ሊቨርፑል፣ አርሰናል፣ ማንቸስተር ሲቲ. . . የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

አስቶን ቪላ ከኒውካስል ዩናይትድ

የፎቶው ባለመብት, PA Media

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቅዳሜ፣ እሑድ እና ሰኞ ይከናወናል።

የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከጫፍ የደረሰው ሊቨርፑል እና በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አርሰናል በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙትን ሌሰትር ሲቲን እና ኢፕስዊች ታወንን ያስተናግዳሉ።

በሰባተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አስቶን ቪላ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ኒውካስል ጋር የሚያደርጉት የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ነው።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን እነዚህን እና ቀሪዎቹን የሳምንቱን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ግምቱን አስቀምጧል።

ቅዳሜ

ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን

ብራይተን አቋሙ ከመውረዱም በላይ ጎሎችን በማስተናገዱ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዞ የማጠናቀቁ ነገር ጥያቄ ውስጥ እየገባ ነው።

ቡድኑ የለም ሲባል ደግሞ መነሳት የሚችል መሆኑን ደጋግሞ አሳይቷል።

ብሬንትፎርድን ማሸነፍ ደግሞ ከባድ ነው።

ግምት፡ 1 – 1

ክሪስታል ፓላስ ከ በርንመዝ

ፓላስ በሳምንቱ አጋማሽ በኒውካስል 5 ለምንም ተሸንፏል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ደግሞ ክለቡ በተመሳሳይ 5 ጎሎች በማንቸስተር ሲቲ ተቆጥረውበታል።

በርንመዝ ባለፈው ሳምንት ፉልሃምን ማሸነፍ ቢችልም ባለፉት ጨዋታዎች የአቋም መውረድ አሳይቷል።

ግምት፡ 1 – 1

ኤቨርተን ከማንቸስተር ሲቲ

ኤቨርተን ከ ማንቸስተር ሲቲ

ይህ ጨዋታ በምን መልኩ ይጠናቀቃል የሚለውን ለመገመት ከባድ ነው።

ኤቨርተን በኳስ ቁጥጥር የበላይ ሳይሆንም ጎል ለማስቆጠር ይሞክራል።

ሲቲ ደግሞ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ በሚቀትለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ጫና አለበት።

ጨዋታው በሲቲ የበላይነት ይጠናቀቃል።

ግምት፡ 1 – 2

ዌስት ሃም ከ ሳውዝሃምፕተን

ሳውዝሃምፕተን ከሊጉ መውረዱን ቢያረጋግጥም ዝቅተኛ ነጥብ ይዞ በመውረድ ክብረወሰኑን ከሰበረው ደርቢ ጋር አቻ ለመሆን ከቀሪ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ይፈልጋል።

ዌስትሃም ከሊጉ የመውረድ ስጋት ባይኖርበትም ደረጃውን ለማሻሻል ይፈልጋል።

ቡድኑ አሸንፎ አስቸጋሪውን የውድድር ዓመት በጥሩ ጎኑ ማጠናቀቅ የደጋፊዎቹ ፍላጎት ነው።

ግምት፡ 2 – 0

አስቶን ቪላ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

የካራባኦ ዋንጫን ከማንሳት ባሸገር በአሁኑ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ በምርጥ ብቃት ላይ የሚገኘው ቡድን ኒውካስል ዩናይትድ ነው።

ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አስቶን ቪላም በሊጉ አራት ጨዋታዎችን በተታታይ ማሸነፍ ችሏል።

እስከአምስት ያለውን ደረጃ ለመያዝ ካለው ጠቀሜታ አንጻር ከፍተኛ ፉክክር የሚደረግበት ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ሁለቱም ጨዋታውን ሊያሸንፉበት የሚችሉበት ዕድል ቢኖርም ከወቅታዊ አቋም አንጻር ኒውካስል ቅድሚያውን ይወስዳል።

ግምት፡ 1 – 2

እሑድ

ፉልሃም ከ ቼልሲ

ቼልሲ ቤት አንድ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ።

ባለፈው ሳምንት ላለመውረድ ከሚታገለው ኢፕስዊች ጋር አቻ ተለያዩ። በኋላም አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ደጋፊዎቹ ቡድኑን እንዲያምኑ እና ተጫዋቾች የደጋፊዎች ጫና እየተሰማቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

ሚሊዮን ዶላሮች የፈሰሳበቸው ተጫዋቾች ጫናውን መቋቋም ካልቻሉ በሂደት ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ።

ከበርንመዝ ጋር ነጥብ መጋራት የነበረባቸው ፉልሃሞች በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያሳካሉ።

ግምት፡ 2 – 1

ኢፕስዊች ታወን ከ አርሰናል

አርሰናል በቻምፒዮንስ ሊጉ ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ በጥሩ ስሜት ላይ ይገኛሉ።

ለዚህ ጨዋታ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ ተጫዋቾችን አሳርፈው ጨዋታውን እንደሚጀምሩ ቢጠበቅም ሚሰለው ቡድን ለኢፕስዊች አይተኛም።

ኢፕስዊች ባለፈው ሳምንት 2 ለምንም ከመምራት ከቼልሲ ጋር አቻ መለያየታቸው የውድድር ዘመናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ግምት፡ 0 – 2

ማንቸስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ዎልቭስ

ዎልቭስ ዘንድሮ ማንቸስተር ዩናይትድን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በወቅታዊ አቋምም የማሸነፍ ቅድሚያውን ግምት ያገኛል።

የቪቶር ሄሬራ ቡድን አራት ተከታታይ ቸዋታዎችን ያሸነፈ ሲሆን ዩናይትድ ደግሞ ወጥነት ይጎድለዋል።

ካለው አቋም አንጻር በዚህ ጨዋታ ቡርኖ ፈርናንዴዝ ጎል ሊያስቆጥር ይችላል።

የዩናይትድ የውድድር ዓመት የሚወሰነው በሽርፍራፊ ሰዓቶች ሊዮንን አሸንፈው ሩብ ፍጻሜ በደረሰቡት የዩሮፓ ሊጎ ጉዞ ላይ ነው።

ለዩናይትድ ደጋፊዎች በሜዳቸው ሌላ ከባድ ሽንፈት ይጠብቃቸዋል።

ግምት፡ 1 – 3

ሌስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል

ሌስተር ባለፈው ሳምንት ከብራይተን ጋር አቻ በመለያየት ያለመሸነፍ ጉዞውን ለመግታት ችሏል።

ሊቨርፑል ባለፈው ሳምንት ከዌስት ሃም ጋር ጥሩ ባይሆንም ለማሸነፍ ችሏል። በዚህ ጨዋታም ጥሩ ሳይንቀሳቀሱ አሸንፈው የበለጠ ወደ ሊጉ ዋንጫ ይቃረባሉ።

ግምት፡ 0 – 3

ሰኞ

ቶተንሃም ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ቶተንሃም ሐሙስ ምሽት በዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ኢንትራ ፍራንክፈርትን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ መደረሱ ደጋፈዎችን አስደስቷል።

ኖቲንግሃም ፎረስት መልሶ ማጥቃት ሃያልነቱን ደጋግሞ ያሳየ ሲሆን በታህሳስ ወር በ30 በመቶ የኳስ ቁጥጥር ብቻ ቶተንሃምን 1 ለምንም ማሸነፉ አንዱ ማሳያ ነው።

ባለፉት ጥቂት ጨዋታዎች ግን ፎረስት የአቋም መዋዠቅ አሳይቷል።

ቡድኑ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ ትኩረት ቢሰጥም ጨዋታው አቻ ይጠናቀቃል።

ግምት፡ 1 – 1