በደቡብ አፍሪካ ያለመሰብሰብ እገዳውን የጣሱ ሙሽሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሙሽሮችንና እድምተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተሰማ።
ሙሽሮቹ ከሚያጋባቸው ካህንና ከ40 እድምተኞች ጋር የተሰባሰቡት በደቡብ አፍሪካ የተጣለውን ከቤት ያለመውጣት ገደብ ጥሰው ነው ተብሏል።
ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ሙሽሮችና እድምተኞች እስር ቤት ያስገባ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።
በደቡብ አፍሪካ 1ሺህ 655 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙ 11 ሰዎች ደግሞ መሞታቸው ተመዝግቧል።
ደቡብ አፍሪካ ዜጎቿ ቤታቸው እንዲቀመጡ ካዘዘች ሁለት ሳምንት ሆኗታል።