ባይደን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የተደረሰውን ስምምነት አወደሱ

የፎቶው ባለመብት, EPA
ጆ ባይደን “ለሳምንታት በእስር እና በቃላት ሊገለጽ የማይችል መከራ” ሲያሳልፉ ከነበሩ ታጋቾች መካከል አንዳንዶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊቀላቀሉ መሆኑ “በጣም አስደስቶኛል” ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኳታር እና የግብጽ መሪዎች ስምምነቱ እንዲደረስ ላሳዩት "ወሳኝ አመራር እና አጋርነት" አመስግነዋቸዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ላሳዩት “ቁርጠኝነት” አድናቆታቸውን ችረዋቸዋል።
"የዚህ ስምምነት ሃሳቦች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸው አስፈላጊ ነው" ሲል አጽንኦት ሰጥተዋል።
በስምምነቱ መሠረት በርካታ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዲገባ በማገዛቸውም ኔታንያሁን አመስግነዋቸዋል።
“ይህም በጋዛ የሚገኙ ንጹሐን ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ያግዛል” ብለዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ መድኃኒት እና ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በስምምነቱ መሠረት ጋዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።












