የአልሻባብ አባል ነው የተባለ የኮሌጅ መምህር በሞት ተቀጣ

ታትሟል

በሶማሊያ አንድ የኮሌጅ መምህርና ሁለት ሌሎች ግለሰቦች በሞት ተቀጥተዋል።

ግለሰቦቹ በመንግሥት በታዘዙ የተኳሾች ቡድን ነው በጥይት ተተኩሶባቸው የተገደሉት።

መንግሥት ግለሰቦቹ የእስላማዊው ታጣቂ ቡድን አልሻባብ አባልና በርካታ ግድያዎችን ፈፅመዋል በማለትም ወንጅሏቸዋል።

የሞት ፍርድም የተፈረደባቸው በሞቃዲሾ በሚገኝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ነው።

ሞሃመድ ሃጂ አህመድ በሞቃዲሾ በሚገኝ አንድ ኮሌጅ ውስጥ ታዋቂ የእንግሊዝኛ መምህር ነው።

ከመምህርነቱ በተጨማሪ በአልሻባብ ውስጥ ኢካኬዝ (ሬድ ቲዝ) ተብለው የሚታወቁ ገዳዮች ውስጥ አንዱ ነው ተብሏል።

በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናትንም በመግደል እጁ እንዳለበትም ተዘግቧል።

"ምህረት የሌለው ነፍሰ ገዳይ" በሚል የተጠራው ይህ መምህር በሞቃዲሾና በቤናዲር ግዛት ውስጥ ያለ የገዳዮች ቡድንንም ይመራ እንደነበር ተገልጿል።

ከሁለቱ ግለሰቦችም ጋር እሁድ እለት ህዳር 20፣ 2013 ዓ.ም ነው በመንግሥት ተኳሾች ቡድን በጥይት ተደብድቦ የተገደለው።

የ27 አመቱ መምህር በተለያዩ የቅፅል ስሞች የሚታወቅ ሲሆን በጎሮጎሳውያኑ 2017 የተገደሉትን ጄኔራል አብዱላሂ መሃመድ ሼክን በመግደል ጥፋተኛ ሆኖ አግኘቸዋለሁ ፍርድ ቤቱ።

የሶማሊያው ፍርድ ቤት በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሆኑትን ሞሃመድ አብዲራህማን መሃመድን እንዲሁም የፖሊስ ኃላፊ መሃመድ ሃጂ አሎው በባለፈው አመት በመግደል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው የወታደራዊው ፍርድ ቤት በሞት የተቀጣው።