ኒውካስል ከአርሴናል፣ ማንቸስተር ሲቲ ከሊድስ. . . የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ግምት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናሉ።
ቅዳሜ አምስት ጨዋታዎች ሲካሄዱ እሑድ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ቀሪዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ሰኞ ምሽት እንዲከናወኑ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።
ትልቅ ግምት የተሰጠው የኒውካስል እና የአርሴና ጨዋታ እሑድ ይደረጋል።
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን እነዚህን ጨዋታዎች ውጤት ገምቷል።
ቅዳሜ
በርንመዝ ከ ቼልሲ
ተጠባባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ቼልሲ የደረሰው ፍራንክ ላማፓርድ ስድስተኛ ተከታታይ ጨዋታውን በአርሰናል ተሸንፏል።
ቡድኑ ከበርንመዝም ቀላል ፉክክር አይጠብቀውም።
ቡድኑ ዶምኒክ ሶላንኬን የመሳሰሉ ድነቅ ተጫዋቾችን ይዟል።
ላመፓርድ ሦስት ነጥብ የሚያሳካ አይመስለኝም። ከቡድኑ አቋም ሳይሆን ከያዛቸው ተጫዋቾች አንጻር ጨዋታውን አቻ ያጠናቅቃል።
ግምት፡ 1 - 1
ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊድስ
አዲሱ የሊድስ አሰልጣኝ ሳም አላርዲየስ ፔፕ ጋርዲዮላን ጨምሮ ከሊጉ አሰልጣኞች በላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሳም ትክክል መሆናቸውን ቅዳሜ የምንመለከተው ይሆናል።
ባለፈው ጨዋታ ሲቲ እንዳሰብኩት ዌስትሃም በቀላሉ ማሸነፍ አልቻለም።
የሊድስ ተከላካይ መስመር ካለው ክፍተት አንጻር ሲቲ ሦስት ነጥቡን ያሳካል።
ግምት፡ 3 – 0

ቶተንሃም ከ ክሪስታል ፓላስ
ይህንን ጨዋታ መገመት ከባድ ነው።
በጥር ወር ስፐርስ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 0 ቢያሸንፍም አሁንም ተመሳሳይ ውጤት መደገሙን እጠራጠራለሁ።
ፓላስ በአሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን ስር የተለየ ቡድን ሲሆን ስፐርስ ደግሞ ቀድሞ ጎሎችን የሚያስተናግድ ቡድን ሆኗል።
ሆኖም ሃሪ ኬንን በመያዛቸው ጨዋታውን ስፐርስ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 – 1
ዎልቭስ ከ አስቶን ቪላ
ይህም ለመገመት ከባድ ጨዋታ ነው። ባለፈው ጨዋታ ቪላ ማንቸስተር ዩናይትድን እንደሚያሸንፍ ብገምትም አልተሳካልኝም። ዎልቭስ ደግሞ በብራይትን ተደቁሷል።
ዎልቭስ በሜዳው ጥሩ ውጤት እያስመዘገበ ነው። ሆኖም ይህን ጨዋታ ቪላ የሚያሸንፍ ይመስለኛል።
ግምት፡ 0 – 1
ሊቨርፑል ከ ብሬንትፈርድ
የሊቨርፑል የአጥቂ መስመር ውጤታማ ሲሆን እንቅስቃሴያቸውንም ወድጄዋለሁ።
በሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።
ብሬንትፈርድ ከተወሰኑ ጨዋታዎች መቀዛቀዝ በኋላ ወደ ድንቅ ብቃታቸው ተመልሰዋል።
በጥር ወር ብሬንትፈርድ አሳማኝ በሆነ ሁኔታ ሊቨርፑልን አሸነፏል። አሁን የተለየ ውጤት አልጠብቅም።
ግምት፡ 1 – 2

እሑድ

ኒውካስል ከ አርሰናል
አርሴናል ባለፈው ጨዋታ ጥሩ የነበረ ቢሆንም የቼልሲ ደካማ መሆን ነው ጥሩ ያስመሰላቸው የሚሉም አሉ።
ጥሩ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኘው ኒውካስል ጋር ጎል ሳይቆጠር የሚጠናቀቅ አይመስለኝም።
አርሰናል በመሪው ማንቸስተር ሲቲ ላይ ጫናውን ለማጠናከር ማሸነፍ ብቻ ይጠበቅበታል። በዚህ ጨዋታ ግን ኒውካስል አሸንፎ በድንቅ ብቃቱ የሚቀጥል ይመስለኛል።
ግምት፡ 2 – 1
ዌስት ሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
የሊጉ ደረጃ በፍጥነት ቢለዋወጥም ዌስትሃም በሊጉ ለመቆየት አንድ ነጥብ ያስፈልገዋል።
ከዚህ ጨዋታ ምንም ነጥብ አያገኙም። ቡድኑ በጉዳት ቢሳሳም ማንቸስተር አሁንም ጨዋታ መቀየር የሚችሉ ተጫዋቾችን ይዟል።
ኤሪክ ቴን ሃግ ጨዋታ ሚያሸንፉበትን መንገድ ከመፍጠር ወደ ኋላ እንደማይሉ በተደጋጋሚ አሳይተዋል።
ግምት፡ 1 – 2

ሰኞ

ፉልሃም ከ ሌስተር
ጂሚ ቫርዲ ወደ ውጤታማነቱ መመለሱ ውጤት ለሚጠብቁት ሌስተሮች ጥሩ ዜና ነው።
ሌስተር ሁሉንም ነገር ቢያደርግም ጨዋታውን ፉልሃም ያሸንፋል። ፉልሃም ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ጥሩ ቢንቀሳቀስም በአንድ ጎል ልዩነት መሸነፉ ዕድለ ቢስነቱን ያሳያል።
ግምት፡ 2 – 1
ብራይተን ከ ኤቨርተን
በዚህ ጨዋታ ብራይተንን እደግፋለሁ።
ኤቨርትን የቆሙ ኳሶች አደገኛ መሆናቸውን አሳይተዋል። በሌላ በኩል ብራይተን ዕድል ለመፍጠር አይቸገርም።
ጥር ላይ እንዳደረጉት ሁሉ ይህንን ጨዋታም ብራይተን ያሸንፋል።
ግምት፡ 2 – 0
ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ሳውዝሃምፕተን
ከዚህ በፊት እንዳልኩት በሳውዝሃምፕተን ተስፋ ቆርጫለሁ። ከበርንመዝ ጨዋታ በኋላ ቀሪ ጨዋታዎቻቸውን እንደሚሸነፉ እገምታለሁ።
የሳውዝሃምፕተን ደጋፊዎች ቡድናቸውን ቢደግፉም በሃሳቤ እንደሚስማሙ አምናለሁ።
የልጅነት ቡድኔ ኖቲንግሃም ፎረስት በሊጉ ይቆያል። ከባድ ጨዋታዎች ቢጠብቋቸውም ይወጡታል።
ይህ ጨዋታ አሸንፈው የሚነሳሱበት ሲሆን ሳውዝሃምፕተን ደግሞ ከሊጉ መውረዱን ያመነ ይመስላል።
ግምት፡ 2 – 1












