የፑቲን አጋር የሆኑት ግለሰብ ልጅ የተገደለችው በዩክሬን እንደሆነ ሩሲያ ከሰሰች

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የሩሲያው ፕሬዝዳንት የቅርብ አጋር የሆኑት ግለሰብ ሴት ልጅ የተገደለችው በዩክሬን ልዩ ኃይል በተቀነባበረ ሴራ ነው ስትል ሩሲያ ከሰሰች።
የ29 ዓመቷ ጋዜጠኛ ዳሪያ ዱጊና ቅዳሜ ዕለት ከሞስኮ አቅራቢያ መኪናዋን እያሽከረከረች ሳለ በተከሰተ ፍንዳታ ነው የተገደለችው።
አባቷ አሌክሳንደር ዱጊና፣ ታዋቂ አክራሪ የሩሲያ ብሔረተኛ ሲሆኑ ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ሰው እንደሆኑ ይነገራል።
ልጃቸውን የገደለው ጥቃት ኢላማም እሳቸው ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል።
የሩሲያ ፌደራል የደኅንነት አገልግሎት (ኤፍኤስቢ) ጥቃቱን ፈጻሚ እንደለየ እና ለዚህም በቀጥታ ተጠያቂዋ ዩክሬን ናት ብሏል።
ነገር ግን የዩክሬን ባለሥልጣናት ቀድመው በዚህ የፍንዳታ ጥቃት ውስጥ እጃቸው እንደሌለበት አስተባብለዋል።
የሩሲያ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ባወጣው እና በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ላይ በቀረበ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፣ ባለፈው ሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ የዩክሬን ልዩ ኃይል የቀጠራት ነፍሰ ገዳይ ከሕጻን ልጇ ጋር ወደ ሩሲያ ገብታለች።
ጨምሮም ግለሰቧ የሟቿን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለመከታተል እንዲያመቻት ከምትኖርነት ሕንጻ ላይ ቤት ተከራይታ ነበር ብሏል።
ተጠርጣሪዋ ሦስት የተለያዩ የሰሌዳ ቁጥሮች ያሉት መኪና ትጠቀም እንደነበር አመለክቷል።
የታዋቂውን የፑቲን የቅርብ ሰው ሴት ልጅ የገደለው ፍንዳታ ከተፈጸመ በኋላ ተልዕኮውን ፈጽማለች የተባለችው ግለሰብ ወደ ጎረቤት አገር ኢስቶኒያ ማምለጧን የሩሲያ ደኅንነት መሥራያ ቤት ገልጿል።
አሌክሳንደርዱጊና ማን ናቸው?
“የፑቲንአንጎል” በመባል የሚታወቁት ሩሲያዊው ፈላስፋ አሌክሳንደር ዱጊና ልጃቸው የተገደለችበት ጥቃት ዋነኛ ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል።
ዱጊናየሩሲያው ፕሬዝዳንት የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚታመን ታዋቂ አክራሪ የሩሲያ ብሔረተኛ አስተሳሰብ አራማጅ ናቸው።
የሩሲያ ሚዲያ 112 እንደዘገበውዱጊን ባለቀ ሰዓት ከልጃቸው ተነጥለው ለመጓዝ ከመወሰናቸው በፊት ቅዳሜ ምሽት ከተካሄደው አንድ ዝግጅት መገባደድ በኋላ አብረው ሊመለሱ አቅደው ነበር።
በቴሌግራምላይ የተለቀቀ ያልተረጋገጠ ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይየድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች ሲረባረቡና በድንጋጤ የሚቃጠለውን ተሽከርካሪ ሲመለከቱ ይታያል።
ቢቢሲተተንቀሳቃሽ ምሥሉን ማረጋገጥአልቻለም።
የሕግአስከባሪ አካላት ታስ ለተሰኘው የዜና ወኪል እንዳረጋገጡት አንዲት ሴት አሽከርካሪ በቦልሺዬ ቪያዚሚ መንደር መኪናዋ ፈንድቶ ሕይወቷ ማለፉን ተናግረዋል። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ግን አልሰጡም።
በመንግሥትአስተዳደር ውስጥ ይፋዊ ወንበር ባይኖራቸውም የዱጊን አባት የሩሲያው ፕሬዝዳንት የቅርብ አጋር ሲሆኑ “የፑቲን ተጽዕኖ ፈጣሪም” ይባላሉ።
የፈላስፋውልጅ ዳሪያ ዱጊና ታዋቂ ጋዜጠኛ ስትሆን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራንም በግልጽ የምትደግፍ ነበረች።












