ፕሪሚየር ሊግ: 'አርሰናል ከ10 ዓመታት በኋላ በሊጉ ሊቨርፑልን በአንፊልድ ያሸንፋል'

ሳካ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

የበርካቶችን ቀልብ ይዞ የሚገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሳምንቱ ጨዋታዎች ለዋንጫ የሚፎካከረውን አርሰናልን ወደ ሊቨርፑል ሲወስድ በወራጅ ቀጠና የሚገኙ ክለቦችንም ያገናኛል።

የሳምንቱ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ቅዳሜ ከሰዓት ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።

የቢቢሲ የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን የጨዋታ ግምቶቹን እንደሚከተለው ሰጥቷል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኤቨርተን

ዩናይትድ ከ ኤቨርተን

ዩናይትድ በቀጣይ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊነቱን ለማረጋገጥ በሜዳው እንደዚህ አይነት ጨዋታዎችን ማሸነፉ ግድ ነው ይላል።

ኤቨርተን ምንም እንኳ ከሜዳው ውጪ የሚያስመዘግበው ውጤት አመርቂ ባይሆንም ዩናይትድን መፈተናቸው አይቀርም ይላል።

ግምት፡ ማንቸስተር ዩናይትድ 2 1 ኤቨርተን

ቀይ መስመር

አስቶን ቪላ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ፎረስት ከሜዳቸው ውጭ ደካማ አቋም እያሳዩ ስለመቆየታቸው በተደጋጋሚ ስገልጽ ቆይቻለሁ።ይህን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብዬ አልጠብቅም።

በተቃራኒው ቪላ ከፍ ብለው እየበረሩ ይገኛሉ።ኡናይ ኤምሪ ክለቡን ከተረከቡ በኋላ አስደናቂ ጨዋታ እና ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።

ቪላዎች ብዙ ዕድሎችን የሚፈጥሩ ሲሆን ኦሊ ዋትኪንስ አጋጣሚዎችን ወደ ግብ ይቀይራል ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ ቪላ 2 0 ፎረስት

ብሬንትፎርድ ከ ኒውካስል

ብሬንትፎርድ ከ ኒውካስል

ኒውካስል በወሳኝ ጊዜ አራት ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችለዋል። የኤዲ ሃው አጨዋወት ስልት አድናቂ ነኝ። ኒውካስሎች ለየትኛውም ክለብ የሚመለሱ አይመስሉም።

ብሬንትፎርድም ቢሆን አጨዋወቱ አስደናቂ ነው። ብዙ ጨዋታ አይሸነፉም። ከቀናት በፊት በዩናይትድ ቢሸነፉም በዚህ የውድድር ዓመት በተከታታይ ሽንፈት አላስተናገዱም።

ይህ ጨዋታ አቻ የመጠናቀቁ ዕድል ሰፊ ቢሆንም ይህን ጨዋታ ኒውካስል ያሸንፋል የሚል ግምት አለኝ።

ግምት፡ ብሬንትፎርድ 1 2 ኒውካስል

ቀይ መስመር

ፉልሃም ከ ዌስት ሃም

ሌላ ለመገመት የሚያዳግተው ጨዋታ ይህ ነው። ፉልሃም በደረጃ ሰንጠረዡ አጋማሽ ላይ እንደመሆኑ በአውሮፓ ሊግ ለመሳተፍ የሚያሳካው ነገር ያለ አይመስልም።

ፉልሃም ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪያቸው አሌክሳንደር ሚትሮቪች ውጪ ነው ዌስት ሃምን የሚያስተናግዳው።

በሜዳው በኒውካስል አሳፋሪ የ5ለ1 ሽንፈት የተከናነበው ዌስት ሃም ደግሞ ከሜዳው ውጪ ዘመኑን በሙሉ ደካማ አቋም ሲያሳይ ቆይቷል። ዌስት ሃም ከሜዳው ውጪ ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው 1 ጨዋታ ብቻ ነው።

ግምት፡ ፉልሃም 1 1 ዌስት ሃም

ቀይ መስመር

ሌስተር ከ ቦርንመውዝ

ይህን ጨዋታ ውጤት መገመት ቀላል አይሆንም። ይህ በሳምንቱ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል አንዱ ነው። የወራጅ ቀጠና ፍጥጫ።

