ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሲኤንኤን ያልተከተቡ ሰራተኞቹ ቢሮ በመሄዳቸው ከስራ አባረረ
የአሜሪካ የዜና አውታር ሲኤንኤን የኮቪድ-19 ክትባት ሳይከተቡ ቢሮ የገቡ ሶስት ሰራተኞቹን ማሰናበቱን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ኩባንያው አስገዳጅ የክትባቱን ህግ የጣሱ ሰራተኞቹን ሲያባርር የመጀመሪያው ኩባንያ ነው ተብሏል።
በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ኩባንያዎች ሰራተኞቻቻውን እንዲከተቡ የመጠየቅ ህጋዊ መሰረት አላቸው።
ፌስቡክን እና ጉግልን ጨምሮ በርካታ ትልልቅ ኩባንያዎች በሚቀጥሉት ወራቶች ውስጥ ቢሮቻቸው ሙሉ በሙሉ ሲከፈቱ ሠራተኞቻቸው ተከትበው መምጣት አለባቸው ብሏል።
የሲኤንኤን ኃላፊ ጄፍ ዙከር ሰራተኞቹ ከስራ መባረራቸውን የጠቀሱት ሐሙስ ዕለት በተላከ እና በበርካታ የአሜሪካ የመገናኛ ብዙኃን ባዩት የኩባንያ ማስታወሻ ውስጥ ነው።
በመስክ ላይ ሪፖርት ለሚያደርግ ወይም ከሌሎች ሰራተኞች ጋር አብሮ የሚሰራና እንዲሁም ወደ ቢሮ ለመግባት ማንኛውም ሰው ክትባት አስገዳጅ ነው ማለታቸውም በማስታወሻው ላይ ሰፍሯል።
የዋርነር ሜዲያ የዜና እና የስፖርት ሊቀመንበር ሚስተር ዙከር "እኔ ግልፅ ልሁን በዚህ ላይ ያለን የመቻቻል ፖሊሲ ዜሮ ነው" ብለዋል።
በግንቦት ወር የአሜሪካ መንግሥት አሠሪዎች ሰራተኞቸቻው ቢሮ የሚገቡ ከሆነ ኮቪድ -19 ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ አለባቸው።
ታላላቆቹ የአየር መንገዶች ዴልታ እና ዩናይትድ አየር መንገድ አዲስ ሠራተኞች የክትባት ማስረጃ እንዲያሳዩ እየጠየቁ ሲሆን የኢንቨስትመንት ባንክ ጎልድማን ሳክስ በበኩሉ ምንም እንኳን ሠራተኞቻቸውን እንዲከተቡ ባያስገድድም የክትባት ሁኔታቸውን እንዲያሳውቁ ይጠይቃል።
ፕሬዚዳንት ባይደን ሁለት ሚሊዮን የፌዴራል ሠራተኞች የክትባት ማረጋገጫ እንዲያሳዩ ወይም አስገዳጅ ምርመራ እና ጭምብል እንዲለብሱ አዘዋል።