በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 30 ሺህ ተጠጋ

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የማሕበረሰብ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ሲሆን ከዚህ ቀደም በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ በመቶዎች ይገኝ የነበረው ወደ ሺህ ተሻግሯል። በትናንትናው ዕለትም ከፍተኛ የተባለው 1ሺህ 652 እንዲሁም በዛሬው ዕለት 982 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ ቁጥሩ ወደ 30 ሺህ ተጠግቷል። አገሪቱ በቫይረሱ ያጣቻቸው ዜጎች ቁጥር 528 አድርሶታል። በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 12 ሺህ 359 መድረሱን የጤና ሚንስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚያወጡት ዕለታዊ መግለጫ አመላክቷል። ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ609 ሺህ 463ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ አከናውናለች። ሳይዘናጉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳችንንና ሌሎችን ከበሽታው እንጠብቅ።

የቀጥታ ሽፋን

  1. ላይቤሪያ አምስት አሜሪካዊያንን በግዴታ ለይቶ ማቆያ አስገባች

    ሙቀት ሲለካ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የላይቤሪያ ጤና ባለሥልጣናት ቀብር ተሳትፈው ወደ አሜሪካ ሊበሩ የነበሩ አምስት ሰዎችን ከአውሮፕላን በማስወረድ በግዴታ ወደ ለይቶ ማቆያ መላካቸውን አስታወቁ።

    ይህ ሊሆን የቻለው ከግለሰቦቹ ጋር ለቀብር ከአሜሪካ የመጣ ግለሰብ በሞኖሮቪያ በኮሮናቫይረስ መሞቱ ከተሰማ በኋላ ነው።

    ዶ/ር ያታ ሳስኪ ዋፖዬ፣ በሞኖሮቪያ አካባቢ የኮቪድ-19 መከላከል ግብረ ኃይል ኃላፊ ሲሆኑ፣ ከግለሰቦቹ ጋር ሊሄዱ የነበሩና "ከፍተኛ ተጋላጭ" የሆኑ ግለሰቦችን እየፈለጉ መሆናቸውን ለበቢሲ ተናግረዋል።

    በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ለይቶ ማቆያ የተላኩት ግለሰቦች ላይቤሪያ የተወለዱ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ከግለሰቦቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ ገልጿል።

    ለግለሰቦቹ በተደረገላቸው ምርመራ መሰረት ከኮቪድ-19 ነጻ ቢሆኑም በላይቤሪያ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ረዥም ጊዜ ከቆዩ አሜሪካ ያላቸውን ሥራ እንዳያጡ ሰግተዋል።

  2. በትግራይ ክልል በኮቪድ-19 መከላከል ተሳታፊ የነበሩት መምህር በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ

  3. በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 30 ሺህ ተጠጋ

  4. በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 21ሺህ 452 ደረሰ

    ግራፊክስ

    ባለፉት 24 ሰዓታት ለ9 ሺህ 203 ናሙናዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ 552 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋገጠ።

    የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ጤና ሚኒስቴር በጋራ ባወጡት እለታዊ መግለጫ እንዳመለከቱት በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 21ሺህ 452 ደርሷል።

    ባለፉት 24 ሰዓታት 388 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ 15 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

    በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9ሺህ 415 ሲደርስ በኮሮና ምክንያት የሞቱ ደግሞ 380 እንደደረሰ መግለጫው አመልክቷል።

    በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው ሰው ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ 478 ሺህ 17 ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተካሂዷል።

  5. በኮሮናቫይረስ ምክንያት ፈተና የገጠመው የወባ መከላከል ስራ

    የወባ ትንኝ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የወባ መከላከያ አጎበር ማከፋፈል በወባ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር በግማሽ ይቀንሳል ሲሉ ተመራማሪዎች ገለፁ።

    በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ በፀረ ወባ የተነከረ አጎበር ማሰራጨት በመቀነሱ የተነሳ ዜጎች እየተቸገሩ ነው የሚል ስጋት አለ።

    በዚህ ዓመት በመላው አፍሪካ 228 ሚሊዮን ፀረ ወባ መድሃኒት የተነከሩ አጎበሮች ለማከፋፈል እቅድ ተይዟል።

    ነገር ግን በለንደኑ ኢምፔሪያል ኮሌጅ ያሉ ተመራማሪዎች በዚህ ዓመት ፀረ ወባ የተነከሩ አጎበሮች ስርጭት ከተስተጓጎለ በወባ ምክንያት የሚሞቱ አፍሪካውያን ቁጥር ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በዚህ ዓመት በእጥፍ እንደሚጨምር ገምተዋል።

