የአሜሪካ ሊግ ቡድኖች፤ ሜሲ ከመጣ ‘ለደሞዙ ከካዝናችን እናዋጣለን’ አሉ

ታትሟል

ማንቸስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን አማካይ በሚመጣው ክረምት የመሸጥ ዕቅድ እንደሌላው ፉትቦል ኢንሳይደር ዘግቧል።

የ27 ካልቪን ፊሊፕስ ከሊድስ ዩናይትድ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ከመጣ በኋላ ለሲቲ ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የተሰለፈው።

ነገር ግን ፊሊፕስ በፔፕ ጉዋርዲዮላ ቡድን የመሰለፍ ዕድል እየተሰጠው ስላለሆነ ሲቲን መልቅ እንደሚፈልግ '90ሚን' የተሰኘው ድረ-ገፅ ፅፏል።

ካልቪን ፊሊፕስ ምንም እንኳ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለሲቲ የተወሰኑ ጨዋታዎችን ብቻ ቢጫወትም በአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አባል ሆኖ ተመርጧል።

የአርሰናሉ የክንፍ መስመር ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ከክለቡ ጋር አዲስ ውል ሲፈፅም፣ በዓመት 15 ሚሊዮን ፓውንድ ሊያገኝ ይችላል ይላል የሜል ዘገባ።

የፒኤስጂው አርጀንቲናዊ አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር (የአሜሪካ እግር ኳስ ሊግ) የሚመጣ ከሆነ 29 የሊጉ ክለቦች ለደሞዙ እንደሚያዋጡ ስፖርት የተሰኘው የስፓኒሽ ጋዜጣ አስነብቧል።

ጋዜጣው እንደሚለው የሊጉ ክለቦች ከሳምንታት በፊት ተሰባስበው ተጫዋቹን ለማስፈረም በወጠኑበት ወቅት ደሞዙን አዋጥተው ለመክፈል ተስማምተዋል።

ክለቦቹ ለተጫዋቹ ደሞዝ ሲያዋጡ ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ ለፈለገው ክለብ እንዲጫወት እንደሚፈቅዱለት ተሰምቷል።

በሌላ ዜና የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የቼልሲውን የ31 ዓመት አማካይ ንጎሎ ካንቴ ለማስፈረም እንደሚሻ ተዘግቧል።

በማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በጥብቅ እየተፈለገ ያለው ናይጄሪያዊው አጥቂ ቪክተር ኦሲምሄን ዋጋ ተተምኖለታል።

ክለቡ ናፖሊ ተጫዋቹን ማስፈረም የሚፈልግ ቢያንስ 150 ሚሊዮን ዩሮ መክፈል አለበት ማለቱን የጣሊያኑ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ፅፏል።

የእንግሊዙ ክለብ ቶተንሃም ባለፈው ሳምንት ከሥራው የተባረረው የባየርን ሙኒኩን አሠልጣኝ ለማስፈረም እንደሚፈልግ ሜል ዘግቧል።

ቶተንሃም ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ ከጀመርናዊው አሠልጣኝ ጁሊያን ናግልስማን ጋር እንደተገናኘ ታይምስ አስነብቧል።

የቶተንሃም ሊቀመንበር ዳኒኤል ሌቪ፤ ናግልስማንን ለማስፈረም ቢፈልጉም አሠልጣኙ በሪያል ማድሪድ እና ቼልሲ ይፈለጋል።

ምንም እንኳ ባየርን ሙኒክ አሠልጣኙን ባልተጠበቀ ሁኔታ ቢያባርርም የክለቡ ተጫዋቾች ለሁለት ተከፍለዋል ይላል የጎል ዘገባ።

አንቶኒዮ ኮንቴ ድጋሚ ወደ አሠልጣኝነት ከመመለሱ በፊት ትንሽ እረፍት ማድረግ እንደሚፈልግ ተሰምቷል።

ኢንተር ሚላን፣ ኤሲ ሚላን፣ ጁቬንቱስ እና ሮማ ኮንቴን ማምጣት ይሻሉ።

የ32 ዓመቱ የሊድስ ዩናይትድ አጥቂ ሮድሪጎ በክለቡ ለመቆየት የሚያስችለውን ማራዘሚያ ፊርማ ካኖረ ደሞዝ መቀነስ ይኖርበታል።

እንደ ፉትቦል ኢንሳይደር ዘገባ ስፔናዊው አጥቂ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ያለው ፊርማ በሚመጣው ክረምት ይጠናቀቃል።

ቼልሲ በሚመጣው ዓመት በርካታ ተጫዋቾችን በመሸጥ ከፍተኛ ገንዘብ ገቢ ካላደረገ የፍትሐዊ ገንዘብ አጠቃቀም ሕግን በመጣስ ሊከሰስ እንደሚችል የታይም ዘገባ ይጠቁማል።

እንደ አትሌቲክ ዘገባ ከሆነ የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ ዮርገን ክሎፕ የእንግሊዛዊውን አማካይ ጄምስ ሚልነር ውል ማራዘም ቢፈልጉም ክለቡ ዳተኛ ሆኗል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር እየተያያዘ የሚገኘው የ18 ዓመት አየርላንዳዊ አጥቂ ኢቫን ፈርጉሰን በቶተንሃም በፅኑ እንደሚፈለግ የፉትቦል ኢንሳይደር ይጠቁማል።

ሰኞ ምሽት በተደረገ የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አየርላንድ በፈረንሳይ 1 ለ 0 ተሸንፋለች።