የኢራን ፓርላማ ከተመድ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ጋር አገሪቷ መተባባር እንድታቆም ድምጽ ሰጠ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የኢራን ፓርላማ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ፣ አለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ አገሪቷ የሚኖራት ትብብር እንዲቆም የሚያግድ ድምጽ መስጠቱን የአገሪቱ መንግሥታዊ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲእስራኤል እና አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ይዞታዎች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ለማውገዝ ፈቃደኛ አልሆነም በማለት የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባ ተናግረዋል።
በዚህም የኤጀንሲው “አለም አቀፍ ተዓማኒነቱን ለሽያጭ አቅርቧል” ሲሉ ተችተዋል።
አፈ ጉባኤው የኢራን የኒውክሌር ባለስልጣናት የአገሪቱ “የኒውክሌር ማብላያ ይዞታዎች ደህንንት እስኪረጋገጥ ድርሰ ከኤጀንሲው ጋር ያላቸውን ትብብር ያቆማሉ” ብለዋል።
አክለውም የኢራን “ሰላማዊ የኒውክሌር መርሃ ግብር በፈጣን ፍጥነት ወደፊት አንደሚራመድ” ተናግረዋል።
በፓርላማ የተሰጠው ድምጽ ተምሳሌታዊ ሲሆን ውሳኔው ፖሊሲ እንዲሆን በኢራን መንግሥት ባሉ ከፍተኛ ባለሰረልጣናት መጽደቅ ይኖርበታል።
ከአውሮፓውያኑ 1970 ጀምሮ 191 አገራት የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎች ሥርጭት እና መስፋፋትን ለመከላከል ያለመውን 'ትሪቲ ኦን ዘ ነን ፕሮሊፈሬሽን ኦፍ ኒውክሌር ዌፐንስ' የተሰኘውን ስምምነት ፈርመዋል።
አምስት አገራት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ቻይና የኒውክሌር የጦር መሳሪያ እንዲኖራቸው ተፈቅዶላቸዋል።
ለዚህም ምክንያቱ ስምምነቱ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ገንብተው ሙከራ አድርገው በማጠናቀቃቸው ነው።
ኢራን የስምምነቱ ፈራሚ አባል ናት።


















