የ30 ዓመቱ የጅግጅጋ ነዋሪ የኮሮናቫይረስ ተገኘበት

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 123 የደረሰ ሲሆን 41 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። ለአለም ስጋት ለሆነው ኮሮና እስካሁን ድረስ የመከላከያ ክትባትም ሆነ የፈውስ መድኃኒት አልተገኘለትም። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚሉት በሽታውን መከላከል የሚያስችሉ ቀላል መንገዶች አሉ የእጅን ንጽህና በአግባቡ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ቀዳሚዎቹ ናቸው። ከተቻለም ከቤት አለመውጣትና በርካታ ሰው ከሚገኝባቸው ቦታዎች እራስን ማራቅ በተደጋጋሚ እየተመከረ ነው። ቢቢሲ አማርኛም ስለወረርሽኙ ዜናና መረጃዎችን እዚህ ገጽ ላይ የቀጥታ ዘገባዎችን ያቀርባል፤ ይከታተሉ።

የቀጥታ ሽፋን

  1. በአሜሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊዮን ደረሰ

  2. ቺሊ ከኮሮናቫይረስ ላገገሙ "ከቫይረሱ ነፃ" የሚል የምስክር ወረቀት ልትሰጥ ነው

  3. ኮሮናቫይረስ ሁለቴ ሊይዘን ይችላል?

  4. አንዳንድ አገራት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የጣሉትን እገዳ እያነሱ ነው። እነማን?

  5. በአዲስ አበባ ሁለት ወጣቶች በጥይት የተመቱበት ክስተት ምንድን ነው?

  6. የኤርትራውያን ስደተኞች ስጋት በኢትዮጵያ

  7. ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮችን እየረዳ ያለው ቢሊየነር ጃክ ማ ማነው?

  8. በኒው ዮርክ ዋነኛዋ ዶክተር እራሷን አጠፋች

  9. እውን የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል?

  10. በዩናይትድ ኪንግደም ኮሮናቫይረስ በተያዙ ህፃናት ላይ ያልተለመደ ምልክት መታየቱ ተገለፀ

  11. የኮሮናቫይረስ ክትባትን በማግኘት ህንድ የዓለምን ሕዝብ ትታደግ ይሆን?

  12. ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባት የተሞከረባቸው በጎ ፈቃደኞች

  13. በዓለም ላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን አለፈ

  14. ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፣ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ

    ቭላድሚር ካቭችኮቭ

    የፎቶው ባለመብት, screen shot

    የቢቢሲ ጋዜጠኞች ቡድን ከሰሞኑ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ማህበራዊ ሚዲያውን ያጥለቀለቁትንና ሃሰተኛ ወይም መሰረት የሌላቸውን መረጃዎች ሰብስቧል።

    የአለምን ህዝብ የመቆጣጠሪያ መንገድ

    ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዘው የሚሰጡ አስተያየቶች ማብቂያ የላቸውም። ኮሮናቫይረስን የፈጠሩት በአለም ታላላቅ የሚባሉ ኃይሎች ሲሆኑ ይህም የአለምን ህዝብ ለመቀነስ የወጠኑት ሴራ እንደሆነ የቀድሞው የሩሲያ ወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ቭላድሚር ካቭችኮቭ በዩቲዩብ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል።

    የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ በሰው ወይም በላብራቶሪ ስለመሰራቱ ሳይንሳዊ መረጃዎች ቢኖሩም በርካታ ሳይንቲስቶች ግን ከእንስሳት ነው የመጣው በማለት አጣጥለውታል ብለዋል።

  15. "ባለቤቴ ዶክተር ሊያይ እንደሄደ አልተመለሰም"

    ሳንድራ ከባሏ ጋር

    የፎቶው ባለመብት, SandraWyness

    ስኮትላንዳዊቷ ሳንድራና የ53 አመት ባለቤቷ የተጋቡት ከሃያ አምስት አመት የጓደኝነት ጊዜ በኋላ ከስድስት ወር በፊት ነው።

    ባለቤቷ ከጥቂት ቀናት በፊት ሳል፣ ሙቀትና ሌሎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይተውበት ወደ ጤና ማእከል አመራ። ባለቤቱም ሳንድራ ይህ የመጨረሻዋ ይሆናል ብላ አልጠበቀችም።

    ራሱ እየነዳ ነበር ወደ መለስተኛ ክሊኒክ ለህክምና ያመራው። ክሊኒኩ በደሰረበት ወቅት የትንፋሹ መቆራረጥ እንዲሁም በደሙ ውስጥ ያለው የኦከስጅን መጠን መቀነስ የጤና ባለሙያዎቹን ስላሳሰባቸው ለበለጠ ምርመራ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ላኩት።

