ኮሮናቫይረስ፡ ቱኒዚያዊቷ በምትለቃቸው የዳንስ ትርኢቶችየግድያ ዛቻ ደረሰብኝ አለች
ቱኒዚያዊቷ ተዋናይት ከእስላማዊ ታጣቂዎች የግድያ ዛቻ ደረሰብኝ አለች።
ተዋናይቷ ማስፈራሪያው ደረሰብኝ ያለችው የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ተከትሎ በቤታቸው እያሳለፉ ያሉ ሰዎችን ለማዝናናት በማህበራዊ ሚዲያ የምትለቃቸውን እና የአረቦች ዳንስ ተብሎ የሚታወቀውን የዳንስ ትርኢት ተከትሎ ነው።
ዛቻው ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ካላቸውና መቀመጫውን በቱኒዚያ ካደረገ ቡድን ጋር ግንኙነት ካላቸው ሰዎች እንደደረሰባት ተናግራለች።
ኔርማይን በፌስቡክ የምትለቃቸው የዳንስ ቪዲዮዎች ከ10 ሺህ በላይ ተመልካቾችን አግኝተዋል።
ተዋናይቷ የዳንስ ትርኢቷን የምትለቀው ሰዎች በቤታቸው እንዲሆኑ ለማበረታታትና ባሉበት ለማዝናናት አስባ እንደሆነ ገልጻለች።