ እና የተሻለች ቦታ ነች። በ1990 ዎቹ መጀመሪያ ሰዎች ምግብ ለመግዛት በቂ ገንዘብ ለማግኘት ንብረታቸውን ለመሸጥ በየመንገዱ ለመውጣት ተገደዋል።
በሱቆች ውስጥ ምግብ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር። እነዚያ አስፈሪ ፣ አስቸጋሪ ጊዜያት የ90 ዎቹ ነበሩ። እናም ማንም ሰው ወደ ኋላ መመለስ የማይፈልግበት ጊዜ ተብሎ የሚጠራውም ያ ነው።
"ሆኖም በተመሳሳይ ጊዜ የ90 ዎቹ ለሩሲያ አዲስ እና አስደሳች የነፃነት ጊዜ ነበሩ ፣ እና እንደ ጋዜጠኝነት ያኔ የነበረኝ የሙያ ነጻነት እየቀነሰ መጥቶ አሁን የደረሰበት ደርሷል።
"ብዙ ሰዎች በዋነኛነት በፖለቲካ አመለካከታቸው ተከሰው ሲከሰሱ ዘጋቢ በመሆን እየተመለከትኩ ብዙ ጊዜዬን አሳልፌያለሁ ሆኖም መጨረሻ ላይ በጣም ተችተዋል ይህም ወደ ፕሬሱ እየመጣ ነው።
"ስለራሴ እያወራሁ አይደለም ስለ ሩሲያውያን ጋዜጠኞች እየተናገርኩ እንጂ፣ ስለ ለገዛ ወገኖቻቸው በገለልተኝነትና በነጻነት ፣ እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ለመዘገብ የሚሞክሩ በጣም ጥቂት ቀርተዋል። በጣም ከባድ ጊዜ በእያንዳንዱ ቀን እና ሳምንቱ ያሳልፋሉ።
በየቀኑ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፖሊስ ፍተሻ ስለተደረገ ሰው ፣ ወደ በፍርድ ቤት ስለተወሰደ ሰው፣ ሀገሩን ጥሎ ስለሄደ ሰው ወሬ እንሰማለን። እንደዚህ ያለ ነገር በጭራሽ አይቼ አላውቅም ያም የሚያሳዝን ነው።
"አዎ ፣ እኔ ሀገሪቱን ለቅቄ እወጣለሁ እና ወደዚህ ተመልሼ ለመምጣት ባለመታደሌ በጣም አዝኛለሁ። አንድ ቀን ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ብዙ ሩሲያውያን ተስፋ እንደሌላቸው እንዲሰማቸው ያደርገኛል። እናም ሩሲያ ከ 30 ዓመታት በፊት ስመጣ እንደነበረችው አይደለችም በእርግጠኝነት ከ 20 ዓመታት በፊት ስዘግብ እንደነበረችው አይደለችም።"












