ሲቲ ከ አርሰናል፡ የዋንጫውን ባለቤት ሊለይ የሚችለውን ጨዋታ ማን ያሸንፋል?

የሲቲ አሰልጣኝ ጋርዲዮላ እና የአርሰናሉ አርቴታ
የምስሉ መግለጫ, የሲቲ አሰልጣኝ ጋርዲዮላ እና የአርሰናሉ አርቴታ
ታትሟል

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከእረፍት በኋላ ሲመለስ “የዋንጫውን ባለቤት ሊለይ የሚችል” ፍጥጫን ያሳየናል።

የ2023/24 የውድድር ዓመት ሊጠናቀቅ 10 ጨዋታዎች ብቻ ይቀራሉ።

በሊጉ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ያሉት ቡድኖች የነጥብ ልዩነታቸው 1 ብቻ ነው።

የፊታችን እሁድ ደግሞ የሊጉ መሪዎች ካለፈው ዓመት ሻምፒዮኖች ጋር ይጋጠማሉ።

የቢቢሲ የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ይህ ጨዋታ ዋንጫው ወደዬት ሊሄድ እንደሚችል ጠቋሚ ሊሆን ይችላል ይላል።

ኒውካስትል  ከ ዌስትሃም

ኒውካስል ከ ዌስትሃም

ኒውካስል በዚህ የውድድር ዓመት ኒውካስል ብቸኛው የቀረው ነገር ቢኖር በሊጉ የተሻለ ድረጃን ይዞ መጨረስ ነው።

ከኤፍኤ ዋንጫ የተወገዱት ኒውካስሎች ከዚህ ጨዋታ ነጥብ ማግኘት ከፈለጉ የኋላ መስመራቸውን አጠናክረው ወደ ሜዳ መግባት ይኖርባቸዋል።

ዴቪድ ሞዬስም ቢሆኑ ከደጋፊዎች እየቀረቡባቸው ካለው ትችት እራሳቸውን ሊታደጉ የሚችሉ ከዚህ መሰል ጨዋታ ነጥብ በማግኘት ነው።

ከዚህ ጨዋታ ሙሉ ነጥብ ማግኘት ለሁለቱም ቡድን ቀላል አይሆንም። ነገር ግን ባለሜዳዎቹ በደጋፊዎቻቸው ታጅበው ይህን ጨዋታ ሊያሸንፉ ይችላሉ።

ግምት፡ ኒውካስል 2 - 1 ዌስትሃም

ውጤት፡ 4 - 3

ቦርንመዝ ከ ኤቨርተን

የሾንዳይሽ ቡድን በሊጉ ድልን ከተጎናጸፈ በጣም ቆይቷል። ቡድኑ በሆነ አጋጣሚ ወደ ድል ለመመለስ ጽኑ ፍላጎት ያላው ቢሆንም ይህ ሊሳካላቸው አልቻለም።

ችግራቸው የሚያገኙትን አጋጣሚ ወደ ጎል መቀየር አለመቻላቸው ነው።

ቦርንመዝ ከአሁን በኋላ የመውረድ ስጋት አለበት ብዬ አላስብም። ቦርንመዝ በመጀመሪያው ጨዋታ ጉዲሰን ፓርክ ላይ ተሸንፎ የነበረ ቢሆንም፣ በሜዳቸው ለኤቨርተን እጅ ይሰጣል ብዬ አላስብም።

ግምት፡ ቦርንመዝ 1 - 1 ኤቨርተን

ውጤት፡ 2 - 1

ቼልሲ ከ በርንሊ

ቼልሲ ከ በርንሊ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የፖቼቲኖ ቡድን ወጥ የሆነ አቋምን እያሳየ ይገኛል። በኤፍኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆናቸው ምናልባት በሊጉ ያሳለፉት መጥፎ ጊዜ በኤፍኤ ዋንጫ ይካካስ ይሆናል።

ከዚህ ጨዋታ በርንሊ ምንም አያገኝም። በርንሊ በጭራሽ ቼልሲን አይቋቋምም።

ግምት፡ ቼልሲ 2 - 0 በርንሊ

ውጤት፡ 2 - 2

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ክርስታል ፓላስ

ፎረስት ባለፈው ጨዋታ ሉተንን ማሸነፍ ነበረበት። በዚያ ጨዋታ የጣሉት ነጥብ ላለመውረድ በሚያደርጉት ትግል ላይ ልዩነት ፈጣሪ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ።

የነጥብ ቅነሳ ከተደረገባቸው በኋላ በሜዳቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚጫወቱት ፎረስቶች ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም።

በተመሳሳይ ክርስታል ፓላስ የሰሞኑ አቋማቸው ጥሩ አይደለም። ከሉተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ ሙሉ ነጥብ መሰብሰብ ሲገባቸው አቻ ተለያይተዋል።

አንድ በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ከፓላስ በላይ ይህን ጨዋታ ለማሸነፍ ተጋድሎ የሚያደርጉት ፎረስቶች ናቸው።