    ተመራማሪዎቹ አጎበር ካልተሰራጨ እና ሌሎች የወባ መከላከያ መንገዶች በጊዜ ተግባራዊ ካልተደረጉ በዚህ ዓመት ብቻ 779 ሺህ ሰዎች በወባ ምክንያት ሊሞቱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

  6. በቤጂንግ የመጨረሻ የኮቪድ-19 ታማሚ ከሆስፒታል ወጡ

    አምቡላንስ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በቤጂንግ ትልቅ የገበያ ማዕከል ዥንፋዲ ተቀስቅሶ በነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቫይረሱ ተይዘው ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩት የመጨረሻው ታማሚ አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተገለፀ።

    የ52 ዓመቱ ግለሰብ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ 335 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

    የቻይና ዋና መዲና የሆነችው ቤጂንግ በጣለችው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብና በስፋት ባካሄደችው ምርመራ ቫይረሱን መቆጣጠር መቻሏ ተነግሯል።

    ለታሚዎቹም ተገቢ ሕክምና በማድረግ ረገድ መቶ በመቶ ውጤታማ እንደነበረች የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

    ዥንዋ የዜና ወኪል በቫይረሱ ከተያዙት መካከል አምስቱ በፅኑ ታመው እንደነበሩና 21 ደግሞ በባሰ የጤና ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ዘግቧል።

    ይሁን እንጅ ቤጂንግ አሁንም ከቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ነፃ አልሆነችም።

    ዛሬ በከተማዋ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰው የተገኙ ሲሆን ግለሰቡ ቀደም ሲል ከሆስፒታል ከወጡት ግለሰብ ጋር ንክኪ እንደነበራቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደነበሩ ተነግሯል።

    ምንም እንኳን ቤጂንግ የመዘገበችው በቫይረሱ የተያዙ ከውጭ የሚገቡ መንገደኞች ቁጥር እምብዛም ቢሆንም ወደ ከተማ ከውጭ አገራት የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀን በለይቶ ማቆያ እንድገቡ የሚል ጥብቅ ሕግ አላት።

  7. አፍሪካ እና ኮቪድ-19

    አፍሪካ

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን አልፏል። ከ 500 ሺህ በላይ የሚሆኑት የሚገኙት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ነው።

    ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ጋር ስትነፃፀር ደቡብ አፍሪካ በተሻለ በኮቪድ-19 በቂ መረጃ አደራጅታለች በሚል ትሞገሳለች።

    በአገሪቱም ትልቅ የተባለ የምርመራ ዘመቻ እያካሄደች ነው።

    ግን አሁን ጥያቄ የሆነው በሌሎች የአፍሪካ አገራት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 500 ሺህ ብቻ ነው የሚለው ነው።

    ባለሙያዎች ለዚህ መልሳቸው አጭርና ግልፅ ነው። አይደለም የሚል።

    የሕክምና እና የሕብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች አህጉሪቱ ያለውን አነስኛ ምርመራ የማድረግ ብቃት በማንሳት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን እንደሚልቅ ይናገራሉ።

    ነገር ግን የሕክምና ባለሙያዎች አክለው ሆስፒታሎች በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሕሙማን አለመጨናነቃቸውን በማንሳት የጉዳዩን አሳሳቢነት ይገልፃሉ።

    ለዚህ ደግሞ በርካታ መላ ምት ይሰጣል። ወደ ጤና ተቋም የመሄድ ፍርሃት፣ በበርካታ አገራት አስቀድሞ የተጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመላምቶቹ መካከል ናቸው።

    እንደ ታንዛንያ ያሉ አገራት ደግሞ በአገራቸው ያለውን የኮቪድ-19 ስርጭት መጠን የሚገልጽ ምንም ዓይነት መረጃ ባለመስጠት የመከላከል ስራውን ፈታኝ ማድረጋቸው ተገልጿል።

    በአህጉሪቱ በአጠቃላይ 22 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ሲያጡ 690 ሺህ ያህሉ ደግሞ ሙሉ በሙሉ አገግመዋል።

    በአፍሪካ እስካሁን ድረስ ስምንት ሚሊዮን ያህል የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ብቻ የተደረጉ ሲሆን፤ ነገር ግን 13 ሚሊዮን ያህል መካሄድ ነበረበት ሲሉ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር ኃላፊ ተናግረዋል።

    በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዘው ሰው የተገኘው በግብጽ የካቲት ወር ላይ ሲሆን ይህም በአውሮፓ ከተገኘ ሶስት ሳምንታት በኋላ ነበር።

