የዘንድሮው የአዲስ ዓመት ገበያ በምስል

ታትሟል

በጦርነት፣ በረሃብ፣ በመፈናቀል በሌሎች ችግሮች የተሞላው አሮጌው ዓመት 2014 ዓመት ተጠናቆ አዲሱን ዓመት ተቀብለናል። የዛሬዋ መስከረም 01/2015 ዘመን መለወጫ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረች ትገኛለች።

ኢትዮጵያውያን በእንቁጣጣሽ እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ ወይም በቅርጫም ቢሆን የበሬ ሥጋቸውን በመጫረት ክብረ በዓሉን ያደምቁታል።

የሽንኩርቱ ቁሌት፣ የቅቤው ሽታ፣ የቡናው መዓዛና የእጣኑ ሽታ በየቤቱ ያውዳል፣ የእርዱ ሁካታ፣ የዘመድ አዝማዱ ሳቅ፣ የአገር ባህል ልብሱ፣ ሙዚቃው የአውደ ዓመቱ  መገለጫዎች ናቸው።

ቢቢሲ አማርኛም በአዲስ አበባ የተወሰኑ ስፍራዎች ተዘዋውሮ የገበያውን ሁኔታ ቃኝቷል።

አዲስ አመትን ከሚያደምቁ መካከል አደይ አበባ አንዷ ስትሆን በርካቶችም ቤታቸውን ቄጤማ በመጨመር ያደምቁበታል።
የምስሉ መግለጫ, አዲስ አመትን ከሚያደምቁ መካከል አደይ አበባ አንዷ ስትሆን በርካቶችም ቤታቸውን ቄጤማ በመጨመር ያደምቁበታል።
ኢትዮጵያውያን በእንቁጣጣሽ እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ ወይም በቅርጫም ቢሆን የበሬ ሥጋ በመጫረት ክብረ በዓሉን ያደምቁታል።
የምስሉ መግለጫ, ኢትዮጵያውያን በእንቁጣጣሽ እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ ወይም በቅርጫም ቢሆን የበሬ ሥጋ በመጫረት ክብረ በዓሉን ያደምቁታል።
የዶሮና እንቁላል ገበያ በአዲስ አበባ
በበርካታ በዓላት በርካቶች ሳር ይጎዘጉዛሉ
በእንቁጣጣሽ የአደይ አበባ ስጦታ መስጠት አንዱ የማህበረሰቡ መገለጫ ነው ነው
የምስሉ መግለጫ, በእንቁጣጣሽ የአደይ አበባ ስጦታ መስጠት አንዱ የማህበረሰቡ መገለጫ ነው ነው
በርካቶች በአዲስ አመት በቻሉት አቅም ዶሮ፣ በግም ይሁን የቻሉትን በመግዛት አውደ አመቱን ያከብሩታል
የምስሉ መግለጫ, በርካቶች በአዲስ አመት በቻሉት አቅም ዶሮ፣ በግም ይሁን የቻሉትን በመግዛት አውደ አመቱን ያከብሩታል
በእንቁጣጣሽ ወቅት የምትታየው አደይ አበባ የአዲሱ አመት ድምቀት ናት
የምስሉ መግለጫ, በእንቁጣጣሽ ወቅት የምትታየው አደይ አበባ የአዲሱ አመት ድምቀት ናት
መስከረም ሲጠባም በርካቶች ለሥራም ሆነ ለሌላ ጉዳይ በሌሎች ከተሞች፣ በየአገራቱ ያሉ አንድ ላይ ተሰባስበው ማዕድ የሚቆርሱበት ወቅት በመሆኑ ምግቡ ከሌላው በተለየ መልኩ ይዘጋጃል
የምስሉ መግለጫ, መስከረም ሲጠባም ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማዱ አንድ ላይ ተሰባስበው ማዕድ የሚቆርሱበት ነው።