ሌስተር እራሳቸውን እዚህ ሁኔታ ውስጥ ማግኘት በጭራሽ አልነበረባቸውም። ቦርንመዞች በውድድር ዓመቱ በሙሉ የወራጅ ቀጠና አካባቢ ቢቆዩም አሁን ላይ ከሊጉ ላለመውረድ ተጋድሎ እያደረጉ ይገኛሉ።

ቼሪዎች ይህን ጨዋታ ባያሸብፉም ጎል እንደሚያስቆጥሩ እገምታለሁ።

ግምት፡ ሌስተር 2 1 ቦርንመውዝ

ቶተነሃም ከ ብራይተን

ቶተነሃም ከ ብራይተን

ብራይተኖች በቀጣይ ዓመት በአውሮፓ ሊግ የመጫወት ህልማቸውን ማሳካት የሚችሉት መሰል ጨዋታዎችን ሲያሸንፉ ነው።

በሊጉ ቶተነሃም በ50 ነጥብ 5ኛ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሁለት ተከታታይ ጨዋታ የሚቀረው ብራይተን በ46 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ስፐርስ በራስ መተማመን እና የጨዋታ እቅድ ያላቸው አይመስሉም። ቶተነሃም በደጋፊው ፊት በብራይተን ይሸነፋል የሚል ግምት አለኝ።

ግምት፡ ቶተነሃም 1 2 ብራይተን

ዎልቭስ ከ ቼልሲ

ዎልቭስ ከ ቼልሲ

ቼልሲ ላምፓርድን መልሶ ማምጣቱ ግራ የሚያጋባ ውሳኔ ነው። ላምፓርድ ይዞ የሚገባው አሰላለፍ ለማየት ጓጉቻለሁ። የቼልሲን አጨዋወት እና አሰላለፍ መገመት ሰለሚከብድ የጨዋታ ውጤት ግምት መስጠት ከባድ ነው። ስለዚህ ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል።

ግምት፡ ዎልቭስ 1 1 ቼልሲ

ቀይ መስመር

ሳውዝሃምፕተን ከ ማንቸስተር ሲቲ

ሁሉም ሰው ሲቲ ከዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥቦችን እንደሚሰበስብ እርግጠኛ ነው። ክሎፕ ግን ቡድናቸው ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ሴንትስ ሜዳ ባቀና ወቅት የተፈጠረውን የሚረሱት አይመስለኝም። ሲቲ በካራባኦ ዋንጫ በሳውዝሃምፕተን ተሸንፎ ነበር።

ሃላንድ ወደ ሜዳ ይመለሳል። ሲቲ ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ ሳውዝሃምፕተን 0 3 ማንቸስተር ሲቲ

እሁድ

እሁድ ከሰዓት ሁለት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። ሊድስ እና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን ያስተናግዳሉ።

ሊድስ ከ ፓላስ

ሊድስ ከ ክርስታል ፓላስ

ሮይ ሆድሰን ወደ ፓላስ ከተመለሱ በኋላ በመጀመሪያ ጨዋታው ድል ከማድረጋቸው በተጨማሪ ፓላስ ጥሩ ተጫውቷል።

ቢሆንም ግን ሊድስ በሜዳው ጥሩ ሪከርድ ስላለው ይህን ጨዋታ ሊያሸንፍ ይችላል ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ ሊድስ 1 0 ፓላስ

ሊቨርፑል ከ አርሰናል

ሊቨርፑል ከ አርሰናል

የሊቨርፑል የቻምፒንስ ሊግ የተሳትፎ ጉዞ አብቅቶለታል። የሊቨርፑል አጥቂ መስመር ጥሩ ሆኖ ሳለ የተከላካይ መስመሩ ግን ለቡድኑ ትልቅ ክፍተት ሆኗል።

የተከላካይ መስመሩ የአርሰናል አጥቂዎችን ማስቆም የሚቻለው አይመስለኝም።አርሰናል በዚህ አጨዋወቱ በአንፊልድ ጎል እንደሚያስቆጥር እጠብቃለሁ።

መድፈኞቹ ከ2012 ጀምሮ በአንፊልድ አላሸነፉም። ሊቨርፑልን ይፈሩ ነበር። አሁን ግን ያ ጊዜ አልፏል።