እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠንክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የአገራቸው ሠራዊት በጦርነቱ የሚያካሂደው ዘመቻ ያለበት ደረጃ “መቀየሩን” በመግለጽ፣ “ተጨማሪ መረጃ አስኪሰጥ ድረስ” ዘመቻው ይቀጥላል ብለዋል። አርብ ምሽት ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ “የጋዛ ምድር ተንቀጥቅጣለች” በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ ለአንድ ቴሌዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

የቀጥታ ሽፋን

  1. በምስል፡ የጋዛ ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ለማዳን እየሞከሩ ነው

    የጋዛዋ ዃን ዩኒስ ከተማ በእስራኤል ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት ደርሶባታል

    የፎቶው ባለመብት, Anadolu via Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, የጋዛዋ ዃን ዩኒስ ከተማ በእስራኤል ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት ደርሶባታል

    የጋዛ ነዋሪዎች በእስራኤል የአየር ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ሕይወት ለማትረፍ እየሞከሩ ነው።

    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ ተጨማሪ ነዳጅ ካላገኘ የእርዳታ ሥራው እንደሚቋረጥ አስታውቋል።

    አንድ የእስራኤል ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሐማስ ነዳጅ እያከማቸ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

    ነዋሪዎች እና የእርዳታ ሠራተኞች ከፈረሰ ህንጻ ስራ ጉዳት የደረሰባቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ነው

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, ነዋሪዎች እና የእርዳታ ሠራተኞች ከፈረሰ ህንጻ ስራ ጉዳት የደረሰባቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ነው
    ህይወታቸው ያለፉት የቀበር ስነ ስርዓትም በመከናወን ላይ ይገኛል

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, ሕይወታቸው ያለፉት የቀበር ስነ ስርዓትም በመከናወን ላይ ይገኛል
    እስራኤል፣ ጋዛን በከበባ ውስጥ ካስገባች ሁለት ሳምንታት አለፉ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, እስራኤል ጋዛን በከበባ ውስጥ ካስገባች ሁለት ሳምንታት አለፉ
  2. አሜሪካ እስራኤልን ለመከላከል ምን ልታደርግ ትችላለች?

  3. የሶሪያ ወታደራዊ ኢላማዋችን ማጥቃቷን እስራኤል አስታወቀች

    ረቡዕ ማለዳ ላይ የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች የሶሪያ ጦር ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን እና የሞርታር ማስወንጨፊያዎችን ማጥቃታቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።

    እርምጃው ማክሰኞ እስራኤል ላይ ለተሰነዘረው ጥቃት ምላሽ ነው ሲልም ጦሩ አክሏል።

    በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች ይፋ አልተደረጉም።

  4. እስራኤል በጄኒን የድሮን ጥቃት ሰነዘረች

    እሑድ በተካሄደ የእስራኤል የአየር ጥቃት ጄኒን ውስጥ ሁለት ወጣቶች ተገድለዋል

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    የምስሉ መግለጫ, እሑድ በተካሄደ የእስራኤል የአየር ጥቃት ጄኒን ውስጥ ሁለት ወጣቶች ተገድለዋል

    የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት “ከአጭር ጊዜ በፊት” በዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ አቅራቢያ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተፈጠረ ግጭት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙን በማህበራዊ ሚዲያ አስታወቀ።

    በጄኒን ሰዎች "ከታጠቁ አሸባሪዎች" ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለት ተይዘዋል ሲል አክሏል።

    ግጭቱ የተቀሰቀሰው እስራኤል በጄኒን የስደተኞች ካምፕ አካባቢ ጥበቃ እያደረገች ባለችበት ወቅት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው በእስራኤል ወታደሮች ላይ ቦንቦችን ከወረወሩ በኋላ መሆኑን ቴል አቪቭ አስታውቃለች።

    እስራኤል በመግለጫዋ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቱ እና በተኩስ ልውውጡ የደረሰው ጉዳት ተለይቷል ብላለች።

