ህንዳዊቷ “ራሷን ለማግባት” ማቀዷ ያስነሳው ውዝግብ  

ክሻማ ቢንዱ

የፎቶው ባለመብት, Kshama Bindu

ታትሟል

ፅንሰ ሃሳቡ ሶሎጋሚ ይባላል።  ግለሰቦች ራሳቸውን የሚያገቡበት የሰርግ ስነ ስርዓት ነው። በምዕራቡ ዓለም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እያደገ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በህንድም ተጀምሯል።

ክሻማ ቢንዱ በምዕራብ ጉጅራት ግዛት በምትገኘው በቫይዶራ ከተማ ቤተ መቅደስ ከሳምንት በኋላ በባህላዊ የሂንዱ የእምነት መሰረት የሰርግ ስነ ስርዓት ለማካሄድ እቅድ አውጥታለች።

እምነቱ በሚያዘው መሰረት ቀይ የሙሽራ ልብሷን ለብሳ፣ እጆቿን በሂና አቅልማ፣ የቫርሚሊየን ዱቄት በጸጉሯ ላይ ነስንሳ ቅዱስ በሚባለው እሳት ሰባት ዙሮችን እንደምታደርግ ከቤቷ ሆኗ በስልክ ነገረችኝ።

ከሠርግ በፊት ያሉ ስርዓቶችም የሚከናወኑ ሲሆን ሃልዲ የተሰኘውና ሙሽራዋ እርድ ከዘይት ጋር ተቀላቅሎ የምትቀባበት እንዲሁም የሙዚቃ እና ውዝዋዜ ስርዓት የሆነውም ሳንጌትም ከሰርጉ አንድ ቀን ቀደም ብሎም ይከናወናሉ።

ከሠርጉ በኋላ ለሁለት ሳምንት የጫጉላ ሽርሽሯን ለማድረግ ያቀደች ሲሆን በዚህም ወደ ጎአ ከተማ ታቀናለች። 

ከሁሉም ክብረ በዓላት ብቸኛው የጎደለው ቢኖር ሙሽራው ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ቢንዱ ራሷን ለማግባት ስላቀደች ነው ምናልባትም በህንድ የመጀመሪያው ሶሎጋሚ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

“በርካቶች በጣም ጥሩ እንደሆንኩና ሊያገቡኝ የሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ይነግሩኛል” የምትለው የ24 አመቷ የሶሺዮሎጂ ተማሪ እና ጦማሪ “እኔ ራሴን አግብቻለሁ እላቸዋለሁ” ብላለች።

ራሷን በማግባት፣ ቢንዱ፣ ህይወቷን "ራሷን ለመውደድና ለማፍቀር" ትሰጣለች።

"ራስን ማግባት ለራስህ ለመኖር ቁርጠኝነትን ማሳየት ነው። የምፈልገውን ህይወት፣ መተዳደሪያና የኑሮ ዘይቤ እንድመርጥ እንዲሁም ለማደግ፣ እያንዳንዷን የህይወቴን ምዕራፍ ትርጉም ባለው መልኩ እንድኖር እንዲሁም ጥልቀት የተሞላበት ደስታ እንዳገኝም የሚያስችለኝ ነው” ትላለች።

"የተለያዩ ማንነቶቼን እንደምቀበል የማሳይበት መንገድ ነው። በተለይም ድክመቶቼን ለመካድ ወይም ለመካድ የሞከርኳቸውን አካላዊ፣አእምሮአዊ ወይም ስሜታዊ ይሁኑ።ለእኔ ይህ ጋብቻ ነው። በጣም ጥልቅ የሆነ ራስን የመቀበል ተግባር ነው። ለማለት የሞከርኩት ራሴን እቀበላለሁ ። ሁሉንም ማንቴን የሰውነቴን ክፍሎች ቆንጆ የማይመስሉ ክፍሎችን የመቀበል ተግባር ነው”

ቢንዱ እንደነገረችኝ ቤተሰቦቿ እንደተቀበሏትና ምርቃታቸውንም እንደሰጡ ከጓደኞቿ ጋርም ሆነው በሰርጓ ስነ ስርዓትም ላይ ይገኛሉ።

“እናቴ ሁልጊዜ አዲስ ነገር ታስቢያለሽ ትለኛለች። ነገር ግን ወላጆቼ ሊበራል ስለሆኑ ውሳኔዬን በበጎ ነው ያዩት። ደስተኛ እስካደረገሽ ድረስ እኛ ውሳኔሽን እንቀበላለን አሉኝ” አለች።

