
የፎቶው ባለመብት, Reuters
የምስሉ መግለጫ, አንድ በአሳ ምግቦች ማቀነባበሪያ ውስጥ የሚሰራ የ58 ዓመት ሴት በኮሮናቫይረስ መያዙን ተከትሎ 190000 ሰዎች እየተመረመሩ ነውበቻይና ሰሜን ምስራቅ የምትገኘው የሊዮንኒንግ ግዛት
ከተማ፣ ዳሊያን በከፊል እንቅስቃሴ የተገደበባት ሲሆን በከተማዋ የሚኖሩ190,000 ነዋሪዎችም የኮቪድ-19 ምርመራ እያደረጉ ነው።
ይህ የሆነው አንድ በአሳ ምግቦች ማቀነባበሪያ ውስጥ
የሚሰሩ የ58 ዓመት ሴት በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው።
ቢያንስ ሌሎች ሁለት ሰዎች የኮቪድ-19 ምልክት
አሳይተው ሲመረመሩ ኮቪድ-19 የተገኘባቸው ሲሆን በዚህም የተነሳ የከተማው አስተዳደር በርካታ ንግድ ቤቶችን ዘግቷል።
የኢንተርኔት ካፌዎች፣ የገላ መታጠቢያዎች፣ የገበያ
አዳራሾች፣ እንዲሁም ሌሎች ንግድ ቤቶች ከተዘጉት ንግድ ቤቶች መካከል ናቸው።
አስተዳደሩ በተጨማሪም በግዛቲቱ ሁለት አካባቢዎች
የሚኖሩ ሰዎችን ራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ አዝዟል።
የቻይና ማዕከላዊ መንግሥት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው
ወረርሽኞች ሲከሰቱ በፍጥነት ለመቆጣጣር የሚጥር ሲሆን፣ አያይዞም የተወሰኑ አካባቢዎችን እንቅስቃሴ በመገደብ ሰፊ ምርመራ
ያደርጋል።
ባለፈው ወር በቤይዢንግ አንድ ሰው ኮቪድ-19
ስለተገኘበት ብቻ 300 ሰዎች ተመርምረው በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።