የሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ
የምስሉ መግለጫ, ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ
ታትሟል

የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ ያለፈው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሰርዘው ነበር።

ይህም ሕዳር ላይ ከሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ጋር ተደማምሮ ለፕሮግራም መጣበብ ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኗል።

የስምንተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ይከናወናሉ።

በዚህ ሳምንትም ሦስት ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል።

አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ የሚካሄዱትን ሰባት ጨዋተዎች ግምት ቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ እንደሚከተለው ቃኝቷቸዋል።

አርብ

አስቶን ቪላ ከ ሳውዝ ሃምፕተን

አሰልጣኝ ዤራርድ ጫና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ ጨዋታ ለቪላ ትልቅ ትርጉም አለው።

ሳውዝ ሃምፕተን ከቪላ የተሻለ ጥሩ አጀማመር አሳይቷል።

የቪላ ደጋፊዎች ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ያገኛሉ።

ጨዋታው ጥሩ ፉክክር የሚኖረው ሲሆን ቪላ ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 – 1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ፉልሃም

2-0 ከመምራት በበርንማውዝ ለተሸነፉት ፎረስቶች ይህ ጨዋታ ወሳኝ ነው።

ሽንፈቱ ለቡድኑም ሆነ ለደጋፊዎቹ ጥሩ አይመስለኝም። ከፉልሃም ጋር በሚኖረው ጨዋታቸው የሚሰጡት ምላሽ ይጠበቃል።

ባለፈው ዓመት ሁለቱ ቡድኖች በሻምፒዮንሺፑ ለይ ሲገናኙ ፉልሃም 4 ለ 0 አሸንፏል። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ዘንድሮም የተለየ ውጤት አልጠብቅም።

ግምት፡ 0 – 2

ቅዳሜ

ዎልቭስ ከ ማንችስተር ሲቲ

ባለፈው ሁለቱ ቡድኖች ተጫውተው ማንቸስተር ሲቲ 5 ለ 1 ሲያሸንፍ በሜዳው ውስጥ ነበርኩ። በዕለቱ ኬቪን ደ ብሩይን ድንቅ ነበር።

ዎልቭሶች አሁን ኤርሊንግ ሃላንድንም እንዴት ማስቆም እንዳለባቸው ሊጨነቁ ይገባል።

ዎልቭሶች ጎል እንደሚያስቆጥሩ ባስብም ሲቲ ያሸንፋል።

ግምት፡ 1 - 3

ብራይትን ከ ክሪስታል ፓላስ

ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።

ኒውካስል ከ በርንማውዝ

የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሆዊ የቀድሞ ክለባቸውን ለማሸነፍ ይጫወታሉ። ማሸነፍ እንደሚችሉም ብዙ ምክንያት ማስቀመጥ ይቻላል።

ኒውካስል በማጥቃት የሚጫወት ሲሆን የተወሰኑ ጎሎችንም ማስቆጠር አለባቸው።

ብርንማውዞች ባለፈው ከፎረስት ጋር ከመመራት ተነስተው ባሸነፉበት መነሳሳት ለመቀጠል ይሞክራሉ።

ብርንማውዞች ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አላስብም።

ቶተንሃም ከ ሌስተር

ቶተንሃም ከ ሌስተር

ቶተንሃም በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በስፖርቲንግ ሊዝበን ተሸንፏል።

ባለፉት ሳምንታት ውጤታቸው ሜዳ ውስጥ ያለውን አቋማቸውን ያሳያል ብዬ አላስብም።

ሌስተሮች በማጥቃት መስመር ጥሩ ቢሆንም የተከላካይ ስፍራ ላይ ብዙ ክፍተት አለባቸው።

ሶን ሁዩንግ ሚን በዚህ ጨዋታ ወደ ጎል ማስቆጠር ይመለሳል ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ 4 – 1

ብሬንትፎርድ ከ አርሰናል

እሑድ

ብሬንትፎርድ ከ አርሴናል

ብሬንትፎርዶች ባለፈው ውድድር ዓመት ወደ ሊጉ እንደመጡ አርሴናልን በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር አድርገዋል። በዚህ ጨዋታም ትልቅ ፉክክር ይኖራል።

አርሰናሎች ባለፉት 12 ወራት ተሻሽለዋል። ብሬንትፎርዶች ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊድስ ጋር ያላቸውን አቅም ማሳየት ችለዋል።

ስለዚህ በዚህ ጨዋታ አርሰናል የሚፈተንበት ይሆናል።

ከዚህ ጨዋታ ብርንትፎርዶች ነጥብ እንደሚያገኙ ይሰማኛል።

ግምት፡ 1 - 1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊድስ

ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።

ኤቨርትን ከዌስት ሃም

ሁለቱም ቡድኖች ዕድለኞች አይደሉም እንጂ አሁን ካላቸው የተሻለ ነጥብ ማግኘት ነበረባቸው።

ኤቨርተኖች በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ።

ከሊቨርፑል ጋር ጥሩ የነበሩ ሲሆን ለማሸነፍ የሚከብዱ ሆነዋል።

ማሸነፍ የሁለቱም ቡድኖች የውድድር ዓመት የሚያቃና ይሆናል። ዌስት ሃም ሦስት ነጥብ ያሳካል ብዬ አስባለሁ።

ባለፈው ዓመት በሁለቱም ጨዋታዎች ዌስትሃሞች ያሸነፉ ሲሆን ዘንድሮም የተለየ አይሆንም።

ግምት፡ 1 - 2

ቼልሲ ከ ሊቨርፑል

ይህ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል።