የቢቢሲው ፎከስ ኦን አፍሪካ 60 ዓመት ሞላው
የፎከስ ድምጾችን ያዛምዱ
ፎከስ ኦን አፍሪካ 60 ዓመት ሆነው! ይህንንም ለማክበር ከፕሮግራሙ አቅራቢዎች መካከል የተወሰኑትን እናስተዋውቃችሁ።
ትክክል ነዎት
ጥሩ ሙከራ። ትክክለኛው መልስ፡
ቢልኪሱ ላባራን የፎከስ ኦን አፍሪካ አርታዒ ነች። ናይጄሪያዊቷ ጋዜጠኛ ለፎከስ ኦን አፍሪካ ለበርካታ ዓመታት ዘግባለች። "እአአ 2010 ላይ የወቅቱን የጋና ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጆን አታ ሚልስ ቃለ መጠይቅ ላደርግ ስል፤ የፕሬስ ቡድናቸው ስለ ፕሬዝደንቱ ጤና ጥያቄ እንዳላነሳ አስጠንቅቀውኝ ነበር። እኔ ስለ ጤናቸው አልጠየኩም። ይሁን አንጂ በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ላይ እንመለከታቸው የነበሩት ፕሬዝደንት ለምን እራሳቸውን ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዳገለሉ ጠይቂያቸው ነበር። ከፕሬስ ቡድናቸው የተሰጠው ምላሽ ግን መነጋገሪያ ሆኖ ነበር"
ካትሪን ፌሎውስ በተለይ በዶክመንታሪ እና በጥበብ ሥራዎች ላይ በማተኮር በቢቢሲ አፍሪካ ላይ ለብዙ ዓመታት ሰርታለች። አሁን በዲጄ ኢዱ ለሚቀርበውና "ዚስ ኢዝ አፍሪካ" ለተሰኘው ፕሮግራም አርታኢ ነች።
ቦላ ሞሱሮ የፎከስ ቤተሰብን የተቀላቀለችው በ1992 [እ.አ.አ] ሲሆን አሁን ዋና አቅራቢ ነች። በድጋሚ ቃለ መጠይቅ የማድረግ እድሉ ቢሰጠኝ፤ ቃለ መጠይቅ ላደርግ የምችለው ለከፌላ [ኩቲ] ነው። በ90ዎቹ ዩናይትድ ኪንግደምን ጎብኝቶ ከበርሚንግሃም ኮንሰርት በኋላ ለመገናኘት ተስማማ። ለእርሱ ትልቅ አድናቆት ነበረኝ። እንደተለመደው ያጨስ ነበር እናም በሌላ እውነት ውስጥ ነበር። በመሆኑም በውስጤ የነበረችው ታዳጊዋ የሴቶች መብት ተከራካሪ የዚያን ሌሊት ይጠቀማቸው የነበሩ ቃላትን ለማስተካከል ጥረት ታደርግ ነበር። በመሆኑም ብዙ ሳናወራ ተለያየን። ጊዜን መመለስ ብችል እንደ "ሻፈሪንግ እና ሽማይሊንግ" ዓይነት ብዙ አዝናኝ ነገሮችን መስማት እፈልግ ነበር።
ትክክል ነዎት
ጥሩ ሙከራ። ትክክለኛው መልስ፡
ግራኟ ኦውድሬይ ብሮውን ደቡብ አፍሪካዊት ነች። ሪፖርተር ሆና ከሰራች በኋላ ከ2005 ጀምሮ አቅራቢ ነች። "በኡጋንዳ ያላገቡና ልጅ ስለሌላቸው ሴቶች መብት ቅስቀሳ ስታደርግ የነበረችን ሴት ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር። የነበረኝ ትንሽ ዝግጅት "ባል የሌላቸውን ሴቶች ከወንዶች ጋር የምታገናኘው ሴት አብራን ትገኛለች" የሚል የተሳሳተ መግቢያ ጽፌ ነበር፤ በቀጥታ ስርጭት ላይ በትህትና ታርሜያለሁ።
ኑር አቢዳ የብሮድካስት ጋዜጠኛ ነች። የፎከስ ራዲዮ ፕሮግራም እና "አፍሪካ ቱዴይ"ን ታዘጋጃለች።
ኪም ቻካኔሳ ዚምባብዌያዊ ጋዜጠኛ ስትሆን ፎከስ አፍሪካን የተቀላቀለችው በ2013 ነው። ኪም በአሁኑ ወቅት "ዘ ኮምብ" የተሰኘ ፖድካስት ታቀርባለች።
ትክክል ነዎት
ጥሩ ሙከራ። ትክክለኛው መልስ፡
ቬሮኒክ ኤድዋርድ ልምድ ያላት አዘጋጅ ስትሆን በአዝናኝ አቀራረቧ፣ በአስቂኝ ቃለ መጠይቆቿ እና የበርካታ የአፍሪካ መሪዎችን የስልክ አድራሻ በመያዝ ትታወቃለች። ምግብ ማብሰል፣ ማዝናናት፣ አትክልት መንከባከብና የአፍሪከ ፋሽንን መከተል ትወዳለች።
