ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህር ድንበርን ያቋረጠ ሚሳኤል ተኮሰች

የሰሜን ኮሪያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቷን ደቡብ ኮሪያ ጋር የሚለያትን የባህር ድንበር አቋርጣ ሚሳኤል ተኩሳለች። ይህም ሀገሪቱ ባህረ ገብ መሬቱን ከተካፈሉት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የተተኮሰው የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል በደቡብ ኮርያ ሶኮቾ ከተባለች ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ስፍራ ላይ አርፏል።

ይህም ደቡብ ኮሪያ ኡሌንጉዶ በተባለው ደሴቷ የሚገኘው አየር ሃይሏ በተጠንቀቅ እንዲቆም ያደረገ ነው።

ደቡብ ኮሪያ በአጸፋው ሶስት ሚሳኤሎችን አከታትላ ተኩሳለች።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ የፒዮንግኣንግን ድርጊት “የድንበር ወረራ” ስትል ጠርታዋለች።

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ቢያንስ 10 ሚሳኤሎችን እንደተኮሰች የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል።

ቀጥሎም ጦሩ ሶስት ከአየር ወደ ምድር የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን ወደ ሰሜን በአጸፋ እንደተኮሰ አስታውቋል።

ጦሩ “ በሰሜን ኮሪያ የሚፈጸሙ እንዲህ አይነት ጽብ አጫሪ ድርጊቶችን አይታገስም። በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ባለው ትብብር ጥብቅ ምላሽ ይሰጣል” ብሏል።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ ለተፈጸመው ጸብ አጫሪ ድርጊት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ማዘዛቸውም ተጠቁሟል።

ሰሜን ኮሪያን ድርጊት ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ብሄራዊ የድህንነት ምክክር ጠርተዋል።

ሁለቱ ሀገራት የድንበር ወሰን ያቋረጠውን ሚሳኤል ጨምሮ የተተኮሱ ሚሳኤሎችን መዝግበዋል።

ወሰኑን ያቋረጠ ሌላ ሚሳኤል ከደቡብ ኮሪያዋ ምስራቃዊ ከተማ ሶኬቾ 57 ኪሎ ሜትር ርቀት እና በሰሜን ምዕራብ ከምትገኘው ኦልንጎዴ ደሴት 167 ኪሎ ሜትር ርቀት ውሃማ አካል ላይ አርፏል።

ይህ ድርጊት “እጅግ ያልተለመደ እና ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ የተናገሩት የጥምር ጦር ዘመቻው መሪ ካንግ ሺንቹል ባህረገብ መሬቱ ከተከፈለ በኋላ በግዛት ውስጥ ላለ የውሃ አካል የቀረበ ተኩስ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎቹን ከማስወንጨፏ ቀድም ብሎ ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከባህረ ገቡ መሬት አቅራቢያ የሚያደርጉትን የጋራ ልምምድ እንዲያቆሙ አስጠንቅቃ ነበር።

ትላንትና ሰሜን ኮሪያ ጥምር ጦሩ ልምምዱን የማያቆም ከሆነ “ሃይለኛ” እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ ነበር። ፒዮንግያንግ ባለፈው ወር አሜሪካ፥ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ላደረጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አጸፋ ሚሳኤል ተኩሳ ነበር። ይህ ተኩስ ወደ ደቡብ ኮሪያ የተደረገ የኒውክሌር ጥቃት “አምሳያ” ነው ትብሏል።