በዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ ወረርሽኙ እየተስፋፋ ያለው የት ነው?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭት በአንዳንድ አገራት እየቀነሰ ቢሆንም ፤ በአንዳንድ አገራት ደግሞ ሊጠፋ ነው ሲባል ዳግም እያገረሸ አስቸግሯል።
ለመሆኑ በዓለማችን የወረርሽኙ ማዕከል የሆኑ አገራት የትኞቹ ናቸው?
ላቲን አሜሪካና እስያ በአንድ ቀን በቫይረሱ የሚያዙ ከፍተኛ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበባቸው አህጉሮች ናቸው። በአገራት ደረጃ ደግሞ፡
አሜሪካ ፡ አሜሪካ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ፤ ብራዚል ትከተላታለች።
ሜክሲኮ፡ በሜክሲኮ በቫይረሱ ሳቢያ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሟቾች ቁጥር በአህጉሩ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አርጀንቲና፡ ምንም እንኳን የለይቶ ማቆያ ሕጓ ጥብቅ የነበረ ቢሆንም አርጀንቲና ሰኞ ዕለት ከፍተኛ የተባለውን በቫይረሱ የተያዙና ሞቱ ሰዎች ቁጥር መዝግባለች።
ሕንድ ፡ በሕንድ እስካሁን ከ3 ሚሊየን ሰዎች በላይ በቫይረሱ ተይዘዋል። በአማካይ በአንድ ቀን ከ60 ሺህ በላይ አዲስ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። ከ58 ሺህ በላይ ሰዎችም በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሕንድ በዓለማችን ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባት አራተኛዋ አገር ናት።