ተጠባቂውን የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ማን በበላይነት ያጠናቅቃል?

ሊቨርፑል ከሲቲ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

በዚህ ሳምንትስ ከሊቨርፑል እና ከማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል?

“ወደ ኤሚሬትስ ስታዲም ከማቅናታቸው በፊት ሊቨርፑሎች ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ይመለሳሉ በሚል ግምቴን ስሰጣቸው ቆይቻለሁ” ይላል ሱቶን።

“ግን አልተሳካም። በቻምፒዮንስ ሊግ ሬንጀርስን 7 ለ 1 ማሸነፍ ቢችሉም ከፊታቸውን ከባድ ጨዋታ አለ።”

ሱቶን ይህንን ጨዋታ ጨምሮ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል።

አርብ

ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን

ውድድር ዓመቱን በድንቅ መንገድ የጀመሩት ብሬንትፎርዶች ከሰሞኑ ውጤት አልቀናቸውም። ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ተደቁሰዋል።

አዲስ አሰልጣኝ የሾሙት ብራይተኖች ደግሞ ምን ዓይነት ጉዞ እንደሚኖራቸው መገመት ከባድ ነው።

ሁሌም ግን ጠንካራ ሆነው ስለሚቀርቡ ይህንን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 2

ቅዳሜ

ሌስተር ከ ክሪስታል ፓላስ

ሌስተሮች በሜዳቸው ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ባደረጉት ጨዋታ ድንቅ ሆነው ቢያመሹም ከብርንማውዝ ጋር ደግሞ ደካማ ነበሩ።

ነገሮች የሚቀየሩ አይመስለኝም። የኋላ መስመራቸው ደካማ ሲሆን እነዊልፍሬድ ዛሃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ፓላሶችም ሊድስ እስኪያሸንፉ ድረስ መንሸራተት ጀምረው ነበር።

ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ይወጣሉ ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 - 2

ቶተንሃም ከ ኤቨርተን

ቶተንሃም ከ ኤቨርተን

ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተለይም ጎል ካስቆጠሩ በኋላ ኤቨርተኖች ከሚገባቸው በታች ነበር የተንቀሳቀሱት።

የቶፊዎቹ ተከላካይ መስመር መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ክፍት መሆኑን ዩናይትድ አሳይቷል።

ስፐርስን ማቆም ቀላል ቢሆንም ሃሪ ኬን እና ሶን ሄዩንግ-ሚን በጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ።

ስለዚህ ቶተንሃም የሚሳካለት ሲሆን የጎሉ መጠን የሚወሰነው ግን የመጀመሪያወን ጎል በሚያስቆጥሩበት ደቂቃ ይሆናል።

ግምት፡ 3 – 1

ፉልሃም ከ በርንዝማውዝ

ፉልሃሞች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ነበሩ።

አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ፍጹም ቅጣት ምት በመሰጠቱ ቢበሳጩም መናደድ ካለባቸው በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ አልሰማ ብሎ ስህተት በሠራው አንድሪያስ ፔሬራ ላይ መሆን ነበረበት።

ሁሌም በርንማውዝን ይሸነፋል እያልኩ ትክክል አለመገመቴን ያሳዩኛል። ደጋፊዎችም ይህን ይወዱታል።

በጋሪ ኦኒዬል ስር ብርንማውዞች ጥሩ ቢሆኑም ሦስቱን ነጥብ ለፉልሃም አሰጠላሁ።

ግምት፡ 2 – 1

ዎልቭስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ዎልቭሶች እስካሁን አሰልጣኝ ባይኖራቸውም በሚገባቸው መጠን መንቀሳቀስ ያልቻሉ ድንቅ ተጫዋቾችን ይዘዋል።

በወራጅ ቀጠና ውስጥ ቢሆንም ብቃቱን ማሳየት እንዳልቻለ ቡድን ነው የምመለከተው።

ኖቲንግሃም ፎረስትን ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ የምመለከተው ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከአስቶንቪላው ጨዋታ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል።