    የእስራኤል ወታደሮች ላይ ጉዳት አለመድረሱም ታውቋል።

    እስራኤል “የአሸባሪዎች ግቢ” ባለችውና በጄኒን በሚገኘ መስጊድ ላይ እሑድ ዕለት የአየር ጥቃት ሰነዘራ ነበር።

  5. የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች

    Ambo Gilad

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሥልጣናቸውን በፍቃዳቸው እንዲለቁ እስራኤል ጠየቀች።

    በድርጀቱ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን ዋና ፀሐፊው "ሐማስ ጥቃቱን የከፈተው ያለ ምክንያት አይደለም" ማለታቸውን ተከትሎ ነው ጉቴሬዝ ሥልጣን እንዲለቁ የጠየቁት።

    አምባሳደሩ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ቡድን በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጥቃት ትክክለኛነት ለማሳየት ከሚጥሩት ጋር ምንም አይነት ንግግር ማድረግ አያስፈልግም ብለዋል።

    ዛሬ [ማክሰኞ] በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ጉቴሬዝ “የፍልስጤም ሕዝብ ለ56 ዓመታት በአፋኝ በሆነ ግዞት ውስጥ ቆይቷል። መሬታቸው በፍጥነት በሰፈራ ሲከፋፈል እና በአመጽ ሲታመስ ተመልክተዋል። ምጣኔ ሃብታቸው ደቋል። ሕዝባቸው ተፈናቅሎ ቤታቸው ፈርሷል። ለስቃያቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ ይገኛል በሚል የነበራቸው ተስፋ መሻታቸው ምላሽ አላገኝም” ሲሉ ተናግረዋል።

    antonio

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በዚህ የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ንግግር ደስተኛ ያልሆኑት የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ ዋና ፀሐፊው ጉቴሬዝ በአስቸኳይ ከመንግሥታቱ ድርጅት ሥልጣናቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል።

    አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚህ ንግግራቸው ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ሳያወግዙ አላለፉም።

    “የፍልስጥኤማውያን ሕመም ሐማስ ላደረሰው አሰቃቂ ጥቃት ምክያት ሊሆን አይችልም፤ እንዲሁም ይህም ጥቃት በፍልስጥኤም ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን የጅምላ ቅጣትን ትክክል አያደርገውመ” ብለዋል።

  6. የተባበሩት መንግሥታት በነዳጅ ችግር ምክንያት ጋዛ ውስጥ ሥራ ሊያቆም ነው

    በጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, በጋዛ እንደ ጤና ተቋማት ያሉ መሠረተ ልማቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።

    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የነዳጅ አቅርቦት ካላገኘ በጋዛ ውስጥ የሚያከናውነውን የሰብአዊ እርዳታ ተግባር ከነገ ረቡዕ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ገለጸ።

    በፍልስጥኤም ውስጥ የስደተኞች ጉዳይን የሚከታተለው የድርጅቱ ተቋም ዛሬ ማክሰኞ እንዳስጠነቀቀው በሰብአዊ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ጋዛ ሰርጥ ውስጥ ሥራውን ለማቆም ከጫፍ ደርሷል።

    የድርጅቱ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ሬዲዮ 4 እንደተናገሩት “በአስቸኳይ ነዳጅ ማግኘት ካልቻልን፣ ከነገ ረቡዕ ምሽት ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የምናካሂደውን ሥራ እንቆማለን” ብለዋል።

  7. ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶችን በመሸሽ የሊባኖስ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ

    የወደመ ታንክ

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    መቀመጫውን ሊባኖስ ባደረገው ሒዝቦላህ እና በእስራኤል መካከል የሚደረገው ግጭት መባባሱን ተከትሎ ድንበር ላይ ያሉ የሊባኖስ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል ጀመሩ።

    የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደሚለው ከሁለት ሳምንታት ገደማ በፊት በሐማስ እና በእስራኤል መካከል ግጭት ከተከሰተ ወዲህ ወደ 20ሺህ የሚጠጉ የሊባኖስ ዜጎች ከደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ተፈናቅለዋል።

    ድንበር ላይ የሚገኙ የሊባኖስ መንደሮች፣ መደብሮች እና መንገዶች ጭር ብለው ታይተዋል።

    ታይሬ በምትባለው ከተማ መሄጃ የሌላቸው ነዋሪዎች ወደ መጠለያነት በተቀየሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።

    ስለ ሒዝቦላህ ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ፡ ሊባኖስ የሚገኘው የእስራኤል ጠላት ሒዝቦላህ ማን ነው?

  8. እስራኤል ታጋቾች ያሉበትን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀት በተነች

    እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት
    የምስሉ መግለጫ, እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት

    እስራኤል በሐማስ የታገቱ ሰዎች መገኛን ለጠቆመ ወሮታ እከፍላለሁ ስትል በራሪ ወረቀቶችን በጋዛ ላይ በተነች።

    የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ በበተነው በራሪ ወረቀት፣ ታጋቾች የሚገኙበትን ትክክለኛ መረጃ ለጠቆመ ወሮታ እና የደኅንነት ጥበቃ እሰጣለሁ ብላለች።

    “ፍላጎትዎ በሰላም መኖር እና ለልጅዎ የተሻለ ሕይወትን የሚመኙ ከሆነ ሰብዓዊነት ያለው ተግባር በመፈጸም በአካባቢዎ የታገቱ ሰዎች ያሉበትን ቦታ ይጠቁሙ” ይላል እስራኤል በአረብኛ ቋንቋ የበተነችው በራሪ ወረቀት።

    እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ በበተነችው ወረቀት ጥቆማ የሚሰጡ ሰዎች ማንነትን በምሥጢር እንደምትይዝ እና የገንዘብ ሽልማትም እንደምትሰጥ ቃል ገብታለች።

    እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, እስራኤል የበተነችው በራሪ ወረቀት በአንዳንዶች በተቃውሞ ተቀዶ ተጥሏል።

    እስራኤል ይህን ትበል እንጂ የሰሜናዊ ጋዛ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶቹን እየቀደዱ ሲበትኑ መመልከቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

    አቡ ራማዳን የተባለ ሰው በራሪ ወረቀቱን ቀዶ በመበተን፤ “. . . የፈለጋችሁትን አድርጉ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በጋዛ ያለን ሰዎች አንንበረከክም። ከፈለጋችሁ በቦምብ ደብድቡን። ሕይወታችንን እና መኖሪያችንን ጥለን አንሰደድም” ሲል ከበውት የነበሩት ሰዎች በጭብጨባ ድጋፋቸውን ገልጸውለታል ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።

  9. ሐማስ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ700 በላይ ሰዎች ተገድለዋል አለ

    በጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, በጋዛ በእስራኤል አየር ጥቃት የወደመ ነዳጅ ማደያ

    በሐማስ የሚተዳደረው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ከ700 ያላነሱ ሰዎች ጋዛ ውስጥ ተገድለዋል አለ።

    የጤና ሚኒስቴሩ የሐማስ እና የእስራኤል ግጭት ከጀመረ ወዲህ የሟቾች ቁጥር ወደ 5 ሺህ 791 ደርሷል።

    ከ700 ያላሱት ሰዎች ባለፉት 24 ሰዓታት የመገደላቸው ዜና የተሰማው የእስራኤል ጦር ትናንት ከ400 ያላነሱ ዒላማዎችን ጋዛ ውስጥ በአየር መደብደቡን ካሳወቀ በኋላ ነው።

    የእስራል ጦር የዒላማ ያደረኩት ሐማስ የሚጠቀምባቸውን መሠረተ ልማቶችን ነው ይላል።

  10. "በቁርዓን እናምናለን፤ አንጎዳችሁም" በሐማስ ታግተው ከተለቀቁት

    ጋዛ ውስጥ ታግተው ከነበሩት አንዷ ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ አጋቾቻቸው

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    ጋዛ ውስጥ ታግተው ከነበሩት አንዷ ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ አጋቾቻቸው "በቁርዓን እናምናለን" አንጎዳችሁም እንዳሏቸው ተናገሩ።

    በትናንትናው ምሽት የተለቀቁት የ85 ዓመቷ የዕድሜ ባለጸጋ በሞተር ሳይክል በማይመች ሁኔታም እንደተወሰዱና መተንፈስም ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል።

