የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ድምፅ መስጠት ተጀመረ

ኦማር ጌሌ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ለአምስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩበት ምርጫ ዛሬ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል፡፡

ከአረብ ሊግ የተወከሉ የምርጫው ታዛቢ ሁሉም ነገር በሰላም እየተካሄደ ነው ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ ከ 200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ጉሌህ ለ 22 አመታት አገሪቷን አስተዳድረዋል፡፡ የበቢሲው ዘጋቢ መሃመድ አብዲራሂም እንዳለው ዋና ዋና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫው የማስመሰል ምርጫ ነው በሚል ጥለው ወጥተዋል፡፡

ብቸኛ ተፎካካሪያቸው ዘካሪያ ኢስማኤል እምብዛም የማይታወቁ ነጋዴ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሰራወት ውስጥ አባልም ነበሩ፡

ተፎካካሪያቸው የፅዳት እቃዎችን ከውጪ አገራት የሚያስገቡ ሲሆን ባለፈው ጥር ለምርጫ እንደሚወዳደሩ ይፋ እስከሚያደርጉ ድረስ በሕዝቡ ዘንድ የሚያውቃቸው አልነበረም፡፡

የ 57 አመት ጎልማሳው ለጉሌህ ስጋት እንደማይሀኑ እና ፕሬዘዳንት ጉሌህ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡

በስትራቴጂያዊ አቀማመጧ ለቀጠናው ቁልፍ ከሚባሉ አገራት መካከል የሆነችው ትንሿ አገር ጂቡቲ ከአንድ ሚሊዮን የሚያንስ ህዝብ ያላት ሲሆን አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ የሃያላን አገራት የወታደራዊ መቀመጫ መሆኗ ይታወቃል፡፡