ከአንድ ወር ለሚበልጥ
ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው ሳትመዘግብ የቆየችው ጎረቤት አገር ኤርትራ፤ በቫይረሱ የተያዙ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን የኮቪድ -19 ከፍተኛ
ግብረ ኃይል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታወቋል፡፡
ባለፈው የፈረንጆቹ
ግንቦት ወር አጋማሽ ላይ የአገሪቷ መንግሥት ሰፊ ምርመራ እንደሚያካሂድ አስታውቆ ነበር፡፡
በዚህም
መሰረት በአስመራ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ባጋጣሚ የተሰበሰቡ ናሙናዎች ምርመራ ትናንት ተጠናቋል፡፡
የናሙና አሰባሰብ
ሂደቱ እና ምርመራው የተካሄደው በጤና ሳይንስ ኮሌጅና በብሄራዊ ላብራቶሪ ቅንጅት ነው ተብሏል፡፡
በአጋጣሚ
ከማህበረሰቡ የተወሰዱት ናሙናዎችም የጾታ፣ የአኗኗር ሁኔታ፣ የከተማ፣ የገጠር በሚል የተለያዩ መስፈርቶችን ያሟሉና ሁሉንም
የህብረተሰብ ክፍል ያማከሉ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
በምርመራው
4659 ቤቶችን ማዳረስ የተቻለ ሲሆን ከአንድ ቤት አንድ ሰው እንዲመረመር ተደርጓል፡፡
በዚህም 4658
ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን አንዲት ሴት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎም
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከግለሰቧ ጋር ንክኪ ያላቸው 13 ግለሰቦች ተለይተው ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሴትዮዋ ባለቤት ሲሆኑ በኋላ ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡
የተደረገው ሰፊ
ምርመራ ውጤት አበረታች መሆኑን የገለጸው ግብረ ኃይሉ፤ አሁንም ግን የወረርሽኙ
ሥርጭት ገና የመጀመሪያው ደረጃ ላይ ነው ሲል አስጠንቅቋል፡፡
ኤርትራ ኮቪድ
-19 ወረርሽኝ ከጀመረ አንስቶ ወደ አገሪቷም ሆነ ከአገሪቷ የሚደረጉ በረራዎች እንዲቆሙ ያደረገች ቢሆንም፤ በየብስና በባህር
የሚደረጉ ጉዞዎች ግን አልቆሙም፡፡
ባለፉት
ጊዜያት 5ሺህ 270 ሰዎች በ81 የለይቶ ማቆያ ማዕከላት እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፤ 3ሺህ 477 ሰዎች አስፈላጊው ክትትል
ተደርጎላቸው ከማዕከላቱ ወጥተዋል፡፡
ይሁን እንጅ
1793 ሰዎች አሁንም በ45 የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ውስጥ እንደሚገኙ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