    በሐማስ ታጋቾች ሲወሰዱም ጌጣጌጦች እና ሰዓታቸው እንደተወሰደባቸው እንዲሁም መመታታቸውንም የገለጹት የዕድሜ ባለጸጋዋ “ሲዖል ውስጥ ነበርኩ” ብለዋል።

    ከሞተር ብስክሌቱ ከወረዱ በኋላ ሰላምታ የሰጧቸው ሰዎች " በቁርዓን እናምናለን" ሲሉም ጉዳት እንደማያደርሱባቸው ነግረውኛል ብለዋል።

    እሳቸው እና ሌሎች 24 ሰዎች ወደ ዋሻዎች መወሰዳቸውን በአስተርጓሚ ልጃቸው በኩል ተናግረዋል።

    የዋሻዎቹ መተላለፊያዎች "እርጥበት የተሞላበት መሬት" መሆኑን መግለጻቸውንም ነው ልጃቸው የተናገረችው።

    ከሁለት ወይም ከሶስት ሰዓታት ገደማ በኋላ ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ አካባቢ የመጡ አምስት ሰዎችን ወደተለየ ክፍል ወሰዷቸው ብለዋል።

    በስፍራው ጠባቂዎች፣ የድንገተኛ አደጋ የጤና ባለሙያ እንዲሁም ዶክተር መኖራቸውንም ገልጸዋል።

    እሳቸው እና ሌሎች ታጋቾች ንጽህናው በተጠበቀ መልኩ መያዛቸውንም አስረድተዋል።

    በዋሻዎች ውስጥ እያሉም ነጭ አይብ እና ኩከምበር እንዲመገቡ ይሰጣቸው እንደነበርም ነው በዚህ ወቅት ያስረዱት።

    የሐማስ ታጣቂዎችም እየተመገቡት የነበረው ተመሳሳይ ምግብም እንደነበርም ገልጸዋል። በጋዛ ስር ባሉ ዋሻዎች ውስጥ ፍራሽ ላይ ያድሩ እንደነበር እና ዶክተሩም በየሁለት እና ሶስት ቀናት ልዩነት ይጎበኘን ነበር ብለዋል።

    ወደ ጋዛ በሚወስደው የሞተር ሳይክል ጉዞ ላይ አደጋ የደረሰበት ታጋች ህክምና እንዳገኘም ገልጸዋል።

    የድንገተኛ አደጋ የጤና ባለሙያውም የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒቶች እንዳመጣላቸውም ነው የተናገሩት

    ሐማስ ሁለቱን አረጋውያን ሴቶች ለመልቀቅ የወሰነው በሰብዓዊነት እና በጤና ምክንያት እንደሆነም አስታውቋል።

    የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ግለሰቦቹን ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ተወካዮች ሰኞ ዕለት አስረክቧል።

    ታጋቾቹ የተለቀቁት በግብጽ እና ኳታር አሸማጋይነት ነው። እስራኤል ሁለቱን ታጋቾች ለማስመለስ ግብጽ በማሸማገሉ ረገድ ላደረገችው ጥረት እንዲሁም ቀይ መስቀል ስላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግናለች።

  11. በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተፈጸሙ የአየር ጥቃት የተገኙ ምስሎች

    በአየር ጥቃቱ ለተገደሉ የቀብር ስነ ስርዓት

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በጋዛ ሰርጥ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።

    በዚህም የሐማስ ተዋጊዎች የሚገኙባቸው ዋሻዎች እና የቡድኑ የቅኝት ማማዎች ተመትተዋል ብሏል።

    ከስፍራው የተገኙ ምስሎች ህንጻዎች መውደማቸውን እና የቆሰሉ ፍልስጥኤማውያንንም አሳይተዋል።

    እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመችው ባለችው ጥቃት ከ5 ሺህ ፍልስጥኤማውያን በላይ መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

    በጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በጋዛ ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

  12. የተባበሩት መንግሥታት 35 ሠራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸ

    የተባበሩት መንግሥታት ሰራተኞች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 35 ሠራተኞች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እንደተገደሉበት አስታወቀ።

    የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ስድስት ሠራተኞች ባለፉት 24 ሰዓታት መገደላቸውን ገልጾ፣ በአጠቃላይም በባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 የድርጅቱ ሠራተኞች ተገድለዋል ብሏል።