    ሆስፒታሉ ከደረሰ በኋላም ህይወቱ ወዲያው አለፈ፤ ባለቤቱ የመሰናበቱንም ዕድል አላገኘችም።

    ባለቤቷን በሞት የተነጠቀችው ሳንድራ ሰዎች ቤታቸው እንዲቀመጡ እንዲሁም አድርጉ የተባሉትን ጥንቃቄዎችም እንዲተገብሩ ተማፅናለች።

  16. የእንቅስቃሴ ገደብ የቀየረው የረመዳን ገፅታ በፎቶ

  17. ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፡ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ

  18. የ30 ዓመቱ የጅግጅጋ ነዋሪ ቫይረሱ ተገኘበት

    ዶ/ር ሊያ ታደሰ

    የፎቶው ባለመብት, MOH

    በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 957 ናሙናዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ መያዙን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 123 ደርሷል።

    በቫይረሱ የተያዘው የ30 ዓመት የጅግጅጋ ነዋሪ ሲሆን ከፑንት ላንድ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ መሆኑ ተገልጿል።

    ምርመራው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙ የምርመራ ጣቢያዎች እንደተደረገ ተነግሯል።

    በኢትዮጵያ እስካሁን 13 ሺህ 645 ምርመራዎች የተደረጉ ሲሆን 123ቱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

    በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 41 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን 12ቱ በትናንትናው እለት ብቻ ያገገሙ ናቸው።

  19. አስር በመቶ የሚሆነው የእንግሊዝ ህዝብ በቫይረሱ ሳይያዝ አይቀርም ተባለ

    በእንግሊዝ የፊት ጭምብል አድርገው ሲሄዱ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ክርስቶፍ ፍሬዘር ለቢቢሲው ጋዜጠኛ አንድሪው ማር እንደተናገሩት አሁን ባለው የቫይረሱ የመዛመት ሁኔታ እስከ አስር በመቶ ህዝብ በቫይረሱ ተይዟል ተብሎ ይገመታል። ይህም ማለት ስድስት ሚሊዮን የሚሆነው የእንግሊዝ ህዝብ ነው።

    ፕሮፌሰሩ በአሁኑ ወቅት በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ወይም ንክኪ የነበራቸው ሰዎችን መከታተል የሚችል መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) እየሰሩ ነው።

    መተግበሪያው የቫይረሱ ምልክት ከመታየቱ በፊት አምሳ በመቶ የሚሆነውን ታማሚ ማግኘት ያስችላልም ተብሏል።

    ምናልባት የቫይረሱ ምልክት ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ማድረግዎትን እንኳን ባያውቁ ይህንን መተግበሪያ በመጠቀም ማወቅ ይችላሉ። ከዚያም አካላዊ ርቀትን በመጠቀም ሁኔታዎን መከታተል ይችላሉ።

    በቫይረሱ የተያዘ ሰው ጋር ግንኙነትም ከነበረዎት መተግበሪያውን በመጠቀም ማወቅ የሚችሉ ሲሆን ከዚያም ራስዎን ለይተው እንዲያቆዩና ወደ ጤና ማእከላት መሄድ ያስችልዎታል።

  20. እስራኤል የተወሰኑ ሱቆች እንዲከፈቱ ፈቀደች

    እስራኤል

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    እስራኤል ወረርሽኙን ተከትሎ ከጣለቻቸው እገዳዎች መካከል የተወሰኑ ንግድ ተቋማት እንዲከፈቱ ፈቀደች። ትምህርት ቤቶችንም ለመክፈት እያሰበች እንደሆነ አስታወቃለች።

    በዚህም መሠረት በጎዳና ዳር ላይ የሚገኙ ሱቆች እንዲከፈቱ ተፈቅዷል።

    ይሁን እንጅ የገበያ ማዕከላትና የገበያ ቦታዎች ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተብሏል።

    ሆኖም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከመጣ የተደረጉት ለውጦቹ እንደገና ሊቀለበሱ እንደሚችሉ ባለስልጣናቱ አሳስበዋል።

    በአገሪቷ አዲስ በተጣለው ገደብ ምግብ ቤቶች፤ ወደ ቤት የሚወሰድ ምግብ እንዲያዘጋጁም ሆነ የማድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ አይፈቀድም።

    በእስራኤል እስካሁን 15 ሺህ 398 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 199 ሰዎች ሞተዋል።