ተአምረኛው ሜሲ በ 1000ኛ ጨዋታው ላይ ለአገሩ ግብ አስቆጠረ

ሊዮኔል ሜሲ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ሜሲ የሁለት ግዜ የአለም ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነችው አገሩ አርጀንቲና አውትራሊያን በመርታት ወደ ሩብ ፍጻሜ ባለፈችበት ብሎም ለእርሱ 1000 ኛ ጨዋታው ላይ ግብ በማስቆጠር ታሪክ ሰርቷል።

ለፓሪስ ሴንት ጀርመን የሚጫወተው ሜሲ አስደናቂ አጨራረስ በማሳየት በመጀመሪያው ግማሽ ሰአት ጭንቀት ውስጥ ገብተው የነበሩትን የአገሩን ደጋፊዎች ያስፈነጠዘ ግብ አስቆጥሯል።

ግቡ ለሜሲ 789ኛ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 94ቱን ለአርጀንቲና ነበር ያስቆጠራቸው። ሜሲ በኳታሩ የአለም ዋንጫም የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ቦታ ለመጋራት ያስቻለውን ግብ ነበር ያስቆጠረው።  

አውስትራሊያ በመጀመሪየው 35 ደቂቃ አርጀንቲናን ብታርበደብድም በመጨረሻ የጨዋታ የበላይነት ተወስዶባታል። ስታዲየሙም ሜሲ ኳስ በመታ ቁጥር በጉጉት ይንቀጠቀጥ ነበር።

ተአምረኛው ሜሲ የምንግዜም ምርጡ ተጫዋች መባሉን በማስመስከር በአገሩ ማሊያ ታጅቦ አስደናቂ ጎል አስቆጥሯል።