በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1ሺህ186 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ የ20 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በ18 ሺህ 060 ናሙናዎች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 186 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ተቋም በዕለታዊ መግለጫቸው አስታወቁ።
ይህም በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 46 ሺህ 407 አድርሶታል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓታት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉም ተገልጿል። እስካሁን ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የ745 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በሌላ በኩል ተጨማሪ 518 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 16 ሺህ 829 ደርሷል።
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 330 ሰዎችም በፅኑ መታመማቸውን መግለጫው አመልክቷል።
እስካሁን 831 ሺህ 470 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተከናውነዋል።