የ30 ዓመቱ የጅግጅጋ ነዋሪ የኮሮናቫይረስ ተገኘበት

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 123 የደረሰ ሲሆን 41 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። ለአለም ስጋት ለሆነው ኮሮና እስካሁን ድረስ የመከላከያ ክትባትም ሆነ የፈውስ መድኃኒት አልተገኘለትም። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚሉት በሽታውን መከላከል የሚያስችሉ ቀላል መንገዶች አሉ የእጅን ንጽህና በአግባቡ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ቀዳሚዎቹ ናቸው። ከተቻለም ከቤት አለመውጣትና በርካታ ሰው ከሚገኝባቸው ቦታዎች እራስን ማራቅ በተደጋጋሚ እየተመከረ ነው። ቢቢሲ አማርኛም ስለወረርሽኙ ዜናና መረጃዎችን እዚህ ገጽ ላይ የቀጥታ ዘገባዎችን ያቀርባል፤ ይከታተሉ።

የቀጥታ ሽፋን

  1. ሳዑዲ አረቢያ የኮሮና ቫይረስ ህጓን አላላች

    ኮሮና በሳዑዲ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስን መዛመትን ለመግታት ጥላቸው የነበሩ አስገዳጅ መመሪያዎቿን አላልታለች።

    ለ24 ሰአታት ተጥሎ የነበረው የሰአት እላፊ የሚነሳ ሲሆን ሰዎች ወጥተው መንቀሳቀስ ይችላሉም ተብሏል።

    ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ መገበያያ መደብሮች ይከፈታሉ፤ አንዳንድ ፋብሪካዎችም ስራ ይጀምራሉ።

    ህጓን ያላላችው የረመዳንን ፆም በማስመልከት እንደሆነ ያሳወቀችው ሳዑዲ አረቢያ፤ አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በሚያዳግቱ እንደ ጂምናዚየምና ሬስቶራንቶች ያሉ ቦታዎችን ግን አይመለከትም ብላለች።

    ሙሉ በሙሉ ዝግ የሆኑት መካና መዲና በመሳሰሉ ከተሞቿ የተላለፉት መመሪያዎች የሚቀጥሉ ይሆናል፤ ቤት መቀመጥም አስገዳጅ እንደሆነ ይቀጥላል።

    በሳዑዲ አረቢያ 16ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 136 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

  2. የአስራ ሦስት ልጆች አባት በቫይረሱ ተያዙ

    ሮይ ሃን ከቤተሰቦቻቸው ጋር

    የፎቶው ባለመብት, Lesley Martin

    ከአስር በላይ ልጆች ጋር ቤት መቀመጥ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አያዳግትም ይባስ ብሎ የ13 ልጆች አባት የሆኑት ሮን ሃን በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

    የስኮትላንዷ ግዛት ደንዲ ነዋሪ የሆኑት አባት በሙያቸውም ነርስ ናቸው።

    ከሙያቸውም ጋር ተያይዞ ከኮሮና ህሙማን ጋር ከመገናኘታቸው አንፃር በቫይረሱ መያዛቸው ምንም እንዳላስደነቃቸው ተናግረዋል።

    በአሁኑ ወቅት የሚታይባቸውም ምልክት መካከለኛ ነው ተብሏል።

    ሮይ ሃን

    የፎቶው ባለመብት, Roy Hann

  3. በቻይና ውሃን፤ ሁሉም የኮሮና ታማሚዎች ድነው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተነገረ

    ውሃን

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው በተገኘባት የቻይናዋ ከተማ ውሃን የሚገኙ የኮሮና ታማሚዎች በሙሉ ከሆስፒታል መውጣታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

    የብሔራዊ ጤና ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ሚ ፌንግ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት በፅኑ ህመም ላይ የነበሩት የመጨረሻው ታማሚ ከበሽታው ድነው አርብ እለት ከሆስፒታል ወጥተዋል።

    ቃል አቀባዩ በከተማዋ በቫይረሱ የተያዘ አዲስ ሰው እንደሌለም አክለዋል።

    በቻይና ወረርሽኙ በታህሳስ ከጀመረ አንስቶ 82 ሺህ 816 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 4 ሺህ 632 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

    ከእዚህ መካከል 56 በመቶ የሚሆኑት ወይም 46 ሺህ 452ቱ የተመዘገቡት በውሃን ከተማ ነው።

  4. ወረርሽኙ በፍጥነት እየተስፋፋ ያለባቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?

    በኮሮና ያጡ ቤተሰቦች ኃዘን ሲገልፁ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    አሜሪካና የአውሮፓ አገራት ባለፉት ሳምንታት የወረርሽኙ ማዕከል ሆነዋል። በሌሎች አገራትም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

    ኢኳዶር፡ በኢኳዶር እስካሁን 22 ሺህ 791 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ቁጥር መጋቢት 17፣ 2012ዓ.ም የተመዘገበ ነበር። በአገሪቷ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ900 በታች መሆኑን የአገሪቷ ባለሥልጣናት ቢያስታውቁም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ይነገራል። የሟች ቤተሰቦችም የቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ለመቅበር እንደተቸገሩ ሲገልፁ ነበር።

    ብራዚል፡ የካቲት 18፣ 2012 ዓ.ም የመጀመሪያውን በቫይረሱ የተያዘ ሰው በመዘገበችው ብራዚል፤ አሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 55 ሺህ 224 ደርሷል። 3 ሺህ 762 ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። በላቲን አሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ወረርሽኝ ወቅት ፕሬዚደንት ጀር ቦልሶናሮ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የተጣሉትን ገደቦች በመቃወም በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመሳተፋቸው ተተችተዋል።

    ቱርክ፡ ቱርክ የመጀመሪያውን በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያገኘችው መጋቢት 2፣2012 ዓ.ም ሲሆን አሁን ቁጥሩ 107 ሺህ 773 ደርሷል። በዓለም በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት ዝርዝርም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በቱርክ እስካሁን 2 ሺህ 706 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል።

    ሩሲያ፡ በሩሲያ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 74 ሺህ 588 ደረሷል። ይህ ቁጥር ከአንድ ወር በፊት 1 ሺህ ነበር። የሟቾች ቁጥርም 681 ሆኖ ተመዝግቧል።

  5. እንግሊዝ ሰራዊቷን በኮሮና ምርመራ ልታሰማራ ነው

    አንድ የሰራዊት አባል

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    እንግሊዝ አስፈላጊ ለሚባሉ የስራ ዘርፎች ቅድሚያ በመስጠት በምታደርገው ምርመራ ሰራዊቷን ልታሰማራ መሆኑን አስታውቃለች።

    ሰራዊቱ የሚሰማሩት በአብዛኛው የማይደረስባቸው ቦታዎች ላይ ሲሆን ምርመራ የሚሰጡት እየተንቀሳቀሱ ነው ተብሏል።

    ይህንን ለማገዝ ዘጠና ስድስት የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ የጤና ማዕከሎችን ያቋቋመች ሲሆን፤ የእንክብካቤ መስጫ ተቋማት፣ ፖሊስ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ከዚህም ምርመራ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

    የተመረጡት የሰራዊቱ አባላት ምርመራውን ለማካሄድ ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን፣ ናሙናውን ከሰበሰቡ በኋላ ውጤቱ በአርባ ስምንት ሰአታት ውስጥ እንደሚታወቅም ተገልጿል።

    ሃገሪቷ ሰራዊቷን ለማሰማራት ከውሳኔ የደረሰችው የጤና ባለሙያዎች ምርመራ ለማካሄድ ረዥምና አስቸጋሪ ጉዞ እያደረጉ መሆናቸውን ተከትሎ ነው።

    ከዚህም በተጨማሪ በርካታ እንክብካቤን የሚሰጡ ማእከላት ሰራተኞቻቸው ምርመራ እንዳላደረጉና፣ የኮሮና ምልክት ታይቶብናል ቢሉም የምርመራ ማዕከላትን ማግኘት አዳጋች በመሆኑ ነው።

    መንግሥት ከሰሞኑ በየቀኑ የሚያደርገውን ምርመራ በመጨመር 100ሺህ ምርመራዎችን በየቀኑ ለማካሄድ እንዳቀደም አስታውቋል። እስካሁን ባለው መሪጃ ሃገሪቷ በየቀኑ የምታደርገው ምርመራ 28 ሺህ አካባቢ ነው።

    በትናንትናው ዕለት በእንግሊዝ ሆስፒታሎች በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሃያ ሺህ መብለጡን የጤና ኃላፊዎች ገልጸዋል።

  6. በአለም ላይ በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ አለፈ

  7. ኮሮናቫይረስ፡ ህንድ ትናንሽ ሱቆች እንዲከፈቱ ፈቀደች

    በህንድ ልጅ አቅፋ የምትጓዝ ሴት

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    የምስሉ መግለጫ, በሚሊየን የሚቆጠሩ ህንዳዊያን ግብይታቸው በአጎራባች በሚገኝ ሱቅ ላይ የተመሰረተ ነው

    በህንድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት አገሪቷ የጣለችውን የእንቅስቃሴ ገደብ ተከትሎ ከአንድ ወር በላይ ተዘግተው የነበሩ ትናንሽ የንግድ ተቋማት እንዲከፈቱ ፈቀደች።

    በእነዚህ ተቋማት መስራት የሚችሉት ግን ግማሽ ያህል ሰራተኞች ብቻ ናቸው ሲሉ የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።

    እነርሱም ቢሆኑ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ እንዲሁም አካላው ርቀታቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

    ይሁን እንጅ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች የገበያ ማዕከላት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደተዘጉ ይቆያሉ ተብሏል።

    ውሳኔው የህንዷ ከተማ ደልሂ ቀስ በቀስ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋን እንደገና ለመጀመር የምታደርገው ሙከራ አካል እንደሆነ ተነግሯል።

    በህንድ እስካሁን 25 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 780 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

  8. በኒውዮርክ የመድኃኒት መደብሮች የኮሮና ምርመራ ሊጀመር ነው

  9. በኮሮና ሞተዋል የተባሉት የ74 ዓመት አዛውንት በሕይወት ተገኙ

    በኮሮና ሞተዋል የተባሉት የ74 ዓመት አዛውንት በሕይወት ተገኙ

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    በኢኳዶር በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው እንዳለፈ የተነገረው የ74 ዓመት ሴት በሕይወት ተገኙ።

    አዛውንቷ አልባ ማሩሪ የሚኖሩት በኢኳዶር የኮቪድ -19 ማዕከል በሆነችው ጉያቂል ነው።

    እንደ አገሪቷ ጋዜጣ ኤል ኮሜርሲዎ ዘገባ፤ አዛውንቷ ማሩሪ ከፍተኛ ትኩሳትና መተንፈስ ችግር ካጋጠማቸው በኋላ ሆስፒታል የገቡት ባለፈው ወር ነበር።

    በዚያው ወር መጨረሻ ላይ መሞታቸው ተነገረ።

    ሆስፒታሉም ቤተሰባቸው አስከሬናቸውን ከንክኪ ነፃ ለመሆን በርቀት እንዲያዩ አደረገ።

    የእህታቸው ልጅ ጃሜ ሞርላ ሲያየቸው አክስቱ እንደሆኑ አስቦ እንደነበር ለባለስልጣናት ተናግሯል።

    “ፊታቸውን ለማየት በጣም ፈርቸ ነበር ፤ አንድ ሜትር ከግማሽ ያህል ርቄ ነበር የተመለከትኳቸው፤ ፀጉራቸው ተመሳሳይ ነበር” ሲል ለኤ ኤፍ ፒ ተናግሯል።

    ከዚያም በስርዓቱ መሰረት አስከሬናቸው እንዲቃጠል ከተደረገ በኋላ የእርሳቸው እንደሆነ የተነገራቸው የአስከሬን አመድ ለቤተሰብ ተላከ።

    ይሁን እንጅ በሞት አፋፍ የነበሩት አዛውንት ሀሙስ እለት ከነቁ በኋላ ወደ ቀልባቸው ተመልሰው ለዶክተሮች ስማቸውን በመንገር እና የስልክ ቁጥር በመስጠት እህታቸው ጋር እንዲደውሉላቸው ጠየቁ።

    ተደወለ፤ እህታቸው ስልኩን አነሱት።

    ቤተሰብ የማን አስከሬን አመድ በቤታቸው እንደተቀመጠ ባያውቁም በደስታ ከመፈንጠዝ አላገዳቸውም። አዛውንቷ ማሩሪ በሕይወት ተገኝተዋል።

    ይህ ሊሆን የቻለው በሆስፒታል ውስጥ በሰዎች ማንነት በተፈጠረ መምታት መሆኑ ተገልጿል።

    ሆስፒታሉ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ በነበረው መጨናነቅ ሳቢያ ስለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቋል።

    የአዛውንቷ ቤተሰቦች ግን ለተፈጠረው ስህተት እንዲሁም አስክሬን ላቃጠሉበት ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።

    ኢኳዶር በኮሮናቫይረስ ክፉኛ የተጠቃች አገር ናት። በአገሪቷ ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 600 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

    የ X ይዘትን ይለፉት
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ

  10. የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሊሆን ነው?

  11. እንደምን አደራችሁ?

    ፎቶው ከጌቲ ኢሜጅስ ማህደር የተገኘ ሲሆን በኮሮና ምክንያት ተሰብስቦ ፀሎትም ሆነ ሃይማኖታዊ አምልኮቶች ማካሄድ በመከልከሉ በአንዋር መስጊድም የረመዳን ፆም እንዲህ ተጀምሯል።

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    እሁድ ጥዋትን እንዴት እያሳለፋችኋት ነው?

    በአለም ላይ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን እየተጠጋ ነው። በዚህም ክፉኛ እየተጠቁ ያሉት አሜሪካና የአውሮፓ ሃገራት ናቸው። አፍሪካ እንደ አህጉር ከ25 ሺ በላይ በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።

    በኢትዮጵያም በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 122 ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 29 ሰዎች አገግመዋል፣ የሶስት ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል። በአገሪቷም ውስጥ እየተደረጉ ያሉ ምርመራዎችም እየጨመሩ ሲሆን እስካሁን ባለው 12ሺ688 ሰዎች የጉዞ ታሪክ ያላቸውና ከህሙማኑ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

    አገሪቷ የምርመራ ቁጥሯን በማሳደግ በቀን እስከ 4ሺ ሰዎችን የመመርመር እቅድ እንዳላትም ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። በተለያዩ የአገሪቷ ከተሞችም ምርመራ ተጀምሯል። ከዚሀም በተጨማሪ ቤት ለቤት የሚደረጉ የሙቀት ልኬቶች እየተደረጉ ሲሆን፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችም ሙቀታቸው ተለክቷል።

    በግላችን የሚደረጉ ጥንቃቄዎችንም አንዘንጋ፣ እጆቻችን በተደጋጋሚ መታጠብ እንዲሁም አካላዊ ርቀታችንንም በተቻለ መጠን እንጠብቅ።

    ቢቢሲ አማርኛ ከኮሮና ጋር በተያያዘ አገራት እየወሰዷቸው ስሏሏቸው እርምጃዎች፣ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ታሪክ፣ እየተሞከሩ ስላሉ መድኃኒቶችና ሌሎች መረጃዎችን ከቀጥታ ዘገባችን ታገኛላችሁ

    የዛሬ እሁድ ሚያዝያ 18/2012 ዓ.ም የቀጥታ ዘገባችን እዚህ ላይ ይጀምራል። የቅዳሜ ዘገባዎቻችንን ለመመልከት ከፈለጋችሁ ወደ ታች በመውረድ ልታገኙ ትችላላችሁ።

    መልካም እሁድ እንዲሆንላችሁ ተመኘን

  12. 'የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ' ታሰሮ የነበረው አስክንድር ነጋ ተለቀቀ

    እስክንድር ነጋ

    ለሰዓታት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የቆየው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀ መንበር እስክንድር ነጋ መለቀቁን ፓርቲው አስታወቀ።

    እስክንድር ከእስር የወጣው ምሸት ሦሰት ሰዓት አካባቢ በመታወቂያ ዋስ መሆኑም ተገልጿል።

    ቢቢሲ ያናገራቸው አንድ የባልደራስለ እውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባል እንደተናገሩት እስክንድር በፖሊስ የታሰረው የኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር መንግሥት ያወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሷል በሚል እንደሆነ ገልጸዋል።

    እስሩ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ስሙ ካባ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሕገወጥ ከተባሉ ቤቶች መፍረስ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተጠቅሷል።

    እስክንድር ኮልፌ አካባቢ ከተከሰተው ነገር ጋር በተያያዘ ሕግ ተላልፎ የፈጸመው ድርጊት ምን እንደሆነ ለማወቅ ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

    ቢቢሲ ስለእስክንድር ነጋ እስር በስልክ ለማረጋገጥ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያደረጋቸው የስልክ ጥሪዎች ምላሽ ያላገኘ ሲሆን፤ የፌደራል ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ደግሞ በዚህ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ይህንን በሚመለከት መግለጫ የመስጠት ስልጣን የሌላ አካል መሆኑን ገልጿል።

    የእስክንድር ነጋ ባልደረቦች ከመፈታቱ በፊት ለቢቢሲ እንደገለጹት ታስሮ ወደሚገኝበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ሲሆን የሚያስፈልገውን አልብሳት ይዘው ሄደው ነበር።

  13. ትራምፕ አገራቸው ለኢትዮጵያ ቬንትሌተሮችን እንደምታቀርብ ገለጹ

    ትራምፕ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የ X ይዘትን ይለፉት, 1
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ, 1

    የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ገለጹ።

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ስለስልክ ውይይታቸው በትዊተራቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አረጋግጠዋል።

    ትራምፕ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኮሮናቫይረስ ጽኑ ህሙማን መርጃ የሚያስረፈልገውን የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እንደሚፈልጉ እንደነገሯቸው አመልክተዋል።

    ጨምረውም አሜሪካ ጥያቄውን በመቀበል ድጋፍ ለማድረግ አቅሙ እንዳለትና ይህንንመ እንደሚያደርጉ በትዊተር መልዕክታቸው ላይ ገልጸዋል።

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በበኩላቸው በትዊተር እንዳመለከቱት በውይይቱ ላይ የሁለቱ አገራት ቀጣይ ግንኙነት የሚያረጋግጡ ጉዳዮች እንደተነሱ ገልጸዋል።

    በተጨማሪም አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያና የበረሃ አንበጣን በመቆጣጠር በኩል ድጋፍ ለማድረግ ያላትን ፈቃደኝነት አድንቀዋል።

    ፕሬዝዳንቱም ሆኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይታቸው ላይ ሌሎች ጉዳዮች ስለመነሳታቸው ያሉት ነገር የለም።

    ዶናልድ ትራምፕ ሐሙስ ዕለት የኢትዮጵያ ጎረቤት ከሆኑት ከኬንያና ከደቡብ ሱዳን አቻዎቻቸው ጋር ተመሳሳይ ውይይት ማድረጋቸውንና ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

    የ X ይዘትን ይለፉት, 2
    ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

    ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

    ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።

    የ X ይዘት መጨረሻ, 2

  14. መቼ ነው ወደ ሆስፒታል መሄድ ያለብን?

    ምርመራ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    መቼ ነው ወደ ሆስፒታል መሄድ ያለብኝ? በርካታ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች በቂ እረፍትና እንደ ፓራሲታሞል ያለ ሕመም ማስታገሻዎች ከወሰዱ ያገግማሉ።

    ሰዎች ወደ ሕክምና ጣቢያ መሄድ ያለባቸው የአተነፋፈስ ችግር ካጋጠማቸው ነው። ዶክተሮች የታማሚን ሳንባ ከመረመሩ በኋላ አስፈላጊውን ሕክምና ያዛሉ። አስፈላጊ ከሆነ ኦክስጂንና ቬንቲሌሽን ሊታዘዝ ይችላል።

    ነገር ግን ሰዎች በሽታው ይዞኛል ብለው ከጠረጠሩ አስቀድመው ወደ ነፃ የእርዳታ መስጫ ቁጥሮች ቢደውሉ ይመከራል። የኢትዮጵያ ነፃ መስመር 8335 ወይም 952 ነው።

    የመተንፈስ ችግር ካለብዎ በተለይ ደግሞ ከጥቂት ቃላት ብቻ ማውጣት ካልቻሉ ደውለው ሐኪም ቢያማክሩ ይመረጣል። የድንገተኛ ክፍል እና የህብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስት ዶ/ር ፅዮን ፍሬው የጤና ሚንስትር አማካሪ ናቸው።

    በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በሆነባት አሜሪካ፣ ኒውዮርክ የሚገኙት ዶ/ር ፅዮን እንደሚሉት፤ ወደ ህክምና መስጫ ሳይሄዱ ቤታቸው ማገገም የሚችሉ ሰዎች አሉ።

    "ሆስፒታል መሄድ የሚያስፈልጋቸው ከ10 በመቶ በታች ናቸው። በእድሜ የገፉ ሰዎችና የተለያየ ህመም ያለባቸው ሰዎች ሆስፒታል መሄድ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ወጣቶችና ሌላ በሽታ የሌለባቸው ሰዎች ቤት እንዲሆኑ ይመከራል" ይላሉ። ተጨማሪ ለማንበብ፡ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው? መቼ ነው ሐኪም ቤት መሄድ ያለብኝ?

  15. ኬንያ ሰዓት እላፊዋን አራዘመች

    Kenya

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ኬንያ ኬንያ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር ላለፉት ሳምንታት ጥላው የነበረው የስዓት እላፊ ገደብን ለቀጣዮቹ ሦስት ሳምንታት አራዘመች።

    የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በቀጥታ ቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት በመላው አገሪቱ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ለ21 ቀናት ባለበት ይጸናል።

    በተጨማሪም ዋና ከተማዋ ናይሮቢን ጨምሮ በወደብ ከተማዋ ሞምባሳና በሌሎች ሁለት ከተሞች ላይ የተጣለው ከከተማ መውጣትና መግባት እገዳም ለሦስት ሳምንት ባለበት እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

    ኬንያ እስካሁን 17 ሺህ ሰዎች የመረመረች ሲሆን 336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 94 ሰዎች ማገገማቸው ሲገለፅ 14 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

  16. አያክስ አመስተርዳም እየመራው የነበረው የደች ሊግ ተሰረዘ

    አያክስ አምስተርዳም

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የኔዘርላንድስ እግር ኳስ ማኅበር የያዝነውን ዓመት ውድድር መቋጨት ባለመቻሉ ምክንያት ኤርዲቪሴ የተሰኘውን ውድድር መሰረዙን አስታውቋል።

    ትናንት አርብ መተሰረዙ የተነገረው የእግር ኳስ ሊግ አሸናፊም ሆነ ወዳቂ ክለቦች አልተለዩም።

    ኔዘርላንድስ ውስጥ አበይት ክንውኖች እስከ መስከረም ድረስ እንዳይካሄዱ ዕግድ ተጥሎባቸዋል።

    ከዋናው ሊግ በተጨማሪ ሁለተኛው ሊግም መሰረዙ ታውቋል።

    ዘጠኝ ጨዋታዎች ቀርተውት የነበረውን ውድድር አያክስ አምስተርዳም በጎል ልዩነት እየመራው ነበር።

    መሪው አያክስና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኤዜድ አልክማር ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ሊያልፉ ይችላሉ እየተባለ ነው።