    በደቡብ አፍሪካ እና ግብጽ በርካታ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣር በቅርበት በአህጉሪቱ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት እየተከታተለ ያለው ደግሞ የናይጄሪያ፣ ጋና ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ዛምብያ እና ዚምባብዌን የስርጭት መጠን በማየት መሆኑን ኃላፊው ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል።

  8. በሜክሲኮ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ አለፈ

    በሃዘን ላይ ያሉ ቤተሰቦች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በሜክሲኮ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ ማለፉን የአገሪቷ መንግሥት አስታወቀ።

    መንግሥት ይህንን ያስታወቀው አገሪቷ በቫይረሱ ባጣቻቸው ዜጎች ቁጥር የዓለማችን ሦስተኛዋ አገር መሆኗን ተከትሎ ነው።

    በዓለማችን ከፍተኛ ሞት ቁጥር የተመዘገበባቸው አገራት አሜሪካና ብራዚል ናቸው።

    የጤና ሚኒስትሩ እንዳሉት በአንድ ቀን ከ819 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር 50 ሺህ 517 አድርሶታል።

    ከ128 ሚሊየን በላይ የሕዝብ ብዛት ባላት ሜክሲኮ፤ እስካሁን 462 ሺህ 690 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

    በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ፕሬዚዳንት አንድሪስ ማኑኤል ሎፔዝ በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከ6 ሺህ እስከ 30 ሺህ ሊሆን እንደሚችል ቅድመ ግምት አስቀምጠው ነበር።

    የአገሪቷ መንግሥት ከሰኔ ወር ጀምሮ ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ማላላት ጀምሯል።

  9. በሊባኖስ የሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያጋጥም የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ

  10. የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ነፃ ምርመር ሊደርግላቸው ነው

    ሆንግ ኮንግ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የሆንግ ኮንግ ዋና አስተዳዳሪ ኬሪ ላም ኮቪድ-19 መመርመር የምትፈልጉ የከተማይቱ ነዋሪዎች በነፃ ምርመራ እንሰጣለን ሲሉ አውጀዋል።

    ምርመራው የሚከናወነው ከቤጂንግ በመጡ ሶስት ድርጅቶች ሲሆን ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ይቆያልም ተብሏል።

    አስተዳዳሪዋ የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ስለ ምርመራው በቤጂንግ ድርጅቶቹ በመሰጠቱ ምክንያት ጥርጣሬ እንዳይገባችሁ፤ ምክንያቱም እርዳታውን የጠየቀችው ሆንግ ኮንግ ናት ብለዋል።

    ሆንግ ኮንግ ግንቦትና ሰኔ ወራት ላይ እምብዛም የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች አልታዩባትም። ነገር ግን ሐምሌ ላይ የታየው የወረርሽኙ ማገርሸት የሆንግ ኮንግን አስተዳዳሪዎች አስጨንቋልን::

    ከዚህ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ደግሞ በየቀኑ ቢያንስ 100 ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነው።

  11. የብሪቲሽ ኤርዌይስ ሠራተኞች ቁርጣቸውን የሚያውቁት ዛሬ ነው

  12. ናይጄሪያው የሙዚቃ ኮከብ ሕግ መጣሱን አመነ

    የ X ይዘትን ይለፉት
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ

    ናይጄሪያዊው ኮከብ ሙዚቀኛ አዚዝ ፋሾላ ወይም በመድረክ ስሙ ናይራ ማርሊ ኮቪድ-19ኝን ለመግታት የወጣውን ሕግ መጣሱን አመነ።

    ሙዚቀኛው 'ኮንሰርት' ለማዘጋጀት ወደ ሌጎስ ባቀናበት ወቅት ነው ሕጉን የተላለፈው።

    ናይራ ማርሊ ባፈለው ማክሰኞ ከወኪሉ [ማኔጀር] ጋር ሳለ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉ አይዘነጋም።

    ሙዚቀኛው ጥፋቱን የፈፀመው ባለፈው ሰኔ ሲሆን በወቅቱ መንግሥት በጣም አስፈላጊ ምክንያት ከሌላችሁ በቀር እንዳትንቀሳቀሱ ሲል አዋጅ አውጥቶ ነበር።

    ሙዚቀኛውና ወኪሉ እያንዳንዳቸው ለፈፀሙት ጥፋት 100 ሺህ ናይራ ወይንም 258 የአሜሪካ ዶላር እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

    ሙዚቀኛውንና ወኪሉን ከሌጎስ ወደ አቡጃ ይዞ የበረረው አየር መንገድ ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ የበረራ ፈቃዱ እንዲሰረዝ ተደርጎ ነበር።

