የጆ ባይደን አስተዳደር በሶማሊያ የመጀመሪያውን የአየር ጥቃት ፈፀመ

የጦር አውሮፕላን

የፎቶው ባለመብት, NurPhoto

የምስሉ መግለጫ, የጦር አውሮፕላን (ከፋይል የተገኘ ፎቶ)
ታትሟል

አሜሪካ በሰሜን ሶማሊያ ጋልካዮ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአልሻባብ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች።

የአየር ጥቃቱ የደረሰው በትናንትናው ዕለት ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላም የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጿል።

አሜሪካ በአልሻባብ ጥቃት ለደረሰበት የሶማሊያ ጦር ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷን የመከላከያ ኃይሉ ቃለ አቀባይ ሲንዲ ኪንግ ተናግረዋል።

በዚህ አየር ጥቃት ያደረሰው የጉዳት ምዘና እየተከናወነ ቢሆንም የመጀመሪያ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግንም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) ጥቃቶችን ገድበዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ወቅት በሶማሊያ የአየር ጥቃቶች እንዲጨምሩ አድርገዋል።

ሆኖም ከስልጣን ሊለቁ ባሉበት ወቅት በሶማሊያ ተሰማርተው የነበሩት 700 ልዩ ኃይሎች እንዲወጡ አዘዋል።

አል-ሸባብ አብዛኛውን ደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሶማሊያን የሚቆጣጠር ሲሆን በተመድ በሚደገፈው መንግሥትም ላይ አዘውትሮ ጥቃቶችን ይፈፅማል።