ካናዳዊው ፖለቲከኛ በዙም ስብሰባ ላይ እርቃናቸውን ታዩ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ካናዳዊው ፖለቲከኛ በአንድ የቪድዮ ስብሰባ ላይ እርቃናቸውን መታየታቸውን ተከትሎ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ፖለቲከኛው ዊሊያም አሞስ ከባልደረቦቻቸው ጋር በነበራቸው የዙም ስብሰባ ላይ እርቃናቸውን ብቅ ያሉት።
"ይህ ጭራሽ ይሆናል ብዬ ያላሰብኩት ነገር ነው" ብለዋል ፖለቲከኛው።
ዊሊያም አሞስ የኪውቤክ ግዛት የፖንቲያክ ክፍለ ግዛት ተወካይ ናቸው።
ሰውዬው ከባልደረቦቻቸው ጋር በነበራቸው የዙም ስብሰባ ላይ እርቃናቸውን ከታዩ በኋላ ረቡዕ ዕለት ኦፊሴላዊ የይቅርታ ደብዳቤ ለቀዋል።
"ትንሽ ሮጥ ብዬ ከተመለስኩ በኋላ የሥራ ልብስ ለመልበስ እየተሰናዳሁ ሳለ ነው ድንገት ቪድዮ የሚያሳየው ቁልፍ የተነካው" ብለዋል ፖለቲከኛው በይቅርታቸው።
ሰውዬው እርቃናቸው ሳሉ ከቪድዮ ላይ የተነሳው ምስል በማሕበራው ድር አምባዎች ላይ ሰዎች ሲጋሩት ነበር።
በዚህ ምስል ላይ ፖለቲከኛው አሞስ ሃፍረተ ስጋቸውን በሞባይል ስልካቸውን ሸፍነው ይታያሉ።
ሊበራሉ የካናዳ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል በኩውቤክና በካናዳ ባንዲራ መካከል ካል አንድ ጠረጴዛና ወንበር ጀርባ ቆመው ነበር።
ሰውዬው ሳያስቡት ድንገት በተፈጠረው ክስተት "እንዳፈሩ" እና እንዲሁም "ድጋሚ ፍፁም እንደማይከሰት" በመግለጫቸው ፅፈዋል።
በትዊተር ገፃቸው ጭምር ይቅርታቸውን ያጋሩት ፖለቲከኛው ይህ "ሳላስበው የሆነ ነው" የሚለውን አስምረውበታል።
ከዚህ ክስተት በኋላ አንድ ሌላ ፖለቲከኛ በተለይ ወንድ ፖለቲከኞው ስብሰባ ላይ ሲቀርቡ ጃኬትና ክራባት እንዲያደርጉ ቢገደዱ መልካም ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
"ፖለቲከኞች ካሜራቸውን ሲያበሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቢነገራቸው መልካም ነው" ብለዋል ፖለቲከኛዋ።