  17. የተራዘመው የለንደን ማራቶን ታዋቂ ሯጮችን ብቻ ሊያሳትፍ ይችላል

    ቀነኒሳ በቀለ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የለንደን ማራቶን ታዋቂ ሯጮችን ብቻ ሊያሳትፍ እንደሚችል የውድድሩ ኃላፊ ሂዩ ብራሸር ተናግረዋል።

    ኃላፊው ውድድሩ ሊካሄድባቸው የሚችሉ 10 አማራጮች መቅረባቸውን አሳውቀው ጊዜው የበለጠ ሊራዘም እንደሚችል ጠቁመዋል።

    ውድድሩ ነገ ሚያዝያ 18 ነበር ሊካሄድ ዕቅድ ወጥቶለት የነበረው። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ መስከረም 24/2013 ዓ.ም ተዘዋውሯል።

    ባለፈው ዓመት በታካሄደው ሩጫ 43 ሺህ ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸው አይዘነጋም።

    ያለፈው ዓመት የለንደን ማራቶን ለእርዳታ የሚሆን 81 ሚሊዮን ዶላር ተዋጥቶበታል።

  18. ሰበር, አራት ቻይናዊያንና አንዲት ኢትዮጵያዊት ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

    በኢትዮጵያ ተጨማሪ አምስት ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው በምርምራ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

    ከአምስቱ ሰዎች መካከል ሦስቱ ወንዶችና አንዷ ሴት የቻይና ዜግነት ያላቸው ሲሆን የተገኙትም ሰበታ ከተማ ውስጥ ነው። ሌላኛዋ ሴት ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪና ኢትዮጵያዊት ናቸው።

    ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በ1079 ሰዎች ላይ የወረርሽኙ ምርመራ መደረጉን ያመለከተው የሚኒስቴሩ መግለጫ ከእነዚህ መካከልም አምስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ብሏል።

    ቻይናዊያኑ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊቷን በተመለከተም ገና ማጣራት እየተደረገ መሆኑ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።

    እስካሁን በወረርሽኙ ተይዘው የህክምና ክትትል ከሚደረግላቸው ሰዎች መካከል ተጨማሪ አራት ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውም ተነግሯል፤ በዚህም በአጠቃላይ ከበሽታው የዳኑ ሰዎች ቁጥር 29 ደርሷል።

    በሽታው የተገኘባቸው ኢትዮጵያዊት ሴት እድሜያቸው 75 ሲሆን ቻይናዊያኑ ከ28 እስከ 59 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

    አስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ 12688 ሰዎች ላይ የበሽታው ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 122 ሰዎች በበሽታው ተይዘው ተገኝተዋል። ሦስት ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

  19. በኮሮናቫይረስ ተይዘው የዳኑ ሰዎች ድጋሚ እንደማይያዙ ማስረጃ የለም ተባለ

    ሀኪሞች

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    በኮሮናቫይረስ ተይዘው የዳኑ ሰዎች በድጋሚ በበሽታው እንደማይያዙ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ እንደሌለ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

    ድርጅቱ እንዳለው በአሁኑ ጊዜ “ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ድጋሚ በኮቪድ-19 እንዳይያዙ የሚያደረግ ተፈጥሯዊ የመከላከያ ዘዴን አዳብረው እንደሆነ የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልተገኘም።”

    በበሽታው ተይዘው የዳኑ ሰዎች በድጋሚ ከመያዝ የሚጠብቃቸውን የበሽታ መከላከያ ስለሚያዳብሩ ሰውነታቸው ቫይረሱን መዋጋት ይችላሉ የሚሉ ሃሳቦች በስፋት ሲነገሩ ቆይተዋል።

    ይህንን በተመለከተም በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ምርመራና ቅኝት እየተደረገ መሆኑም ተነግሯል።

    ሰዎች በበሽታው ከተያዙ በኋላ ጸረ ተህዋሲ ተፈጥሯዊ መከላከያ ማዳበራቸው ከተረጋገጠ ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሏል።

  20. ከኮሮናቫይረስ ለማገገም ምን ያክል ጊዜ ይወስዳል?