ግምት፡ ፎረስት 1 - 0 ፓላስ

ውጤት፡ 1 - 1

ሼፊልድ ከ ፉልሃም

ሼፊልድ ከ ፉልሃም

ባለፈው ጨዋታ ፉልሃም ሳይጠበቅ ቶተነሃምን መጨዋች ነበር ያደረጓቸው።

የማርኮ ሲልቫ ቡድን ከሳምንት ሳምንት መሻሻሎችን እያሳየ ነው። ሼፊልድ እጅ ላለመስጠት ብዙ ይጠራሉ ጥረታቸው ግን በቂ አይሆንም።

ግምት፡ ሼፊልድ 0 - 2 ፉልሃም

ውጤት፡ 3 - 3

ቶተንሃም ከ ሉተን

የሰሜን ለንደኑ ክለብ በፉልሃም ከደረሰበት አሳፋሪ ሽንፈት በኋላ ወደ ሜዳው ይመለሳል።

ጨዋታቸውን መመልከት ከሚስደስተኝ ቡድኖች መካከል ሉተን አንደኛው ነው።

በቶተንሃም ላለመሸነፍ ብዙ ጥረት እንደሚያደርጉ እጠብቃለሁ። ጎልም ያስቆጥራሉ ብዬ እገምታለሁ። ግን ድሉ የቶተነሃም ይሆናል።

ግምት፡ ቶተነሃም 4 - 1 ሉተን

ውጤት፡ 2 - 1

አስተን ቪላ ከ ዎልቭስ

ቮልቭስ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ በኮቫንተሪ ተሸንፈው ከኤፍኤ ዋንጫ ቢወገዱም በፕሪሚየር ሊጉ ጥሩ የውድድር ዓመት እያሳለፉ እንደሚገኙ እገምታለሁ።

የቡድኑ አባላትን ያጋጠማቸው የጉዳት መጠን ግን ችግር ሊሆን ይችላል።

ቪላ ከዚህ ቀደም በሜዳቸው ባደረጉት ጨዋታ በቶተነሃም ቢሸነፉም ዳግም በደጋፊዎቻቸው ፊት ይሸነፋሉ ብዬ አልጠብቅም።

ግምት፡ ቪላ 2 - 1 ዎልቭስ

ውጤት፡ 2 - 0

ብሬንትፎርድ ከ ማን ዩናይትድ

ብሬንትፎርድ ከ ማን ዩናይትድ

ይህን መገመት አዳጋች ሊሆን ይችላል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ይህ ጨዋታ የተጠናቀቀው በብሬንትፎርድ 4 ለ 0 አሸናፊነት ነበር።

አሁን ላይ ደካማ አቋም ላይ የሚገኙት ንቦቹ ይህን መድገም አይቻላቸውም። ነገር ግን ነጥብ መጋራት ይችላሉ።

ይህ ጨዋታ ለኤሪክ ቴን ሃግ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።

ግምት፡ ብሬንትፎርድ 2 - 2 ዩናይትድ

ውጤት፡ 1 - 1

ሊቨርፑል ከ ብራይተን

ክሎፕ ሊቨርፑልን ሲሰናበቱ የብራይተኑ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ሊቨርፑልን ሊረከቡ ይችላሉ የሚል ወሬ አለ። ይህ ቢሆንም የዲ ዘርቢ ልጆች አንፊልድ ላይ ማሳካት የሚከብዳቸውን ለማድረግ ብዙ መጣራቸው አይቀርም።

አንድ ማስታወስ ያለብን ነገር ብራይተን አንፊልድ ላይ ከተሸነፈ ሰነባብቷል። ቀያዮቹ ብራይተንን አንፊልድ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፉት 2019 ላይ ነው።

ይሁን እንጂ የሊቨርፑል ወቅታዊ አቋም ጠንካራ በመሆኑ ይህን ጨዋታ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ እገምታለሁ።

ግምት፡ ሊቨርፑል 3 - 1 ብራይተን

ማንቸስተር ሲቲ ከ አርሰናል

ማንቸስተር ሲቲ ከ አርሰናል

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ አርሰናል በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ጎል አስቆጥሮ ኤምሬትስ ላይ ሲቲን በጠባብ የጎል ልዩነት አሸንፎ ነበር።

በዚህ ጨዋታም ብዙ ጎል እንደማይቆጠር እገምታለሁ። የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የሚሆነው ብዙ ኳስ በተቆጣጠረ ሳይሆን፣ የሚገኝ ድንገተኛ አጋጣሚን የሚጠቀም ቡድን ነው።

ስለ ሲቲ ሳስብ በቅርቡ እያሳዩት ባለው እርግጠኛ አይደለሁም። የኳስ ፍሰታቸው እንደ ከዚህ ቀደሙ አይደለም።

በሊጉ እስከ አምስተኛ ደረጃ ያሉ ቡድኖችን በዚህ የውድድር ዓመት እስካሁን አላሸነፉም።

በሌላ አንጻር አርሰናል የሊጉ መሪ ነው። ብዙ ጎል አሰቆጥሮ ትንሽ ጎል የገባበት ቡድን ነው። ተከታታይ 8 የሊጉን ጨዋታዎችንም ማሸነፍ ችለዋል።

ይህ ጨዋታ ግን ማሸነፍ ቀላል አይሆንላቸውም። ሲቲ ተሸነፈ ማለት 9 ጨዋታ እየቀረ ከአርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 4 ይሆናል። ይህ እንዲሆን ጋርዲዮላ በጭራሽ አይፈቅም።

ግምት፡ ሲቲ 1 - 0 አርሰናል