የሰርግ መጥሪያ ወረቀት

የፎቶው ባለመብት, Kshama Bindu

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

 

 ራስን “ማግባት” የሚለው ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው ከ20 አመት በፊት ገደማ በፊት ታዋቂ በሆነው የአሜሪካ ሴክስ ኤንድ ዘ ሲቲ ተከታታይ ፊልም ገጸ ባህርይ ከሆነችው ኬሪ ብራድሾው ነበር። ፊልሙ አስቂኝ ድራማም ስለሆነም ብዙም ልብ ያለው አለው አልነበረም።

ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በመቶዎች የሚቆጠሩ እንዲህ ያሉ ጋብቻዎች በተለይም የፍቅር ጓደኛ በሌላቸው ሴቶች እንደሚፈጸሙ ነው።

ሙሽሮች እቅፍ አበባ ይዘው በሚያምር የሰርግ ቬሎ ተውበው አንዳንዴ በቤተሰቦች እና ጓደኞች ታጅበው ብቻቸውን ሲዳሩ ተመልክተናል።

እናም ከነዚህ ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ የ33 ዓመቷ ብራዚላዊት ሞዴል ራሷን ባገባች ቦሶስት ወሯ ከራሷ ጋር ፍቺ መፈጸሟ ነው ።

በተለያዩ ዓለማችን ይህንን የሰርግ ስነ ስርዓት በማየት ንግዶች ተጧጡፈዋል። ለብቻ የሚሆን ቀለበት፣ የቃለ መሃላ ካርዶች ለምሳሌ “አዎ ግሩም ነኝ” የሚሉና ሌሎችም እንዲሁ መታየት ጀምረዋል።

ነገር ግን እንደዚህ አይነት ታሪኮች በህንድ ውስጥ እስካሁን ያልተሰሙ በመሆናቸው የቢንዱ የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ዜና መነጋገሪያ መሆኑ አልቀረም።

ያነጋገርኳቸው አንድ የአእምሮ ጤና ባለሙያ “ሶሎጋሚ” የሚለው ፅንሰ ሃሳብ በሚወክለው ነገር ተገርመዋል።

“ለእኔ በጣም እንግዳ የሆነ ፅንሰ-ሀሳብ ይመስላል” ሲሉም በቻንዲጋርህ ከተማ በፒግመር ሆስፒታል የቀድሞ ዲን እና የአእምሮ ህክምና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ሳቪታ ማልሆትራ ተናግረዋል።

"ሁሉም ሰው ራሱን ይወዳል። ራስን መውደድ ለማሳየት መበታተን ወይም ውጫዊ ቅጂ መፍጠር አያስፈልግም። ለሁላችንም ውስጣዊ ነው። እና ጋብቻ ማለት ሁለት አካላት አንድ ላይ የሚጣመሩበት ነው” ይላሉ።

ዜናው በማህበራዊ ሚዲያ ክርክርና ውዝግብ አስነስቷል። አንዳንዶች ብዙዎችን ለበጎ ያነሳሳል ሲሉ ያሞገሷት ሲሆን አብዛኛዎቹ ግን ሶሎጋሚ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ግራ እንደገባቸው ነው።

በትዊተር ሃሳቧን የገለጸች አንዲት ሴት ሌላ ሰው ከሌለ የጋብቻ አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ እንደሆነ ጥያቄ አንስታለች።

ሌላኛዋ ደግሞ ቢንዱ ከቤተሰብ ሀላፊነቶች ለመሸሽ እየሞከረች እንደሆነ ተናግራለች።

አንዳንዶች ሶሎጋሚን “አስገራሚ እና አሳዛኝ ድርጊት” ሲሉ ተችተው “ሥር የሰደደ ራስ ወዳድነት” ነው ሲሉም ወቅሰዋል።

ለተቺዎቿ ቢንዱ የምትለው "አንድ ነገር ብቻ" አለ ይህም "እኔ የፈለግኩትን ለማግባት የእኔ ውሳኔ ነው “ የሚል ነው፤ ወንድ ወይም ሴት ወይም ራሴን።ራሴን በማግባት ሶሎጋሚን የተለመደ ፅንሰ ሃሳብ የማድረግ ፍላጎቱ አላት።

ለሰዎች መንገር የምፈልገው ወደዚህ አለም የንመጣው ብቻችን ነው ትተናትም የምንሄደው ብቻችንን ነው። ታዲያ ከራሳችን በላይ የሚወደን ማን ነው? ከወደቅን ራሳችንን ማንሳት ያለብን እኛው ራሳችን ነን።