ፈረንሳይ 20 ሺህ ሟቾችን በመመዝገብ አራተኛዋ አገር ሆነች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በፈረንሳይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሺህ በላይ ሆነ።
የአገሪቱ የጤና ዳይሬክተር "እጅግ በጣም የሚያሳምም" ባሉት ሪፖርታቸው በአገሪቱ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 20,265 መሆኑን ተናግረዋል።
ዤሮሜ ሳሎሞን እንዳሉት 12,513 ያክሉ በሆስፒታል የሞቱ ሲሆን 7,752 ደግሞ በአዛውንቶች መጦሪያ ውስጥ ህይወታቸው አልፏል።
በዚህም ፈረንሳይ ከ20 ሺህ በላይ ሟቾች ቁጥርን በማስመዝገብ አራተኛዋ አገር ሆናለች።
ከዚህ ቀደም ጣሊያን፣ ስፔን እና አሜሪካ ከ20 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን ከኮሮናቫይስ ጋር በተያያዘ አጥተዋል።
