ኒሻት ላድሃ ለብዙ ዓመታት "ስፖርትስዎርልድ" ስታቀርብ ከቆየች በኋላ አሁን "ፎከስ ስፖርት"ን ታቀርባለች። እንደ ስፖርት አፍቃሪ፤ አፍሪካውያን የስፖርት ከዋክብት የተጓዙበትን የስኬት መንገድ መስማት ያስደስታታል። በጣም የምትወደው ቃለ መጠይቅ በቅርቡ ከካሜሩናዊቷ የሁለት ጊዜ ኦሊምፒክ አሸናፊ ፍራንሷ ምባንጎ ጋር ያደረገችው ቆይታ ነው። "እንደ እናት ከወሊድ ተመልሳ የ2008 የቤጂንግ ኦሊምፒክን ዘውድ መጫኗን መስማት ያስደንቃል። የማይታመን ነው! "
ሂወቴ ኃይለሥላሴ የፎከስን ቡድን የተቀላቀለችው ፍሪላንስ አዘጋጅ ሆና እአአ 2008 ነበር። በአሁኑ ወቅት ለቡድኑ ዕቅድ በማዘጋጀት እየሰራች ትገኛለች።
ትክክል ነዎት
ጥሩ ሙከራ። ትክክለኛው መልስ፡
ስታንሌይ ክዌንዳ ዝምባብዌያዊ ጋዜጠኛ ነው። የፎከስ አዘጋጅ ሲሆን በቅርቡም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ለቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል።
በፎከስ ዝግጅት የፖል ባቺቢንጋ ድምጽ በመላው አፍሪካ መሰማት የጀመረው ከ2004 ጀምሮ ነው። በየሳምንቱ የሚወጡ ፕሮግራሞችንም አርትኦት የሚሰራው እርሱ ነው።
ቪክተር ሲልቨር ሪፖርተርነትን የጀመረው በ1991 ሴራ ሊዮን ሳለ ነበር። በ1997 ከአገሩ ወጥቶ አሁን በፎከስ አዘጋጅነት እየሰራ ነው።
ትክክል ነዎት
ጥሩ ሙከራ። ትክክለኛው መልስ፡
ዴቪድ አማኖር በተለያዩ ጊዜያት ከ2012 ጀምሮ የፎከስ አቅራቢ ሆኖ ሰርቷል። "የእኔ ምርጥ ቃለ መጠይቆች ከተራው ማኅበረሰብ ጋር የማደርጋቸው ይመስሉኛል፤ ለምሳሌ በ2019 የማላዊ ምርጫ ራሷን ዋይኒ ሩኒ ብላ ከምትጠራው እግር ኳስ ተጫዋች ሉኒ ጋር ያደረግሁት ቃለ መጠይቅ፣ በ2015 በአይቮሪኮስት ምርጫ ያናገርኳት ገበያተኛ ሴት፣ በ2014 ኬንያ አውቶብስ ውስጥ ያናገርኳት ሴት፣ በጣም የምወደው ደግሞ በ2008 የአፍሪካ ዋንጫ ሰዎች ታኮራዲ ወደብን ሲያቋርጡ ያናገርኩበት ቅጽበት ናቸው።"
ክሪስ ቢከርተን ከ1970 ጀምሮ ለ30 ዓመታት ፎከስ ኦን አፍሪካ ላይ በመስራቱ የአፍሪካ ድምጽ በመባል ይታወቃል። በፎከስ አድማጮች አሁንም ድረስ በጣም ተወዳጅ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ 2002 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ፒርስ ሊንች ፎከስ ኦን አፍሪካን የተቀላቀለው ከ2 ዓመት በፊት ነው። አሁን የ 'ዘ ኮምብ' እና 'አፍሪካ ቱዴይ' ፕሮግራሞች አርታኢ ነው።
ትክክል ነዎት
ጥሩ ሙከራ። ትክክለኛው መልስ፡
አሊስ ሙቴንጊ በሪፖርተርነት፣ በዶክመንታሪ አዘጋጅነትና በአዘጋጅነት ለብዙ ዓመታት ለቢቢሲ አፍሪካ የሰራች ኬንያዊት ጋዜጠኛ ነች።
ኢሳው ዊሊያምስ የቢቢሲ አፍሪካ ጋዜጠኛ ሲሆን የፎከስም አቅራቢ ነው። ቼዝ እና ክላሲካል ሙዚቃ ያዝናናዋል።
ሃሰን አሩኒ ለፎከስ ኦን አፍሪካ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አቅራቢ ነበር። "ባለፈው ዓመት ከናይጀሪያዊው ሙዚቀኛ ዲ'ባንጂ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጌያለሁ። በመጨረሻም ሁለታችንም በደመነፍስ በእንጉርጉሮ ጭልጥ አልን። የተጠያቂው ልብ ውስጥ ለመግባት ያስቻለኝ የቃለ መጠይቅ ተደራጊው ቴክኒክ ነበር ብዬ አስባለሁ። "
አዘጋጆች-ፔኒ ዴል፣ ፒዩሪቲ ቢሪር፣ ዲዛይነር- ሚሊ ዋቺራ፣ አስተባባሪ ሙቶኒ ሙቺሪ








