ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የሕፃናት ወሲባዊ ምስሎችን የሚያሰራጩ ሰዎች ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ታትሟል
ህፃናት ላይ የሚደረግ ወሲባዊ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምስሎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ጀመርን ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የህፃናትን ወሲባዊ ጥቃቶች የሚያጋራውና በዓለም ትልቅ እንደሆነ የተነገረለት ድረ ገፅን እንደሚዘውሩ የተጠረጠሩ ናቸው ግለሰቦቹ።
የጀርመን ፖሊስ 3 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ቀሪ አንድ ግለሰብ በፓራጓይ እየታደነ ይገኛል።
አሁን ላይ የታገደውና 'ቦይስታውን' የሚል መጠሪያ ያለው ድረገፅ ከ 400 ሺህ ተጠቃሚ እንዳለው ተነግሯል።
ይህ ድረ-ገፅ በኢንተርኔት በመደበኛ መንገድ ተፈልጎ በማይገኝ 'ዳርክ ኔት' በተሰኘ ድር አምባ የተካተተ ነው።
ድረ ገፁ በጣም ከባድ የሆነ የህፃናት ወሲባዊ ጥቃት ፎቶዎች እንደያዘም ተመላክቷል።
ጀርመን በመራችው በዚህ ምርመራ የኔዘርላንድስ፣ የስዊድን፣ አውስትራሊያ፣ የአሜሪካና የካናዳ የህግ ማስከበር ተቋማት ተሳትፈዋል።
የአውሮፓ ህብረት ፓሊስ ኤጀንሲ በምርመራው የተገኙ ውጤቶችን ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከል እንደሚጠቀምበት ገልፃል።
ከባለፈው ወር አጋማሽ ጀምሮ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጀርመን ፓሊስ ጠቁሟል።
ፖሊስ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በሀንቡርግ የተያዘው የ64 ዓመት ግለሰብ 3,500 ይዘቶችን 'ፓስት' አድርጓል ብሏል።