    አየር መንገዱ ሙዚቀኛው የፍርደ ቤት ዳኛ መስሎኝ ነው ይዤው የበረርኩት ሲል አስተባብሏል።

  13. በኢራቅ አይ ኤስን የሚዋጉ ወታደሮችን ወደ ቀብር አስፈጻሚነት ተቀየሩ

  14. በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊዮን ተሻገረ

    ሕንድ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊዮን ተሻገረ።

    ሕንድ 1 ሚሊዮን ዜጎቸው በቫይረሱ የተያዙባት በ20 ቀናት ውስጥ ብቻ ነው። ይህም በርካታ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በቫይረሱ ሲያዙ ከፍተኛው አሃዝ ነው።

    ሕንድ ከአሜሪካ እና ብራዚል በመቀለጠ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባቸው አገራት ዝርዝርን ተቀላቅላለች።

    ዝግ ተደርገው የነበሩ እንቅስቃሴዎች መክፈት እየጀመረች ያለችው ሕንድ፤ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን አጠናክራ ቀጥላለች።

    1.3 ቢሊዮን የህዝብ ቁጥር ባላት ሕንድ፤ እስካሁን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 2,025,409 ደርሷል። 40ሺህ 700 ሰዎች ድግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል።

  15. በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊዮን ተሻገረ

    Africa Covid-19

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በአህጉረ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊዮን ተሻገረ። ገሚሱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚገኙት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ነው።

    ይሁን እንጂ በበርካታ የአፍሪካ አገራት የሚከናወኑት የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች አነስተኛ በመሆናቸው ቫይረሱ የያዛቸው ሰዎች አሃዝ ከዚህ በላይ እንደሆነ ይታመናል።

    በአፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሆኖ የታየው በትላልቅ ከተሞች አከባቢ ነው።

    እንደ ዓለም ጤና ድርጅት አሃዝ ከሆነ በመላው ዓለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18.6 ሚሊዮን ሲሆን ከ702 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

    በአፍሪካ ደግሞ 21ሺህ ሰዎች ሲሞቱ ከ670 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።

    የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ጆን ኬንጋሶንግ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ በአፍሪካ በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 70 በመቶ ያክሉ አገግመዋል ብለዋል።

  16. "በአባታችን ቀብር ላይ ሆነን የእናታችንን ሞት ሰማን"

  17. በኢትዮጵያ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 365 ደረሰ

    በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 365 ደርሷል። አጠቃላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙት ደግሞ ወደ 21ሺህ ተጠግቷል።

    የጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ መገልጫ መሠረት እስከ ትናንት ሐሙስ የተካሄደው አጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 468ሺህ814 ነው።

    ከእነዚህ መካከል 9ሺህ027 የሚሆኑት ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ 11ሺህ506 ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው ናቸው።

    ትናንት ሐምሌ 30 የወጣው የኮሮናቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የሚከተለው ነው።

    የኮሮናቫይረስ ሁኔታ መግለጫ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

  18. የኦሃዮ ገዢ በኮሮና ተያዙ

    የኦሃይዎ ግዛት አስተዳዳሪ ማይክ ዲዋይን

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, የኦሃዮ ግዛት አስተዳዳሪ ማይክ ዲዋይን ከዚህ ቀደም ከትራምፕ ጋር ተገናኝተው ነበር

    የኦሃዮ ግዛት አስተዳዳሪ ከታቀደው የትራምፕ ጉብኝት በፊት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተነገረ።

    የግዛቷ አስተዳዳሪ የሆኑት ማይክ ዲዋይን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ሰዓታት ሲቀራቸው ነው ተብሏል። በዚህም ከፕሬዝደንቱ ጋር ለመገናኘት የያዙትን ቀጠሮ ለመሰረዝ ተገደዋል።

    ለሚቀጥሉት 14 ቀናት በመኖሪያ ቤታቸው እራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩም ጽ/ቤታቸው አስታውቋል።

    ማይክ ዲዋይን ከኦክላሆማ ግዛት አስተዳዳሪ ኬቪን ስቲት በመቀጠል በኮቪድ-19 የተያዙ ሁለተኛው የአሜሪካ ግዛት አስተዳዳሪ ሆነዋል።

    ኦሃዮ ግዛት ከ90ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ሲሆን ከ3ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

  19. እንዴት አደራችሁ?

    ማስክ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    እንዴት አደራችሁ ውድ የቢቢሲ አማርኛ ወዳጆች የቀጥታ ዘገባ ገጻችን ተጀምሯል።

    በዚህ ገጽ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት ጋር የተያያዙ ወቅታዊ መረጃዎችን ከአገር ቤት እና ከመላው ዓለም እናደርሳችኋላን።

    አብራችሁን ቆዩ።

    መልካም ቀን!