የፎረስት ተጫዋቾች ያልተዋሃዱ ሲሆን  በራሳቸው ላይ ያለቸው እምነትም እየተሸረሸረ ይመስለኛል።

ግምት፡ 2 – 0

አስቶን ቪላ ከ ቼልሲ

እሑድ

አስቶን ቪላ ከ ቼልሲ

የአስልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጉዳይ በአስቶን ቪላ ደጋፊዎች ዘንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ያገኘ አይመስልም።

ዋናው ምክንያት ደግሞ የሚመርጡት አጨዋወት ነው።

ፒየር-ኤመሪክ ኦባሚያንግ ጎል እያስቆጠረ ሲሆን አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርም የመላመድ ብቃታቸውን እያሳዩ ነው።

ቪላ በሜዳው የማሸነፍ ጫና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ተጫዋቾቹም ተጽዕኖው ያገኛቸዋል።

ግምት፡0 – 2

ሊድስ ከ አርሴናል

ሊድሶች ከፓላስ ጋር በነበራቸው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ቢሆኑም አልዘለቁበትም።

በዚህ ጨዋታም ሊድስ መጀመሪያ ላይ ተጭኖ ለመጫወት ቢሞክርም አይዘልቅበትም።

ካላቸው ጥሩ እንቅስቃሴ እና ካለፈው ሳምንት ውጤት በኋላ አርሴናሎች ጨዋታውን በበላይነት እንደሚያጠናቅቁ እገምታለሁ።

እንደምገምተው ሊድሶች አጥቅተው ለመጫወት ከሞከሩ ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ የመጫወቻ ክፍተት ይገኛሉ። ለጋብርኤል ጂሰስም ዕድሎችን ይፈጥራል።

ግምት፡ 1 – 3

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል

ይህን ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብዬ አልገምትም። ጥያቄው ኒውካስል አንድ ነጥብ ያገኛል ወይስ ሦስት ነጥብ የሚለው ነው።

ማንቸስተር በኤሪክ ቴን ሃግ ስር እየተሻሻለ መሆኑን እቀበላለሁ።

ከዚህ ይልቅ ኒውካስል በማጥቃት መጫወት በመጀመራቸው እና ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠራቸው ነው።

አሰልጣኝ ኤዲ ሃዊ በኦልትራፎርድ አጨዋወታቸውን ይቀይራሉ ብዬ አልገምትም።

ይህ ደግሞ ቸዋታው ክፍት እንዲሆን ሲያደርግ ማንቸስተርንም ተጠቃሚ ያደርጋል።

ግምት፡ 1 – 1

ሳውዝሃምፕተን ከ ዌስት ሃም

ይህም ከባድ ጨዋታ ነው።

ሳውዝሃምፕተንን በማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ መገምገም ከባድ ነው።

አሰልጣኝ ራልፍ ላይ ያንዣበበው ጫና ባለመቀነሱ ከዚህ ጨዋታ ውጤት ይጠብቃሉ።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ ብገምትም ነገሮች ወደ ዌስት ሃም ያደሉብኛል።

ጂያንሉካ ስካማካን እወደዋለሁ። ዌስት ሃሞችም ወደ ድል መስመር ተመልሰዋል።

ግምት፡ 1 – 2

ሊቨርፑል ከ ማንቸስተር ሲቲ

ሊቨርፑልን ከዋንጫው ፉክክር ውጭ ማድረግ ከባድ ቢሆንም ሲቲ ወደ አንፊልድ አቅንቶ ማሸነፍ ከቻል ዕድል አይኖራቸውም።

ሲቲዎች ይህንን ስለሚያውቁ ይጠቀሙበታል። ኤርሊንግ ሃላንድ በሳምንቱ አጋማሽ እረፍት በማግኘቱ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል።

የሊቨርፑል አጨዋወት ለሃለንድ ስለሚመች ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

ሊቨርፑሎች ዕድል መፍጠር ቢችሉም ማንቸስተር ሲቲ ባለው አቋም በላይ መሆኑ ግልጽ ነው።

በ2021 የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አራት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ተመሳሳይ ጎል እጠብቃለሁ።

ግምት፡ 1 - 4