የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታዎች ግምት

የሊቨርፑሉ ዲያጎ ጆታ እና የቼልሲው ኤንዞ ፈርናንዴዝ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የሊቨርፑሉ ዲያጎ ጆታ እና የቼልሲው ኤንዞ ፈርናንዴዝ
ታትሟል

በሳምንቱ መጨረሻ የ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የካራባኦ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

አራት ዋንጫዎችን ለማንሳት ተስፋ ያለው ሊቨርፑል የመጀመሪያውን ለማሳካት እሑድ ከቼልሲ ጋር ይፋለማል።

በዚህ ጨዋታ ምክንያት በሊጉ ቼልሲ እና ቶተንሃም ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ደግሞ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የሊጉን ጨምሮ የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታውን ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ቅዳሜ

አስቶን ቪላ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

እነዚህ ሁለት ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ማሸነፍ ችለዋል። ፎረስት ውጤታማ አለመሆኑ መሻሻል እያስመዘገበ መሆኑን ሸፍኖታል።

ቪላ በሜዳው ያለው ጠንካራ አቋም ባለፉት ሦስት የሜዳው ጨዋታዎች በመሸነፉ ሊቀጥል አልቻለም። የኦሌ ዋትኪንስ ወደ አቋሙ መመለሱ ቡድኑን ወደ ድል እንዲያመራ ያግዘዋል።

ግምት፡ 2 – 0

ብራይተን ከ ኤቨርተን

ኤቨርተን ባለፈው የውድድር ዓመት መጨረሻ ብራይተንን አሸንፎ ከሊጉ ከመውረድ መትረፉን አረጋግጧል።

ላለፉት ሳምንታት ማሸነፍ ያልቻሉት ኤቨርተኖች ተመሳሳይ ድል ይጠብቃሉ።

ብራይተን ጎል ማምረት ቢጀምርም ይህንን ጨዋታ ኤቨርተን እንደሚያሸንፍ እጠብቃለሁ።

ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ተከላክለው በመልሶ ማጥቃት ይጫወታሉ። ከተሳካላቸው ሦስት ነጥቡን ያገኛሉ።

ግምት፡ 1 – 2

ክሪስታል ፓላስ ከበርንሌይ

ክሪስታል ፓላስ ከ በርንሌይ

በአርሴናል ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ ከበርንሌይ ምን መጠበቅ እንደሚገባ ግራ ያጋባል።

ከፓላስ አንጻር የተሻለ ዕድል ቢኖራቸውም አዲስ ከተሾሙት አሠልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር ምን እንደሚጠበቅ ማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል።

በአንድ ጊዜ ከአንድ አጨዋወት ወደ ሌላ መቀየር ከባድ ቢሆንም ባለሜዳዎች ውጤታማ እንደሚሆኑ እጠብቃለሁ።

ግምት፡1 – 0

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ፉልሃም

ማንቸስትር ዩናይትድ አምስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ከማሸነፉም በላይ አጥቂው ራስመስ ሆይሉንድ ጎል ማስቆጠሩን ቀጥሎበታል።

ፉልሃም ክራቨን ኮቴጅ ላይ በዩናይትድ ዕድለኛ ሳይሆን ቢሸነፍም ከሜዳ ውጭ ያለው አቋሙ ጥሩ አይደለም።

ፉልሃም መልሶ ማጥቃት ስለሚወድ ጨዋታው ለዩናይትድ ቀላል አይሆንም። የኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን አሁን በነጻነት በመጫወት ላይ በመሆኑ የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

ግምት፡ 2 – 1

በርንመዝ ከ ማንቸስተር ሲቲ

ማንቸስተር ሲቲ ባለፈው ማክሰኞ ብሬንትፎርድን ሲያሸንፉ ጥሩ ባይሆኑም ዋናው ጉዳይ ውጤቱ ነው።

በዚህ ሳምንትም በተመሳሳይ ሲቲ ተፈትኖም ቢሆንም ሦስት ነጥቡን ያሳካል።

በርንመዝ ሲቲ ላይ ጎል ከማስቆጠር የዘለለ የሚያገኙት ነገር አይኖርም።

ግምት፡ 1 – 3

አርሰናል ከኒውካስል

አርሰናል ከ ኒውካስል

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሲገናኙ ኒውካስል ያሸነፈበትን ጎል ጨምሮ በርካታ ውዝግቦች ነበሩ። ይህ ደግሞ ጨዋታው በውጥረት እንዲጀመር ያደርገዋል።

አርሴናል በሳምንቱ አጋማስ ከፖርቶ ጋር በነበረው ጨዋታው አስደሳች ፖርቶም ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓል።

ኒውካስልም ተመሳሳይ አጨዋወት ቢከተልም መድፈኞቹ የሚያሸንፉ ይመስለኛል።

ግምት፡ 2 – 1

እሑድ

ዎልቭስ ከ ሼፊልድ ዩናይትድ

ይህንን ጨዋታ ዎልቭስ ያሰንፋል። ዋናው ጥያቄ በስንት ጎል የሚለው ነው።

እስከማስበው ሼፊልድ ከሊጉ ይወርዳል።

ዎልቭስን በሜዳቸው ቢያሸንፉም ሼፊልዶች በየሳምንቱ የሚሸነፉ ይመስላል።

ግምት፡ 2 – 0

ቼልሲ ከሊቨርፑል

ቼልሲ ከ ሊቨርፑል (የካራባኦ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ)

ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንፊልድ ላይ ሁለቱ ቡድኖች ተገናኝተው ሊቨርፑል 4 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።

ውጤቱ ግን ይህንን የፍጻሜ ጨዋታ የሚወስነው አይሆንም።

ቼልሲ ባለፈው ሳምንት ሲቲን ለረዥም ደቂቃ መርቶ አቻ መውጣቱን ለተመለከተ በዚህ ጨዋታ የማሸነፍ ዕድል እንዳለውም ማንሳት ይችላል።

ሊቨርፑል ደግሞ ሞሐመድ ሳላህን ጨምሮ በርካታ አጥቂዎቹ ተጎድተውበታል።

ከሉተን ጋር በነበረው የመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታ ሊቨርፑል ጥሩ ባይሆንም ከእረፍት መልስ ተሻሽሎ ቀርቧል። በዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች የሚኖራቸው አሰላለፍ ተጠባቂ ነው።

ግምት፡ 1 – 2 (ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ)

ሰኞ

ዌስት ሃም ከ ብሬንትፎርድ

ሁለቱም ቡድኖች ከዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥቦችን ማሳካተን አጥብቀው ይፈልጋሉ። ብሬንትፎርድ ከሲቲ ጋር ጥሩ የተጫወተ ሲሆን ይህንን ፍልሚያም በድል እንደሚወጣ ይሰማኛል።

በዌስት ሃሙ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስ ዙሪያ ያለው ሁኔታ ቡድኑ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል።

የአሰልጣኙ ጉዳይ ቡድኑ በሜዳው በሚያደርገውን ጨዋታ በራስ መተማመን እንዲያጣ አድርጎታል።

ለቡድኑ ጥሩ ቢሠራም አሁን ደጋፊዎች ጀርባቸውን ሰጥተውታል።

ግምት፡ 1 – 2

ዌስት ሃም ከብሬንትፎርድ