ባገባደድነው ሳምንት በዓለም ዙርያ በዜና አገልግሎቶች ከተነሱ ፎቶግራፎች ምርጥ 10ሩ

ሎይድ ስኮት

የፎቶው ባለመብት, Joe Giddens / PA Wire

የምስሉ መግለጫ, ሎይድ ስኮት የቀድሞ የእንግሊዝ እግርኳስ ግብ ጠባቂ ነበር፡፡ አሁን እድሜው ገፍቶ በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ነው፡፡ ይህን ተራራ መውጣቱም ለዚሁ ነው፡፡ የባህር ጠላቂ ደንብ ልብስ ለብሶ በዩኬ ረዥሙን ተራራ እየወጣ ይታያል፡፡ በ2002 በሎንዶን ማራቶን ይህንኑ ልብስ ለብሶ በዓለም እጅግ ዘገምተኛውን የኦሎምፒክ ሰዓት አስመዝግቦ ነበር፡፡
ታትሟል

ባገባደድነው ሳምንት በዓለም ዙርያ በዜና አገልግሎቶች ከተነሱ ፎቶገራፎች ምርጥ ዓሥር ፎቶዎችን እናስቃኛችሁ። ከስብስቦቹ መካከል የአየር ንብረት ለውጥ ተቃውሞ፣ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ ይገኙበታል።

በሱባንግ ጃያ፣ ማሌዢያ፤ አንድ ሐኪም የኮቪድ ቅንጣት ምርመራ ለማድረግ የበሽተኛውም መምጣት እየጠበቀ፡፡

የፎቶው ባለመብት, Lim Huey Teng / Reuters

የምስሉ መግለጫ, በሱባንግ ጃያ፣ ማሌዢያ፤ አንድ ሐኪም የኮቪድ ቅንጣት ምርመራ ለማድረግ የበሽተኛውም መምጣት እየጠበቀ፡፡
ኔዘርላንድስ፣ ሳሰኔም ውስጥ ከቤት ሆና በመሥራት ላይ የነበረች ሴት የገዛ ድምቷ "ፍቅር አነሰኝ" እያለቻት ይመስላል፡፡

የፎቶው ባለመብት, Eva Plevier / Reuters

የምስሉ መግለጫ, ኔዘርላንድስ፣ ሳሰኔም ውስጥ ከቤት ሆና በመሥራት ላይ የነበረች ሴት የገዛ ድምቷ "ፍቅር አነሰኝ" እያለቻት ይመስላል፡፡
በጀርመን መዲና በርሊን የአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪ በአደባባይ ተቃውሞ ላይ

የፎቶው ባለመብት, Michele Tantussi / Reuters

የምስሉ መግለጫ, በጀርመን መዲና በርሊን የአየር ንብረት ለውጥ ተቆርቋሪ በአደባባይ ተቃውሞ ላይ
በአማን፤ ጆርዳን በኮሮና ምክንያት ተማሪዎች ባለመምጣታቸው መምህርት የርቀት ትምህርት በመስጠት ላይ

የፎቶው ባለመብት, Muhammad Hamed / Reuters

የምስሉ መግለጫ, በአማን፤ ጆርዳን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተማሪዎች ባለመምጣታቸው መምህርት የርቀት ትምህርት በመስጠት ላይ
ትራምፕ ከኮሮና ምልክቶች ተፈውሻለሁ ብለው ገና ከሆስፒታል ዋይትሐውስ እንደደረሱ ትሩማን ባልኮኒ ላይ ሆነው ጭምብላቸውን ወዲያ ሲያደርጉ (ቦታ ዋሺንግተን ዲሲ፣ አሜሪካ)

የፎቶው ባለመብት, Erin Scott

የምስሉ መግለጫ, ትራምፕ ከኮሮና ምልክቶች ተፈውሻለሁ ብለው ገና ከሆስፒታል ዋይትሐውስ እንደደረሱ ትሩማን ባልኮኒ ላይ ሆነው ጭምብላቸውን ወዲያ ሲያደርጉ (ቦታ ዋሺንግተን ዲሲ፣ አሜሪካ)
ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስና ሴናተር ካመላ ሐሪስ የ90 ደቂቃ ክርክር ለማድረግ ሲሰናዱ (ቦታ፣ ሶልትሌክ፣ ዩታ፣ አሜሪካ)

የፎቶው ባለመብት, Jim Lo Scalzo / EPA-EFE

የምስሉ መግለጫ, ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስና ሴናተር ካመላ ሐሪስ የ90 ደቂቃ ክርክር ለማድረግ ሲሰናዱ (ቦታ፣ ሶልትሌክ፣ ዩታ፣ አሜሪካ)
ለተቃውሞ የወጡ ወጣቶች አንዲት የዕድሜ ባለጸጋን ከፖሊሶች ጥቃት በመከላከል ላይ ሳሉ (ቦታ፣ ጃካርታ ኢንዶኒዚያ)

የፎቶው ባለመብት, Willy Kurniawan / Reuters

የምስሉ መግለጫ, ለተቃውሞ የወጡ ወጣቶች አንዲት የዕድሜ ባለጸጋን ከፖሊሶች ጥቃት በመከላከል ላይ ሳሉ (ቦታ፣ ጃካርታ ኢንዶኒዚያ)
የብርቱካን ፍሬ በማሽን በመሰብሰብ ላይ ሳለ፡፡ ገበሬዎቹ የብርቱካን ለቃሚ ሰራተኛ እጥረት ገጥሟቸዋል፡፡ (ነው ሳውዝ ዌልስ፣ አውስትራሊያ)

የፎቶው ባለመብት, Lukas Cochairs / EPA-EFE

የምስሉ መግለጫ, የብርቱካን ፍሬ በማሽን በመሰብሰብ ላይ ሳለ፡፡ ገበሬዎቹ የብርቱካን ለቃሚ ሰራተኛ እጥረት ገጥሟቸዋል፡፡ (ነው ሳውዝ ዌልስ፣ አውስትራሊያ)
ሎንዶን ማራቶን በወረርሽኙ ምክንያት መደበኛ (ተራ) ተሳታፊዎች አልተገኙበትም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ባሉበት ሆነው ስልክ ላይ በሚጫን የሩጫ መተግበርያ ውድድሩን ተሳትፈዋል፡፡ ኮሊን በርጊን ፕሊውስ በቅጽል ስሙ ‹ቢግ ፒንክ ድሬስ› ሎንዶን ማራቶንን ለበጎ አድራጎት ማሳባሰብያ ካለበት ቦታ ለ5ኛ ጊዜ ሲካፈል፡፡ (ቦታ ሰሜን ምሥራቅ ኢንግላንድ)

የፎቶው ባለመብት, Owen Humphreys/PA Wire

የምስሉ መግለጫ, ሎንዶን ማራቶን በወረርሽኙ ምክንያት መደበኛ (ተራ) ተሳታፊዎች አልተገኙበትም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ባሉበት ሆነው ስልክ ላይ በሚጫን የሩጫ መተግበርያ ውድድሩን ተሳትፈዋል፡፡ ኮሊን በርጊን ፕሊውስ በቅጽል ስሙ ‹ቢግ ፒንክ ድሬስ› ሎንዶን ማራቶንን ለበጎ አድራጎት ማሳባሰብያ ካለበት ቦታ ለ5ኛ ጊዜ ሲካፈል፡፡ (ቦታ ሰሜን ምሥራቅ ኢንግላንድ)