    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "በህልፈታቸው አዝነናል እናም በዚህ ወቅት የተቸገሩትን ለመርዳት እየጣሩ ካሉ የሥራ ባልደረቦቻችን ጋር አብረን እንቆማለን" ሲሉም በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

    እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ፣ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።

    በእነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኞቹ ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

    ከተገደሉት መካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል። በአጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ከ5 ሺህ አልፏል።

  13. የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን እስራኤል ገቡ

    የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ እስራኤል አቅንተዋል።

    ቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ ማረፊያ በዛሬው ዕለት የደረሱት ፕሬዚዳንቱ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሏል።

    የፕሬዚዳንቱ የጉብኝቱ አላማ አገራቸው ለእስራኤል ያላትን አጋርነት ለማሳየት፣ በሐማስ ቁጥጥር ስር ያሉ ታጋቾችን እንዲፈቱ ለማገዝ እና ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግ መሆኑን አማካሪዎቻቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል።

    ማክሮን በዚህ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ በተጨማሪ ከእስራኤሉ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና ከሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

  14. ሰበር, የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት 400 ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ

    በጋዛ የደረሰው የአየር ጥቃት

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ400 በላይ ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ።

    በትናንትናው ዕለት የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ የሚገኙ 320 ዒላማዎችን መምታቱን ገልጾ በዚህም የሐማስ ተዋጊዎች የሚገኙባቸው ዋሻዎች እና የቡድኑ የቅኝት ማማዎች ወድመዋል ብሎ ነበር።

    እንደ መከላከያው ከሆነ በዚህኛው ጥቃት ኢላማ የተደረጉት ወደ እስራኤል ሮኬት ሊያስወነጭፉ የነበሩ የሐማስ ታጣቂዎች እንዲሁም እስራኤልን በባህር ለማጥቃት የሚያስችል የዋሻ መተላለፊያ ነው ብሏል።

    እንዲሁም ታጣቂዎች እንደ ጦር መሳሪያ ይጠቀሙበታል የተባለ በመስጊዶች ውስጥ የሚገኙ የማዘዣ ማዕከላት ኢላማ እንደተደረገባቸውም ገልጿል።

    መከላከያው "የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥም ጥረቱን ይቀጥላል" ሲልም አክሏል። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።

    በነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

    ከተገደሉት መካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል። በአጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ከ5 ሺህ አልፏል።

  15. በእስራኤል ማስጠንቀቂያ ከሰሜን ጋዛ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው- ተመድ

  16. እስራኤል ሁለት ተጨማሪ ታጋቾች ከጋዛ መለቀቃቸውን አረጋገጠች

    በጋዛ ውስጥ ታግተው የነበሩ ሁለት እስራኤላዊ አረጋውያን ሴቶች

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በጋዛ ውስጥ ታግተው የነበሩ ሁለት እስራኤላዊ አረጋውያን ሴቶች ሐማስ መልቀቁን እስራኤል አረጋገጠች።

    ግለሰቦቹ የ79 ዓመቷ ኑሪት ኩፐር እና የ85 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የሆኑት ዮቼቭድ ሊቭሺትዝ ቴልአቪአቭ መግባታቸውም ተገልጿል።

    ሐማስ ሁለቱን አረጋውያን ሴቶች ለመልቀቅ የወሰነው በሰብዓዊነት እና በጤና ምክንያት እንደሆነም አስታውቋል።

    የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ግለሰቦቹን ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ተወካዮች ሰኞ ዕለት አስረክቧል።

    ታጋቾቹ የተለቀቁት በግብጽ እና ኳታር አሸማጋይነት ነው። እስራኤል ሁለቱን ታጋቾች ለማስመለስ ግብጽ በማሸማገሉ ረገድ ላደረገችው ጥረት እንዲሁም ቀይ መስቀል ስላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግናለች።

    ሁለቱ የዕድሜ ባለጸጎች ቢለቀቁም የግለሰቦቹ ባለቤት የሆኑት የ85 እና የ83 ዓመት አረጋውያን አሁንም በጋዛ ውስጥ በሐማስ ታግተው እንደሚገኙ የእስራኤል ባለስልጣናት ገልጸዋል።

