ተጨማሪ 459 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው በምርመራ ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 459 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
በመግለጫው ላይ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7319 ናሙናዎች ምርመራ መደረጉ ተጠቅሶ ከእነዚህ መካከልም 459 ሰዎች በቫይረሱ መያዛው መረጋገጡ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ 13 ሰዎች ህይወታው ሲያልፍ 358 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ማገገማቸው ይፋ ሆኗል።
በተጨማሪም በኮሮናቫይረስ ከተያዙ ግለሰቦች መካከል 185 ሰዎች በጽኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የሕክምና ክትትል እያገኙ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 356 የደረሰ ሲሆን እስካሁን በኮቪድ-19 የተያዙት ደግሞ 20 ሺህ 336 እንደደረሰ የጤና ሚኒስቴር እለታዊ መግለጫ ያሳያል።
የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተረጋገጠ አንስቶ እስካሁን ድረስ ለ459 ሺህ 746 ናሙናዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።














