ኔዘርላንድስ፣ እንግሊዝ እና ኦስትሪያ በዩሮ 2020፤ ብራዚል ደግሞ በኮፓ አሜሪካ ጉዟቸውን በድል ጀመሩ

የፎቶው ባለመብት, PA
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ታላላቅ አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድሮች መካሄድ ጀምረዋል።
በዚህም መሠረት ዩሮ 2020 በተለያዩ የአውሮፓ አገራት እንዲሁም ኮፓ አሜሪካ ብራዚል ውስጥ እየተካሄዱ ነው።
በአውሮፓ እግር ኳስ ውድድር እንግሊዝ የዩሮ 2020 ጉዞዋን በድል ጀምራለች።
በዌምብሌይ በተደረገው ጨዋታ እንግሊዝ በራሄም ስተርሊንግ ግብ ክሮኤሺያን ማሸነፍ ችላለች።
ስተርሊንግ በ57ኛው ደቂቃ አሸናፊ ያደረገቻቸውን ጎል ከካልቪን ፊሊፕስ የተቀበለውን ድንቅ ኳስ ተጠቅሞ አስቆጥሯል።
ሳውዝጌት ከአስቶን ቪላ ጃክ ግሪያሪሽ ጋር የመጫወት ፈተናውን ተቋቁሞ እንግሊዝ የበላይነታቸውን የሚጠበቅበትን ድል በማረጋገጡ ከስተርሊንግ አስደሳች አፈፃፀም ተሸልሟል።
ሦስቱ አናብስት በፊል ፎደን ጎል ቃደሚ ሊሆኑ የሚችሉበትን ዕድል የግቡ ብረት መልሶታል።
ግብ ጠባቂው ጆርዳን ፒክፎርድ ብዙም ያልተፈተነበት ጨዋታ ሆኖም ተጠናቋል። ሦስት ነጥብ ያገኘችው እንግሊዝ በመጪው አርብ ከስኮትላንድ ጋር ዌምብሌይ ላይ ትጫወታለች።
ኦስትሪያ በአውሮፓ ዋንጫ የመጀመሪያ ድሏን ሰሜን መቄዶንያ ላይ አስመዝግባለች።
ኦስትሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድሩ የተሳተፈፈችውን ሰሜን መቄዶንያን ያሸነፈችበትን ሦስት ጎሎች ማርኮ አርናውቶቪች፣ ማይክል ግሪጎርቲሽ እና ላይነር አስቆጥረዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ሰሜን መቄዶንያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል አንጋፋው አጥቂ ጎራን ፓንዴቭ አስቆጥሯል።
ሰሜን መቄዶንያን በቀጣይ ከዩክሬይን ጋር ስትጫወት ኦስትሪያ ደግሞ ኔዘርላንድስን ትገጥማለች።
በሌላኛው የምድብ ሦስት ጨዋታ ኔዘርላንድ ዩክሬንን 3 ለ 2 አሸንፋለች።
ጆርጂኒዮ ዋይናልደም እና ዉት ዌጎርስት ባስቆጠሯቸው ሁከት ጎሎች ኔዘርላንድስ 2 ለ 0 መምራት ችላለች።
ዩክሬን በተከታታይ በአንድሪ ያርሞሌንኮ እና ሮማን ያሬምቹክ ጎሎች ጨዋታው ሁለት አቻ ሆነ።
ዴንዝል ደምፍራይስ በ85ኛው ደቂቃ ከናታን አኬ የተሻገረለትን ኳስ በማስቆጠር ብርቱካናማዎቹ ሦስት ነጥብ ይዘው እንዲወጡ አስችሏል።
ምድቡን ኦስትሪያ በሦስት ነጥብ ስትመራ ኔዘርላንድስም በተመሳሳይ ነጥብ በአንድ የጎል ልዩነት ተበልጣ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ዩክሬን ሦስተኛ ስትሆን ሰሜን መቄዶንያ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የዩሮ 2020 ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ስኮትላንድ እና ቼክ ሪፐብሊክ ይጫወታሉ። ምሽት አንድ ሰዓት ፖላንድ ከስሎቫኪያ ሲገናኙ በምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ ስፔን እና ስዊዲን ምሽት አራት ሰዓት ይገጥማሉ።
በኮፓ አሜሪካ የመክፈቻ ጨዋታ ያለፈው ውድድር አሸናፊ እና አስተናጋጇ ብራዚል በኮቪድ-19 የተጎዳችውን ቬንዙዌላን በማሸነፍ ውድድሩን ጀመረች።ኮከቡ ኔይማር አንድ ጎል አስቆጥሮ ለሌላ ጎል መቆጠር ደግሞ ኳስ አመቻችቶ ሰጥቷል። ለቲቴ ቡድን ሁለተኛውን ጎል ከፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር ለጋብርኤል ባርቦሳ ጎል ኳስ አመቻችቶም ሰጥቷል።የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑ ተከላካይ ማርኪንሆስ በ23ኛው ደቂቃ የውድድሩን የመክፈቻ ጎል ከማዕዘን የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ አስቆጥሯል።ግጥሚያው ከመደረጉ ከአንድ ቀን በፊት ከቬንዙዌላ ተጫዋቾች እና ከአሰልጣኞች መካከል አስራ ሁለቱ ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል። በሌላ ኮፓ አሜሪካ ውድድር ኮሎምቢያ ኢኳዶርን 1 ለ 0 አሸንፋለች። 47ኛው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አንድ ዓመት ዘግይቷል። ኮሎምቢያ እና አርጀንቲና ውድድሩን ከተነጠቁ በኋላ ነው በብራዚል እየተካሄደ የሚገኘው።የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ኮንሜቦል) የፀረ-መንግሥት ተቃውሞን ተከትሎ በግንቦት ኮሎምቢያን ከአስተናጋጅነት ያሰናበተ ሲሆን፤ በአርጀንቲና የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ማሻቀብ ደግሞ ሌላ አስተናጋጅ አገር እንዲመረጥ አስገድዷል። ውድድሩ ዛሬም አርጀንቲና ከቺሊ እና ፓራጓይ ከቦሊቪያ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይቀጥላል።












