ጠ/ሚንስትሩ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎችም ስጦታ አበረከቱ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በኤካ ኮተቤ ሆስፒተሰል ተገኝተው በተቋሙ እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎችም የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸው ተነገረ።
ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማም፤ ከጠቅላይ ሚንትሩ እና ከቀዳማዊት እመቤት ጋር የፋሲካ በዓለን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ቦታዎችን ተዟዙረን ስጦታዎችን አበርክተናል ብለዋል።
በተመሳሳይ መሪዎቹ የአረጋውያንን ቤት ማደስ መርሀ ግብርን ያስጀመሩበት እማሆይ አዱኛ መኖሪያ ቤትና የአካባቢው ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት በመገኘትም የበዓል ስጦታዎችን አበርክተዋል ሲል ፋና ዘግቧል።
- በተጨማሪም አፍንጮ በር አካባቢ ሚገኝ የህፃናት ማሳደጊያ ተገኝተው የፋሲካ በዓል ስጦታ ማበርከታቸውን ተዘግቧል።