የገንዘብ ኖት እጥረት ባጋጠማት ናይጄሪያ በሁለት ከተሞች ባንኮች ላይ ጥቃት ደረሰ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አዲስ የገንዘብ ኖት ማግኘት አስቸጋሪ በሆነባት ናይጄሪያ የተለያዩ ከተሞች ብስጭት ያስከተለው ተቃውሞ ተቀስቅሷል።
አዲስ የናይራ የገንዘብ ኖቶችን ያስተዋወቀችው ናይጄሪያ ያጋጠማት የኖት እጥረት ብስጭት ጭሯል።
በደቡብ የናይጄሪያ ክፍል በሚገኙና ዋሪ እንዲሁም ቤኒን በተባሉ ሁለት ከተሞች ላይ ደንበኞች ባንኮችን በእሳት ማቃጠላቸው ተነግሯል።
በናይጄሪያ ገንዘብ ለማግኘት በገንዘብ አቅራቢ ተቋማትና ማሽኖች ጋር ረጅም ሰልፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
በሀገሪቱ ባለው የገንዘብ ኖት እጥረት ምክንያት የምግብ ሰዓታቸውን ለመዝለል መገደዳቸውን እና ያለክፍያ ለመስራትና ለምግብና ትራንስፖርት ለመክፍል መቸገራቸው ይነገራል።
በአንዳንድ ባንኮች ተቃዋሚዎች ጥሰው በመግባት የክፍያ ማሽኖችን ዘርፈዋል። በቤኒን ከተማ ደንበኞች የማዕከላዊ ባንኩን አከባቢያዊ ቅርንጫፍ ለመውረር የሞከሩ ቢሆነም በጸጥታ ሃይሎች አስለቃሽ ጭስ ተተኩሶባቸዋል።
የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ በኢኮኖሚው ውስጥ የተሰራጩና የቆሸሹ ኖቶችን ለማስወገድ፣ የዋጋ ንረትን ለመቀነስ፣ መጭበርበርን ለመቀነስ እንዲሁም ያለጥሬ ገንዘብ በዲጂታል መንገድ ኢኮኖሚውን ማንቀሳቀስን ለማበረታታት በሚል የ200፣ 500 እና የ1000 ሺህ ገንዘብ ኖቶችን ቀይሯል።
ባለፈው ጥቅምት ወር ወር የገንዘብ ኖቶቹ ላይ ስለሚደረገው ለውጥ የተነገራቸው ሲሆን ያላቸውን ጥሬ ገንዘብ በባንክ እንዲያስቀምጡ ተጠቅመው ነበር።
ሆኖም ጥሬ ገንዘብ አሁንም በስፋት ጥቅም ላይ በሚውለባት ሀገር አዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች በበቂ ሁታ አልተሰራጩም። ከናይጄሪያ ጠቅላላ ህዘብ 40 በመቶ የሚገመመቱት የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ አይደሉም።
ኢባዳን በተባለችው ከተማ የራሳቸውን ገንዘብ ከባንክ ማውጣት ያልቻሉና ንዴት የገባቸው በርካታ ሰዎች መንገድ የዘጉ ዘግተዋል። የማዕከላዊ ባንክ ሰራተኞች ላይም ጥቃት አድርሰዋል።
በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጩ ቪዲዮዎች ብሰጭታቸውን የሚገልጹ ናይጄሪያውንን ታይተውበታል።
በሀገሪቱ ጠቅላላ ምርጫ ሊካሂድ 10 ቀናት ብቻ የቀሩ ሲሆን ገዢው ፓርቲ በምርጫው ድምጽ እንዳያጣ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ ቦሃሪ ችግሩን ለመፍታት እርምጃ እንዲወስዱ እየተጠየቁ ነው።












