ዩናይትድን ከቶተነሃም ያፋጠጠው የ11ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ዩናይትድ ከቶተነሃም

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

የቢቢሲው  የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን አንድንድ ጊዜ የሚሰጠው ግምት አስደንጋጭ የሚባል ነው።

ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑል በሜዳው በማንቸስተር ሲቲ 4 ለ 1 እንደሚሸነፍ ግምቱን አስቀምጦ ነበር።

በሊቨርፑል ዙሪያ ስሀተት ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።

በርንማውዞች ምን ይበሉ? ያለፉትን 10 ሳምንታት ጨዋታዎች በሙሉ እንደሚሸነፉ ግምቱን አስቀምጧል።

የ11ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ትላንት ምሽት ተጀምረዋል።

ሱቶን በብራይተን የበላይነት ይጠናቀቃል ያለው የብራይተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ ያለጎል አቻ ተጠናቋል።

ክሪስታል ፓላስ እና ዎልቭስ ደግሞ አንድ አቻ ይለያያሉ ሲል ግምቱን አስቀምጦ ነበር።

ፓላስ ግን ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሌሎች ጨዋታዎችን ግምት እንደሚከተለው እንቃኛለን።

ረቡዕ

አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ ማድረግ የነበረባቸው ይህ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።

በርንማውዝ ከ ሳውዝሃምፕተን

የትኛውም የበርንማውዝ ደጋፊ በማይጠብቀው መልኩ ቡድኑ ያሸንፋል ብዬ ግምቴን ላስቀምጥ።

በርንማውዝ ይህን ጨዋታ ማሸነፍ ይኖርበታል።

ሳውዝሃምፕተኖች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል።

በርንማውዞች ከፉልሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያስቆጠሩት የመጀመሪያ ጎል ድንቅ ነበር።

ግምት፡ 2 – 1

ብሬንትፎርድ ከ ቼልሲ

ብሬንትፎርድ ከ ቼልሲ

ቼልሲዎች ባለፈው እሁድ አስቶን ቪላን ማሸነፍ ችለዋል።

ከብሬንትፎርድ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። ከብራይተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ አጥቂ ክፍላቸው ወደ አቋሙ የተመለሰ መስሏል።

ቼልስ በጥሩ አቋም ላይ ካልተገኘ እና ብሬንትፎርዶች በተመሳሳይ መልኩ ከተጫወቱ አንድ ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ 1 – 1

ሊቨርፑል ከ ዌስት ሃም

ከሰሞኑ ከሊቨርፑል ደጋፊዎች ብዙ ትችት አስተናግጃለሁ።

ሊቨርፑል ከሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ በተለይም የኋላ መስመሩ አስደናቂ ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊው ከጎናቸው የቆመበት እና አንፊልድ ወደ ቀድሞ አቋሙ የተመለሰበት አጋጣሚ ነበር።

ወደ አቋማቸው ለመመለስ በተገቢው መንገድ ላይ ያሉ ይመስለኛል። የዌስትሃም የኋላ መስመር መሳሳት የሚረዳቸው ሲሆን ጂያንሉካ ሳማካ ደግሞ ጎል ያስቆጥራል።

ግምት፡ 3 – 1

ኒውካስል ከ ኤቨርተን

ኒውካስል ኦልትራፎድ ላይ አለማሸነፉ ትንሽ ዕድለ ቢስ ያደርገዋል። ቡድኑ ሚዛኑን ያገኘ ይመስላል።

በመከላከል በኩል ጥሩ ሲሆኑ የተወሰኑ ዕድሎችንም ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ለመፍጠር ችለዋል።

እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ውስጥ ለምን እንደተቀመጡ መረዳት የሚቻል ሲሆን አሁን ካላቸው ነጠብ የተሻለም ማግኘት ነበረባቸው።

ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፉት ኤቨርተኖች በዚህ ጨዋታም ይቸገራሉ ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 – 0

ማንቸስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም

ማንቸስተር ዩናይትዶች ከኒውካስል ጋር ዕድል ያመለጣቸው ይመስለኛል። የስፐርስ ጨዋታ ሌላ ጉዳይ ነው።

ሃሪ ኬን ዕድል ካገኘ ጎል የማስቆጠር ብቃቱ ላይ ይገኛል።

ዩናይትድ ደግሞ ጥርስ አልባ መሆኑን ባለፈው ሳምንት አሳይቷል። ቡድኑ ክርስቲያን ኤሪክሰንን በህምም ምክንያት ማጣቱ የጎዳው ሲሆን ለዚህ ለቀድሞ ክለቡ ጨዋታም ላይደርስ ይችላል።

ኤሪክሰን ቢሰለፍም አንቶኒዮ ኮንቴ በመልሶ ማጥቃት የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

ግምት፡ 1 – 3

ፉልሃም ከ አስቶን ቪላ

ሐሙስ

ፉልሃም ከ አስቶን ቪላ

አስቶን ቪላዎች ባለፈው ሳምንት ከቼልሲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ ቢሆኑም በዚያው አልቀጠሉበትም።

አሰልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጫና ውስጥ የወደቀ ሲሆን ደጋፊዎችም ፊታቸውን ያዞሩበት ይመስላል። ስለዚህ በዚህ ጨዋታ ጥሩ ውጤት ይጠብቃል።

ፉልሃም እና ብርንማውዝ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ፉልሃሞች አደገኛ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ። ይህ ጨዋታ አቻ ይጠናቀቃል ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 – 1

ሌስተር ከ ሊድስ

ሌስተሮች ተጽዕኖ ፈጠሪ የሆነውን ተጫዋቻቸውን ጀምስ ማዲሰንን በቅጣት አያገኙም።

በአርሰናል የተሸነፉበትን ጨምሮ ሊድሶች በዘንድሮው ዓመት እንደአጨዋወታቸው የሚገባቸውን ውጤት ያላገኙባቸው ጨዋታዎች አሉ።

በዚህ ጨዋታ ግን ይህንን የሚቀይሩበት እንደሚሆን እገምታለሁ።

አጨዋወታቸውንም የምወደው ሲሆን ተገቢውንም ነጥብ ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ 1 – 4