በግብጽ ኮሮናቫይረስን ተገን አድርጎ ልጆቹን ያስገረዘው አባት ተከሰሰ

የግብጽ አቃቤ ሕግ አንድ አባት ሶስት ሴት ልጆቹን የኮሮናቫይረስ ሕክምና እየተከታተሉ ነው በሚል ሽፋን በማስገረዙ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ።
አባትና ግርዛቱን የፈፀመው ዶክተር ጉዳያቸው ወደ ወንጀል ችሎት ተመርቷል።
የልጆቹን መገረዝ ለፖሊስ ያመለከተችው እናታቸው ናት።
እናትየው ከአባታቸው ጋር የተፋታች ሲሆን፣ አባት ልጆቹን "የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ትከተባላችሁ" በሚል ወደ ክሊኒኩ እንደወሰዳቸው ተናግራለች።
በክሊኒኩ ውስጥ ማደንዘዣ ከተወጉ በኋላ መገረዛቸው ተገልጿል።
በግብጽ ከጎርጎሳውያኑ 2008 ጀምሮ የሴት ልጅ ግርዛት ቢከለከልም አሁንም ግን በሰፊው ይተገበራል።