  17. አሜሪካ የጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን ተቃወመች

    የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረግ የለበትም ስትል አሜሪካ ተቃወመች።

    የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ጊዜው አሁን አይደለም ሲሉም የዋይት ሐውስ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ገልጸዋል።

    "የተኩስ ማቆም ስምምነት ወቅቱ አሁን ነው ብለን አናምንም" በማለት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

    "እስራኤላውያን ራሳቸውን የመከላከል መብት አላቸው። ከሐማስ አመራሮች ጋር ተያይዞ አሁንም የሚቀሩ ስራዎች አሉ" በማለት የተናገሩት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ቃለ አቀባይ ማቲው ሚለር ናቸው።

    አክለውም "ይህንን በተመለከተ የምናከናውነው ተግባር ወደ ጋዛ ሰብዓዊ እርዳታ በማግኘት ላይ ያተኮረ ነው" ብለዋል።

    አሜሪካ ይህንን ግጭት በዋነኝት እንዲከታተሉ ዴቪድ ሳተርፊልድ የተባሉ ልዑክ መሾሟን ሚለር ገልጸዋል። ልዑኩም " የሰብዓዊ እርዳታ ቀጣይነት እንዲኖረው የማድረግ እና በጋዛ ውስጥ ያሉ ሲቪሎች ጉዳት የማይደርስባቸውን ቦታዎችንም ለመለየት እየሰራን ነው" ብለዋል።

    የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያለው ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ከሰሞኑ ጥሪ አቅርበዋል።

    የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የዓለም የጤና ድርጅትን ጨምሮ አምስት የተመድ ኤጀንሲዎች የጋዛን ሁኔታ "አሰቃቂ" ሲሉም በጋራ ባወጡት መግለጫ አስፍረዋል።

    እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ አስገብቻታለሁ ባለቻት ጋዛ ሰርጥ የተጠናከረ ጥቃት እንደሚቀጥል እያስጠነቀቀች ባለችበት ወቅትም ነው የተባበሩት መንግሥታት ግጭቱ እንዲረግብ እየተማጸነ ያለው።

  18. በፍልስጥኤማውያን ላይ የተባባሰው የእስራኤላውያን ሰፋሪዎች ጥቃት

  19. የጋዛን ሰፈር ወደ ፍርስራሽ ክምርነት የቀየረው ጥቃት

  20. የእስራኤል ራስን የመከላከል መብት ገደቦች አሉበት፡ ጆሴፍ ቦሬል

    ጆሴፍ ቦሬል
    የምስሉ መግለጫ, ጆሴፍ ቦሬል

    የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል እስራኤል ያላት ራስን የመከላከል መብት ገደቦች አሉበት በማለት ተናገሩ።

    ቦሬን ላክሰንበርግ ውስጥ ከተካሄደው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ስበሰባ በኋላ እንደተናገሩት “ገደቦቹ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የተቀመጡ ናቸው።

    “እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት አላት፤ ይህም በዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ መሠረት ተግባራዊ መሆን አለበት። ይህ እንዲሁ በቃል ብቻ የሚነገር መሆን የለበትም።

    “በዚህም መሠረት ለሲቪል ሰዎች የሚቀርበውን ውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ማቋረጥ አይቻልም። በዓለም አቀፍ ሰብአዊነት ሕግ ስር በከበባ ስር ያለ ሕዝብ ውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዳያገኝ ማድረግ አይቻልም” ብለዋል።

    ቦሬል ጨምረውም ሰብአዊ እርዳታን ጭነው ከግብፅ ወደ ጋዛ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች በቂ እንዳልሆኑ እና በተለይ ነዳጅ ለጋዛ በጣም አስፈላጊ አቅርቦት መሆኑን ተናግረዋል።

    “ጋዛ ውስጥ እየሆነ ያለው በሰብአዊነት ላይ የሚደርሰው መቅሰፍት ነው። ሰብአዊ እርዳታ ማቅረብም በእጅጉ አስፈላጊ ጉዳይ ነው” ሲሉ ቦሬል አሳስበዋል።